Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 9 9

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

እንዲሁም በተፈጥሮ ላይ እርግማንን አስከትሏል፡፡ እግዚአብሔር በሴቲቱ ዘር እና በእባቡ መካከል ጠላትነትን ያስቀመጠ ሲሆን በሴቲቱም ዘር በኩል አመጽን ለማስቆም በሉአላዊ ቸርነቱ ቃል ገብቷል፡፡ በውድቀትም ምክንያት ፍጥረት ሁሉ በጦርነት ውስጥ ነው፤ እግዚአብሔርም ከእባቡና ከእርሱ ጋር ከሚቆሙ ሁሉ ጋር ጦርነት ውስጥ እንደሆነ አውጇል፡፡ በወንዝና በባህር ከተመሰለው ክፋት ጋር በሚያደርገው ጦርነት እንዲሁም ከፈርኦንና ከሰራዊቱ እና ከከነዓናውያን ጋር ባደረገው ውጊያ እግዚአብሔር ራሱን እንደ ተዋጊ አሳይቷል፡፡ በአሳዛኝ መልኩ ከአመጻቸውና አለመታዘዛቸው የተነሳ እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር ግጭት ውስጥ ለመግባት ተገዷል፡፡ በተጨማሪም የእስራኤል ነቢያት እግዚአብሔርን በመሲሁ በኩል ለአንዴና ለመጨረሻ ክፋትን ሁሉ እንደሚያጠፋ መለኮታዊ ተዋጊ መስለውታል፡፡ ይህ መሲሐዊ አገዛዝ በኢየሱስ ሰውነት ተጀምሯል፤ ውልደቱ፣ ተዓምራቶቹ፣ ትምህርቶቹ፣ አጋንንት ማስወጣቱ፣ ስራዎቹ፣ ሞቱና ትንሳኤው የእግዚአብሔርን መንግስት አምጥቷል፡፡ መንግስቱ “መጥቷል” ግን ደግሞ “ገና አልተጠናቀቀም”፤ ይህ መሲሐዊ ተሰፋ በክርስቶስ መፈጸም የጀመረ ቢሆንም ሙላቱን የሚያገኘው በዳግም ምጽአት ነው፡፡ ዛሬ በዚህ ዘመን የርስቷ መያዣ የሆነው የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነችው የኢየሱስ ክርሰቶስ ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር መንግስት ምልክትና ቅምሻ ነች፡፡ ቤተክርስቲያን ክርስቶስ በሰይጣንና በጭፍሮቹ ላይ የተቀዳጀውን ድል ታሳየን ዘንድ ስልጣን ተሰጥቷታል፡፡ እንግዲህ ሚሽን ማለት እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስና ወኪሉ በሆነችው ቤተክርስቲያን በኩል አገዛዙን በፍጥረት ሁሉ ላይ ማወጅ ማለት ነው፡፡ ስለ ክርስቲያን ሚሽን ራእይ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ክፍል - 2 ተጨማሪ ሀሳቦችን ለመከታተል ፍላጎት ካለህ እነዚህን መጻሕፍት መመልከት ይረዳህ ይሆናል: Costas, Orlando E. Christ Outside the Gate: Mission Beyond Christendom. Maryknoll, NY: Orbis Books, 1982. Curtis, Brent, and John Eldredge. The Sacred Romance: Drawing Closer to the Heart of God. Nashville: Nelson Books, 1997. Jones, E. Stanley. Is the Kingdom of God Realism? New York: Abingdon-Cokesbury, 1940. Newbigin, Lesslie. Sign of the Kingdom. Grand Rapids: Eerdmans, 1980. Yoder, John Howard. The Politics of Jesus. Grand Rapids: Eerdmans, 1972. በህይወትህና በአገልግሎትህ እውነተኛና ተግባራዊ የሆነ የአገልግሎት ዕድሎች የምታገኝበት መንገድ እንዲጠቁምህ በዚህ ትምህርት ውስጥ የተካተቱ ጭብጦችን እያሰላሰልክ መንፈስ ቅዱስን ጠይቅ፡፡ በቀጣዩ ሳምንት ልትጸልይበትና ልታሰላስለው የምትችለው አንድ ወይም ከዛ በላይ የሆነ ጭብጥ ምረጥ፡፡ ከዚያም በአንተ ትምህርቶች፣ ስብከቶችና ምስክርነቶች እነዚህን ጭብጦች እንዴት መረዳትና ተግባራዊ ማድረግ እንደምትችል ግልጽ ወደ ሆነ መንገድ ይመራህ ዘንድ ለመንፈስ ቅዱስ ምሪት ራስህን ክፍት አድርግ፡፡

2

ማጣቀሻዎች

የአገልግሎት ግንኙነቶች

Made with FlippingBook - Online catalogs