Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
/ 9 3
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
³ የእስራኤል እንደ እግዚአብሔር ሙሽራ ጽንሰ ሃሳብ የሚጀምረው እግዚአብሔር በሚያሳዝን እና በቸልተኛ ማንነቷ ከእስራኤል ጋር ካለው ግንኙነት ነው ፣ ወደ እግዚአብሔር ፀጋ ምርጫ ፣ የፍቅር ግንኙነት እና ጋብቻ ፣ በጣዖት አምልኮ እና በፍትሕ ማጓደል የእስራኤል ማመንዘር፣ በእስራኤል (በሰሜናዊው መንግሥት) እና በይሁዳ (በደቡባዊው መንግሥት) ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ እና ግዞት እስከመምጣት ድረስ ይሄዳል፡፡ ³ በቂሮስ ትዕዛዝ መሰረት በእዝራ፣ ዘሩባቤልና ነህምያ አማካኝነት የቅሬታዎቹ ወደ ምድራቸው ዳግም ተመልሰዋል ፤ ነገር ግን በመታዘዛቸውና ከማንነታቸው የተነሳ ሳይሆን እርሱ ራሱ ህጉን በልባቸው ስለጻፈውና አዲስን መንፈስ ስለሰጣቸው ነው፡፡ በዋነኝነት ሙሽራ በሙሽራይቱ ደስ እንደሚሰኝ እንዲሁ ህዝቡ ተሃድሶ ሆኖላቸው እግዚአብሔርም በልጁ ደስ መሰኘቱ ነው፡፡ ³ የአዲሱ ኪዳን ተስፋ እግዚአብሔር ለአብርሃም በገባው ኪዳን በአህዛብ መጠራት ውስጥ ተካቷል፤ የሙሽራው ዘይቤያዊ ምስል በኢየሱስ ሰውነት ውስጥ ተፈጽሟል፡፡ ስለዚህ ደግሞ አዲሱ ሙሽራ ኢየሱስ የቤተክርስቲያን ምንጭና ህይወት ሆኗል፤ መጥምቁ ዮሐንስ ደግሞ የሙሽራው ወዳጅ ነው፡፡ የአካሉም ምስጢር አሁን በሐዋርያት እና በነቢያት ተገልጧል፡፡ አህዛብ በአዲሱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን መሰረት ከአይሁድ ጋር አብረው ወራሾች መሆናቸውንና በዚህም የተነሳ የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባላት እና የክርስቶስ ሙሽራ ተደርገዋል፡፡ ³ አህዛብ ከአይሁድ ጋር አብረው ወራሾች ሆነዋል በዚህም ምክንያት ወደ አዲሱ የእግዚአብሔር ቤተሰብነትና ወደ ክርስቶስ ሙሽራነት ስለመግባት የእግዚአብሔር ሃሳብ ምስጢር በሐዋርያነትና በነቢያት ተገልጧል፡፡ ³ እንደ ክርስቶስ ሙሽራ ከአህዛብ መካተት ጋር የተያያዙ ዋና ዋና የዶክትሪን ጉዳዮችን የተደረገላቸውን የእምነት ግብዣ ጨምሮ፣ በኢየሩሳሌም ጉባኤ ስለተሰጠው መፍትሄ፣ እነርሱን በኪዳኑ ውስጥ ስለማካተት የኢየሱስ ደም ስላለው ኃይል፣ እንዴት ሐዋርያዊው አገልግሎት የእግዚአብሔርን ህዝብ ለክርስቶስ ነውር እነደሌለባት ሙሽራ እያዘጋጃት ነው። ³ $$ ይህ መለኮታዊ ፍቅር የእግዚአብሔር የህዝቡ መኖሪያ ከሆነች ከአዲሲቱ ኢየሩሳሌም በሚገለጥበት ወቅት ሙላቱን የሚያገኝ ሲሆን የእግዚአብሔርም ህዝብ እሱን መስለው ከክርስቶስ ጋር ይለያሉ፤ ከእርሱም ጋር ለዘላለም ይነግሳሉ፡፡ ³ እግዚአብሔር ከአህዛብ መካከል ለራሱ ህዝብን ለይቶ ማውጣቱ የመለኮታዊውን ፍቅር አንድምታ ያሳያል፤ ይህ መጥራት አይሁድንና አህዛብን ሁሉ ያካተተ ነው፡፡ ስለዚህ ሚሽን ማለት እግዚአበሔር ከእርሱ ጋር ለዘላለም የሚኖሩትን የእርሱን መንግስት አባላት ከአይሁድና ከአህዛብ መካከል መጥራቱን መመስከር ነው፡፡ ³ ሚሽን እንደ ሽፍቶች ጦርነት በሚለው ማዕቀፍ ውስጥ ምናልባትም አስደናቂ የሆነውን የሚሽን ምስል ከቅዱሳት መጽሐፍት መረዳት ይቻላል፤ ይህ ማዕቀፍ በጌታ በኢየሱስ አማካኝነት የእግዚአብሔርን መንግስት አገዛዝ ስለማወጅ ያትታል።
2
Made with FlippingBook - Online catalogs