Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
9 4 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
³ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ያለው የጦርነት ዘይቤ አጭር ቅኝት በያህዌ የሁሉም ፈጣሪነት እና ደጋፊነት ይጀምራል ፡፡ በጥንት እና በሩቅ ጊዜ የክፋት ምስጢር ተከስቷል (በሰማያዊው ስፍራ የነበረው ሰይጣናዊ አመጽ)፣ ከዚያም ያስከተለው ፈተና፣ የሰው ልጆች ውድቀትና እርግማን፤ ሆኖም ግን የተጠናቀቀው በሴቲቱ ዘር አማካኝነት የእባቡ እራስ እንደሚቀጠቀጥ እግዚአበሄር በሰጠው የተስፋ ቃል ነው፡፡ በውድቀት ምክንያት ፍጥረት ሁሉ በጦርነት ላይ ነው፤ እግዚአብሔርም ከእባቡ እና አብረውት ከሚገኙት ጋር በጦርነት ላይ መሆኑን አውጇል፡፡ እግዚአብሔር ከወንዝ እና ከባህር ፣ ከፈርዖን እና ከሠራዊቱ እንዲሁም ከከነዓን አሕዛብ ጋር በተዛመደ ከክፋት ጋር በተደረገው ውጊያ ራሱን እንደ መለኮታዊ ተዋጊ አድርጎ አሳይቷል ፡፡ ³ እግዚአብሔር ከወንዝ እና ከባህር ፣ ከፈርዖን እና ከሠራዊቱ እንዲሁም ከከነዓን አሕዛብ ጋር በተዛመደ ከክፋት ጋር በተደረገው ውጊያ ራሱን እንደ መለኮታዊ ተዋጊ አድርጎ አሳይቷል ፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ ባለመታዘዛቸውና በእግዚአብሔር ላይ በማመጻቸው ምክንያት እግዚአብሔር ከገዛ ህዝቡ ጋር ተዋግቷል። የእስራኤል ነቢያት በመሲሑ አማካይነት እግዚአብሔርን በመጨረሻ ክፉን ሁሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደሚያጠፋ መለኮታዊ ተዋጊ አድርገው ስለውታል፡፡ ይህ መሲሐዊ አገዛዝ በኢየሱስ ማንነት ተከፍቷል ፤ ውልደቱ ፣ ትምህርቶቹ፣ ተአምራቱ፣ አጋንንት ማስወጣቱ፣ስራዎቹ ሞቱ እና ትንሳኤው የእግዚአብሔርን መንግሥት ያስገኘ ነው ፡፡ መንግሥቱ “መጥቷል” ደግሞም “ገና ይመጣል” ፣ በኢየሱስ መሲሐዊው ተስፋ ሲፈጽም ተፈጽሟል ነገር ግን በዳግም ምጽአቱ ይጠናቀቃል፡፡ ³ በዳዊት ሀረግ ውስጥ የመሲሁ የመምጣት ተስፋ እንዴት እንደተወከለ፣ እግዚአበሔር ለህዝቡ መንግስት የሚመልስን ንጉስ የመስጠት ፍላጎቱን፤ አህዘብን ሁሉ በጽድቅና በፍትህ ማስተዳደር መፈለጉን፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ጌታና ንጉስ እንደሆነ ምድር ሁሉ እንዲያውቅ እግዚአብሔር ያለውን ፍላጎት ያሳያል፡፡ ³ ተስፋ የተገባው የእግዚአብሔር አገዛዝ እንዴት አገዛዙን ለመመለስ ከዳዊት ስር በሚወጣው በኢየሱስ ክርሰቶስ ሰውነት በኩል እንደተከፈተ ከቅዱሳት መጻህፍት አንጻር መረዳት እንችላለን፤ በእርሱና በውልደቱ፤ ትምህርቶቹ፣ ተአምራቱ፣ አጋንንት ማስወጣቱ፣ ተግባራቱ እና ትንሳኤው አማካኝነት የእግዚአብሔር መንግስት አሁን እዚህ ናት፤ በቤተክርስቲያን ህይወት ውስጥ አለች፡፡ ³ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ፣ የሙሉ ውርስ ቃል ኪዳን በመሆኗ የመንግሥቱ ምልክት እና ቅምሻ ናት፡፡ ቤተክርሰቲያን በሰይጣን ላይ የክርስቶስ ድልና የደረሰበትን እርግማን ለማወጅና ለማሳየት የተሾመች የዛሬይቱ የእግዚአብሔር መንግሥት ምልክተ እና ቅምሻ ናት፡፡ ስለዚህም ሚሽን እግዚአብሔር በአሁኑ ጊዜ በፍጥረታት ሁሉ ላይ በኢየሱስ ክርስቶስ እና እንዲሁም በወኪሉ በቤተክርስቲያኑ በኩል ስላለው አገዛዝ እያረጋገጠ መሆኑን ማወጅ ነው፡፡
2
Made with FlippingBook - Online catalogs