Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

9 6 /

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

• መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ውግያ፣ ግጭትና ትግል የሚያወራው ቋንቋ አንተ እንደ አማኝ ካልህ ልምምድ ጋር እንዴት አብሮ ይሄዳል? ይህን ቋንቋና ምስል እንደ ኢየሱስ ደቀመዛሙርት በህይወታችን መተግበር ያለብን እንዴት ነው? • ለጌታ ምላሽ እንዳይሰጡ የምትፈልጋቸው ሰዎች አሉን? እግዚአብሔር በየትኛውም ቦታ ሰዎችን ወደ አካሉ እና ሙሽራው እንዲሆኑ ይጠራቸዋል የሚለው ላንተ ያለው ትርጉም ምንድነው (ዮሐ6፡44)? • ራስህን እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ወታደር ትመለከታለህ? ካልሆነስ ለምን? ይህን ምሰላ የምትቀበለው ከሆነ ዛሬ ባለንበት ከባቢያዊ ሁኔታ ውስጥ በጣም የገነነውና ተቀባይነት ያገኘው ለምን ይመስልሃል? • ዛሬ በአለም ላይ የሚከሰቱ ግጭቶችን እና አለማቀፋዊ ሽብርተኝነትን በለመለከተ የጦር ምስሎችን፣ ዘይቤያዊ አነጋገሮችን እና ምልክቶችን መጠቀሙ ብልህነት ነውን? እነዚህ ምስሎች ዛሬ በሌሎች ዘንድ የተሳሳተ መረዳት እንደይፈጥሩ ልናስቀራቸው ይገባልን? • የእግዚአብሔር መንግስት በኢየሱስ በቤተክርስቲያን ውስጥ መኖር አማካኝነት መረጋገጡን እንደሚያምን ሰው እየኖርክ ነው? የራስህን አጥቢያ ቤተክርስቲያን ዛሬ በምድር ላይ እንደ “የእግዚአብሔር መንግስት ምልክትና ጣዕም” ትመለከታለህ? ለምን? • የሚከተለውን አረፍተ ነገር አጠናቅቅ - “አሁን ባለሁበት እነዚህ ጭብጦች በህይወቴ ውስጥ ህያው እንዲሆኑ ለማድረግ የምችለው አንድ ነገር ቢኖር እለርሱም...” የጦርነት ምስሎች እምነትን አያጎለብቱም ምንም እንኳን መጽሐፍ ቅዱስ በዜይቤያዊ አነጋገር፣ በፈሊጦች፣ በምሳሌያዊ አነጋጋርና በአፈታሪኮች የተትረፈረፈ ቢሆንም ብዙ ክርስቲያኖች ስለሽፍቶች ጦርነት፣ ያህዌ እንደ ተዋጊና ክርስቶስን በሰይጣን፣ በሞትና በእርግማን ላይ እንደ ድል አድራጊ በማየት ጉዳይ ላይ ፍርሃት ይሰማቸዋል፡፡ በዚህ በሽብርተኝነት፣ በግጭት እና በጦርነት በተመሰቃቀለች አለም ውስጥ ብዙ ክርሰቲያኖች እንዲህ አይነቱ ምሳሌያዊ አነጋጋር ጠቃሚ ነው ብለው አያምኑም። የወንጌል ማዕከላዊ ክፍል የሆነውን በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት በኩል ለአለም የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ፍቅር ከማሳየት ይልቅ እንዲህ አይነቱ አገላለጽ ሰዎችን ግራ ሲያጋባ ይታያል፤ እንዲያውም ለመረዳት ከባድ የሆኑ ሃሳቦችን በማምጣት እግዚአብሔር ለድሆችና ለተጠቁት ያለውን ርህራሄ የሚጋርድ ይሆናል፡፡ ሌሎች ደግሞ ስለ መንፈሳዊ ውጊያ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አጽንዖትን ችላ ማለት ወይም ትኩረት አለመስጠት ምናልባትም በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የተገለጸውን በጣም አስፈላጊ መንፈሳዊ አለም ለመረዳት ወሳኙን ጭብጥ ማጣት እንደሆነ ይሰማቸዋል፡፡ የውጊያን ምስላዊ ዋጋ የሚገነዘቡት ውጊያችን ከስጋና ከደም ጋር አለመሆኑን ያረጋግጡልናል፤ ይልቁንም ሊያጠፉን ከሚሹ ኃይላት ጋር ነው እንጂ መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ፡፡ እነዚህ ምስሎች መልካም በክፉው ላይ ስለሚኖረው የክርስቲያናዊ ተጋድሎ አለም ተጨባጭ ግንዛቤ ይሰጡናል፤ ከእነእርሱም ልንማር ይገባናል፡፡ በዛሬው አለም ውስጥ የክርስትናን እምነት ለሌሎች በማስተላለፍ

2

CASE STUDIES

1

Made with FlippingBook - Online catalogs