Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 9 5

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

³ ሚሽን እንደ ሽፍቶች ጦርነት የሚለው ማእቀፍ አንድምታ እግዚአብሔር በክርሰቶስ ኢየሱስ በኩል ዛሬ በፍጥረታት ላይ ያለውን አገዛዝ ጨምሮ፤ እግዚአብሔር በተቀባው በልጁ በኩል የክፉን ኃይልና የእርግማንን ተጽዕኖ ያሸነፈ ተዋጊ መሆኑና ሚሽን በዚህ መነጽር ሲታይ እንዴት የእግዚአብሔር መንግስት እዚህና አሁን የመሆኑ ማሳያና አዋጅ መሆኑን ያሳያል፡፡ አህዛብን ሁሉ ደቀ መዝሙር ማድረግ ማለት በናዝሬቱ በኢየሱስ ሊመጣ ያለውን የእግዚአብሔር አገዛዝ ማስፋት ማለት ነው፡፡ አሁን አብረውህ ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር በመሆን እነዚህን ወሳኝ ጭብጦች ከቅዱሳት መጻሕፍት አንጻር የምትወያይበት ጊዜ ነው፡፡ ቀጥሎ የቀረቡት ጥያቄዎች በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ስለተማርካቸው ነገሮች የራስህን አንድምታዎች ለማስቀመጥ እንዲረዱህ ታስበው የተዘጋጁ ናቸው። ስለዚህ እነዚህንና ሌሎች በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙ ተዛማጅ ጥያቄዎችን ስትዳስስ በተቻለህ መጠን ግልጽ ለመሆን ሞክር፡፡ • መለኮታዊ ፍቅር ወይም የሽፍቶች ጦርነት የሚሉትን ጭብጦች ከቅዱሳት መጻሕፍት አንጻር በጥልቀትና በግልጽ አጥንተሃቸው ከሆነ የደረስክባቸው ዋና ዋና ድምዳሜዎች ምንድ ናቸው? እነዚህን ጭብጦች “መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው” ምን እንደሆነ በተለይም በብሉይ እና በአዲስ ኪዳን መካከል ስላለው አንድነት በግልጽ እንድትረዳ ረድተውሃል? • እነዚህ ጭብጦች በከተማ ውስጥ ላለው ልምምድ ምን ያህል ጠቀሜታ አላቸው ትላለህ? የቤተሰብ መበታተን ወይም በወንድና በሴት ግንኙነት ውስጥ ታማኝነት ሰዎች የመለኮታዊ ፍቅርን ጭብጥ አስገዳጅነት እንዲረዱ ወይም እንዳይረዱ እንዴት ሊያደርግ ይችላል? • ሰዎች በጣም በሚወዷቸው ጭብጦች ላይ ብቻ ማተኮር ነው ያለብን ወይስ ምንም ቢሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦችን ነው ማስተማር ያለብን? መልስህን በጥልቀት አብራራ፡፡ • እስራኤል ከእግዚአብሔር ጋር ያላት ግንኙት በምን መልኩ እንተ ከጌታ ጋረ ካለህ ግንኙነተ ጋር ይመሳሰላል? አንተ እስራኤላውያንን ትመስላለህ ወይስ አትመስልም? እንዴት እንደሆነ አብራራ፡፡ • የእስራኤልን ታሪክ ለመምራት፣ ለትምህርትና ለመታነጽ እንደራሳችን ታሪክ እንዴት ልናስተምረው እንችላለን? (1ቆሮ10፡6-11 “እነዚህም ክፉ ነገር እንደ ተመኙ እኛ ደግሞ እንዳንመኝይህምሳሌሆነልን።ሕዝብምሊበሉሊጠጡምተቀመጡሊዘፍኑምተነሡተብሎ እንደ ተጻፈ ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንዳደረጉት ጣዖትን የምታመልኩ አትሁኑ። ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንደ ሴሰኑ በአንድ ቀንም ሁለት እልፍ ከሦስት ሺህ እንደ ወደቁ አንሴስን። ከእነርሱም አንዳንዶቹ ጌታን እንደ ተፈታተኑት በእባቦቹም እንደ ጠፉ ጌታን አንፈታተን። ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንዳንጎራጎሩ በሚያጠፋውም እንደ ጠፉ አታንጐርጕሩ። ይህም ሁሉ እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፥ እኛንም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን ሊገሥጸን ተጻፈ።”)

የተማሪው ትግበራ እና አንደምታዎች

2

Made with FlippingBook - Online catalogs