Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 9 7

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

ረገድ ከእነዚህ ቡድኖች መካካል ትክክል የሆነው የትኛው ነው? በጦርነት እና በግጭቶች በደቀቀው በዚህ አለም ውስጥ እምነትን ለመረዳትና ለሌሎች ለማሸጋገር ሌሎች ጭብጦችን መፈለግ አለብን ወይስ ሌሎች የጦርነትን ተፈጥሮ ምንነት እና ምን ያህል እነዚህን ምስሎች በህይወታቸው መረዳትና ተግባራዊ ማድረግ እንደጋረጠባቸው ይረዱ ዘንድ እንጠቀማቸው?

የጋብቻን ጭብጥ ግላዊነት ማላበስ? (በእውተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ)፤ ሁለት ያላገቡና ለክርስቶስ የተሰጡ ሚሽነሪ እህታማቾች ዛሬ በቤተክርስቲያን ትኩረት ስለተሰጣቸው ሁለት አይነት ጭብጦች ያላቸውን አመለካከት ሰንዝረዋል፡፡ ሁለቱም እግዚአብሔርን እንደ ንጉስ፣ ዳኛና ፈጣሪ እድርጎ መመልከት ይህን ዘመናዊውን አለም ለመገናኘት በጣም ጠቅለል ያለ እንደሆነ ያምናሉ። እንደ እነርሱ አገላለጽ የኢየሱስ እንደ ቅርብ፣ የግል አፍቃሪ ሙሽራ የተሳለው ምስል ዛሬ እግዚአብሔር ለህዝቡ ያለውን ልብ በሙላትና በጣም አውዱን በጠበቀ መንገድ ለማቅረብ አስችሏል፡፡ ሁለቱም ስለጋብቻ ተምሳሌታዊነት ያላቸውን ሃሳብ ገልጸዋል፤ አንዲያውም አላግባብና አደገኛ እሰከሚመስልበት ጥግ ድረስ እንኳ ደርሰዋል። ስለዚህ ተምሳሌታዊነት ግንዛቤው ቢኖራቸውም እንኳን እነርሱ ያላገቡ እንደመሆናቸው መጠን ለእነርሱ አግባብነት ስለማይኖረው ተቃውመውታል፡፡ ይህ ደግሞ በራሳቸው ተነሳሽነት ራሳቸውን ለክርስቶስና ለእርሱ ብቻ ለሚሰጡ እህቶች ያለማግባት የተለመደ ክርስትያናዊ ክርክር መሰረት ነው፡፡ ለነዚህ ሁለት የተወደዱ እህትማማች ሚሽነሪዎች ያለህ ምላሽ ምንድነው? ይህን ምስል ግላዊነት ማላበስ አግባብ ነው ወይስ የክርስቶስ ሙሽራ የሆኑት የእግዚአብሔር ህዝቦች እንዳይጠቀሙት እገዳ እናድርግ? ከተማዊና ከፊል ከተማዊ የመንፈሳዊነት ዜቤዎች ክርስትያናዊ ደቀመዝሙርትና ሚሽን የውጊያ ጭብጥን በተመለከተ ማንም ሰው በመንፈሳዊ ውጊያ ከተማዊና ከፊል ከተማዊ ዘይቤዎች መካከል ግልጽ ልዩነት መመልከት ይችላል፡፡ ጠቅለል ባለ አነጋገር ብልጽግናና ምቾትን ስለተለማመዱ ከፊል ከተሜዎች በመንፈሳዊ ጉዞአቸው ዋና ትኩረት የሚሰጡት ለደህንነታቸው እና ጥበቃ ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ህብረተሰብ ከአዎንታዊ ስነምግባርና ጨዋነት ጋር እንደሚወዋጋ ክፉ አጸፋዊ ሃይል ተደርጎ ይወሰዳል፤ ግቡም እነዚህ እሴቶችና የእምነት ስርአቶችን ሊያናጓቸው ከሚችሉ ሃይሎች ጠብቆ ማቆየት ነው፡፡ በሌላ አንጻር ደግሞ ከተሜያዊ የመንፈሳዊነት ዘይቤ ከአለም ጋር የሚደረግን ትግልና ግጭት እንዲሁም ይህን እድራጊዎችን አጉልተው ያሳያሉ፡፡ ውጊያ ለከበቡን ክፋቶች ሁሉ እና እነርሱን ለማጥፋትና ለመዋጥ ለሚፈልግ ሁሉ እንደ አስፈላጊ ምለሽ ይታያል፡፡ የአንድ የጎለመሰ ክርስቲያን ዝንባሌ የሚሆነው የማይቋረጥ ቅድመ ጥንቃቄና ከስልጣናት ጋር በየእለቱ የሚደረግ ትግል ነው፡፡ እነዚህ መላምቶች እሴቶችን በማስጠበቅ ላይ ሳይሆን ሰዎችን አንቀው ከሚይዙ ጨቋኝና አደገኛ መዋቅሮች ነፃ በማውጣት ላይ የተመሰረቱ ናቸው፡፡ ምንም ደህንነትና ብልጽግና ባለመጠባበቅ ትግልን፣ ተሳትፎንና ጦርነት የሚያጎሉ መንፋሳዊ ጭብጦችን ያራምዳሉ፡፡ ስለነዚህ የተለያዩ ዘይቤዎች ምን ትላለህ? በነዚህ በተለያዩ አውዶች ላይ በመመርኮዝ የመጡ የመንፈሳዊ ጉዞ ውጤቶች ናቸው ወይስ በተለያዩ መላምቶችና መንፈሳዊ ህይወት ውሰጥ በሚሰሩበት መንገድ ተጨማሪ መሰረታዊ ነገሮች አሉ?

2

2

3

Made with FlippingBook - Online catalogs