Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

9 8 /

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

ክርሰትና የምእራባውያን ሃይማኖት ነውን? እንዳለመታደል ሆኖ ብዙዎች መላውን የክርስትና ነገር እንደ ምዕራባዊ፤ ነጭ እና መካከለኛ መደብ ከሚቆጠረው አውሮፓን ያማከለ የቁጥጥር ስርአት አድርገው ይመለከቱታል፡፡ ምንም እንኳን በአሁኑ ጊዜ በጣም ጠንካራና ታላላቅ የክርሰትና እንቅስቃሴዎች በሶስተኛው አለምና የተለያየ የቆዳ ቀለም ባላቸው ክፍሎች የተያዙ ቢሆንም ለብዙዎች የክርሰትናው አለም የሃይልና የፋይናንስ ማእከሎች አሁንም ነጮች እና ምእራባውያን ናቸው፡፡ አብዘኛዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤቶች (ሴሚናሪዎች)፤ የህትመት ቤቶች፤ አብያተ ክርስትያናትና ተዛማጅ ድርጅቶች በአብዛኛው የተያዙትና የሚተዳደሩት አውሮፓዊ ወይም ሰሜን አሜሪካዊ መነሻ ባላቸው ነጮች ነው፡፡ ለብዙዎች ከውጪ ሲመለከቱት ክርስትና በመተሳሰር፣ በእኩልነት፣ በብዝሃነት በመንፈስ የሆነን ትስስር ለመካፈል እንደተሰባሰበ የእግዚአብሔር ሕዝብ መስሎ አይታይም። ይልቁንም የክርስቶስ አካልና ሙሽራ በአመለካከት አህዛብና በአካል ደግሞ ምእራባዊ ትመስላለች፡፡ እነዚህ ግንዛቤዎች በመሰረቱ ክርስትናን ምዕራባዊና ባህላዊ ሃይማኖት አድርገው ወደሚመለከቱ ማህበረሰቦች ውስጥ የመግባት አቅማቸንን እያሳጡን ነው፤ ብዙ ሃገራት ሚሽነሪዎችን እንደ ሰማዩ ዜጋ ተወካዮች ሳይሆን እንደ ምዕራባውያን ዕሴቶችና ስርዓቶች ወኪሎች ስለሚመለከቷቸው ክርስቲያን ሚሽነሪዎችን ለመቀበል ፈቃደኛ አይደሉም፡፡ በክርስትና እና በምእራቡ አለም ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ከመጣው ጥላቻ አንጻር የምእራባውያንና የነጭ በሆነ ነገር ሁሉ ላይ ጥርጣሬ በሚያድርበት መጪው ትውልድ መካከል እንደ ሚሽን መሪዎች ክርስቶስን ለሌሎች ለማድረስ ምን ማድረግ አለብን? በእግዚአብሔርና በህዝቡ መካከል ያለው መለኮታዊ ፍቅር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙ ዋና ዋና የሚሽን ጭብጦች አንዱ ነው፡፡ ይህም እግዚአብሔር ራሱ በክርስቶስ ፍቅር ለእርሱ ቤተክርስቲያን ሙሉ የሆነና ለርስቱ የሚሆንን ህዝብ ከአለም መጥራቱ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሙሽሪትና የሙሽራው እሳቤ ጎልቶ የሚታየው ከማህበራዊ አንድነት፣ ቅሬታ እና ደስታ ጋር ተያይዞ እንዲሁም እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር ያለውን ግንኙነት በመጠቀም ነው (በመኃልየ መኃልይ ላይ እንደተገለጸው)፡፡ በዋነኝነት ህዝቡ በመታደሳቸውና በመመለሳቸው ምክንያት ሙሽራው በሙሽሪት ደስ እንደሚሰኝ እንዲሁ እግዚአብሔር በህዝቡ ደስ ይሰኛል፡፡ የአዲሱ ኪዳን ተስፋ እግዚአብሔር ለአብርሃም በገባውኪዳንን በአህዛብ መጥራት ውስጥ ተካቷል፡፡ የሙሽራው ዘይቤያዊ ምስል በኢየሱስ ሰውነት ውስጥ ተፈጽሟል፡፡ ስለዚህ ደግሞ አዲሱ ሙሽራ ኢየሱስ የቤተክርስቲያን ምንጭና ህይወት ሆኗል፤ መጥምቁ ዮሐንስ ደግሞ የሙሽራው ወዳጅ፡፡ የአካሉም ምስጢር አሁን በሐዋሪያትና በነቢያት ተገልጧል፤ አህዛብ በአዲሱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን መሰረት ከአይሁድ ጋር አብረው ወራሾች መሆናቸውንና በዚህም የተነሳ የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባላት እና የክርስቶስ ሙሽራ ተደርገዋል፡፡ መለኮታዊ ፍቅር የእግዚአብሔር የህዝቡ መኖሪያ ከሆነች ከአዲሲቱ ኢየሩሳሌም በሚገለጥበት ወቅት ሙላቱን የሚያገኝ ሲሆን የእግዚአብሔርም ህዝብ እርሱን መስለው ከክርስቶስ ጋር ይለያሉ፤ ከእርሱም ጋር ለዘላለም ይነግሳሉ፡፡ ስለዚህ ሚሽን ይህንን እግዚአብሔር በእርሱ መንግስት ውስጥ ለዘላለም አብረውት የሚኖሩትን ከወገን ሁሉ የመምረጡን መልዕክት ለሌሎች ማካፈል ነው፡፡ ሚሽን እንደ ሽፍቶች ጦርነት የተሰኘው ጭብጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉ በጣም አስገራሚ የሚሽን ምሳሌዎች አንዱ ሲሆን ይህም የሚጀምረው ያህዌ የሁሉም ፈጣሪና አኗሪ በሆነበት ሉአላዊ አገዛዝ ነው፡፡ የእግዚአብሔር አገዛዝ በአመጽ ምስጢር (ማለትም በሰማይ ስፍራ የተካሄደው ሰይጣናዊ አመጽ) አማካኝነት ተቃውሞ ደርሶበታል ይህም በሰው ልጆች ላይ መፈተንና ውድቀትን

4

2

የትምህርቱን ንድፋዊ ሃሳብ በድጋሚ መጻፍ

Made with FlippingBook - Online catalogs