Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
9 2 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
የተስፋው አምላክ የውጊያም አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን እንደ መለኮታዊ ተዋጊ ሲገለጥ ብዙውን ጊዜ ህዝቡን ከጠላቶቻቸው ሊያድናቸው ሲመጣ ነው፡፡ ይህም ሲሆን የነበረው ቀይ ባህርን ከመሻገራቸው አንስቶ እስከ ኋለኛው የእስራኤል ታሪክ ድረስ ነው፡፡ እግዚአብሔር ራሱን እንደ ንጉስ በቃልኪዳን ስምምነት ውስጥ ከገለጠ በኋላ በጠላቶቻቻው ከሚደርስባቸው አደገኛ ማስፈራራት ህዝቡን ለመጠበቅ ቃል ገብቶላቸዋል። ይህን በቃልኪዳኑ መከበር ምክንያት በሚፈስሰው በረከት ውስጥ ማየት እንችላለን። ንጉሱ እግዚአብሔር እስራኤል የምትታዘዝ ከሆነ በዘዳግም 28:7 ላይ ቃል ገብቶላቸዋል። እግዚአብሔርም በላይህ የሚቆሙትን ጠላቶችህን በፊትህ የተመቱ ያደርጋቸዋል፤ በአንድ መንገድ ይመጡብሃል፥ በሰባትም መንገድ ከፊትህ ይሸሻሉ፡፡ ይህን በተለያ ዘዴዎችና የማሸነፊያ መንገዶች በእራኤል ታሪክ ውስጥ ሲያደርገው ቆይቷል፡፡ እግዚአበሄር ብዙውን ጊዜ የራሱን ፍጥረታት የሆኑትን የተፈጥሪ ሀይሎች እንደጦር መሳሪያዎቹ ሲጠቀምባቸው ይታያል፡፡ ቀይ ባህርን በተሻገሩ ጊዜ እስራኤል ሲድንና ግብጽ ሲፈረድበት እስራኤል በደረቅ መሬት እንዲሻገር እግዚአብሔር የተጠቀመው ንፋስን ነበር (ዘፀ 14 እና 14)፡፡ በኋላም ኢያሱ ከደቡብ ከነአናውያን ነገስታት ጥምረት ጋር ሲዋጋ ጦርነቱ በሚያልቅበት ቀን ብርሀን እንዲሆን ፀሀይን በማቆም ጠላትን በመግደል ትላልቅ ቋጥኞችን በመጠቀም እግዚአብሔር ተፈጥሮን እንደጦር መሳሪያ ተጠቅሞ አሳይቷል (ኢያሱ 10፡1-5)፡፡ በሌሎችም አጋጣሚዎች እግዚአብሔር የእስራኤልን ጠላቶች ለመዋጋት የሰማይ ሰራዊቱን ይጠቀማል፡፡ ይህ ትምህርት ሚሽንን በተመለከተ ብቻ ሳይሆን መላውን ቅዱሳት መጻሕፍት አስመልክቶ በጣም ጠቃሚ ስለሆኑ ሁለት ጭብጦች ይዳስሳል፡፡ ሚሽን እንደ ዘመናት ፍቅር እና ሚሽን እንደ ሽፍቶች ጦርነት የሚሉት ጭብጦች ስለመሲሁ ስራና ስለ ቤተክርስቲያን የሚኖረንን መረዳት ከመፍጠር አንጻር እነዚህ ሃቦች በጣም ጠቃሚ ሚና ይጫወታሉ፡፡ እነዚህን ጭብጦች መጨበጥ የሚሽንን ትርጉም ብቻ ሳይሆን የቤተክርስቲያንን ተፈጥሮና ስራ በደንብ ለመረዳት ይረዳል፡፡ ስለዚህ እነዚህን ጽንሰ ሀሳቦች በጥንቃቄ በመቃኘት ከቅዱሳት መጻሕፍትጋር በማዛመድ አስቀምጥ፡፡ ³ እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር የገባበት መለኮታዊ ፍቅር ለመጽሐፍ ቅዱሳዊው ሚሽን እንደ አንዱ ዋነኛ ጭብጥ ነው፤ ይህም እግዚአብሔር ለእርሱ የተለየን ህዝብና ከዚያም በክርስቶስ ኢየሱስ ህያው የሆነችውን ቤተክርስቲያን ከአህዛብ መካከል ማውጣቱ ነው፡፡ ³ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሙሽራይቱና የሙሽራውን ሃሳብ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ካለው የደስታና የፈንጠዝያ ሀሳብ ጋር የተዛመደ ነው፤ እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር ስላለው ግንኙነት መሰረታዊ ምስል (በመኃልየ መኃልይ እንደተመከተው) እና ከእስራኤል አሳዛኝ ጅማሮ አንስቶ ባለመታመንዋ እስከመጣባት ፍርድና ስደት ድረስ እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር ያለው ግንኙነት የጎለበተበትን መንገድ የሚያሳይ ነው፡፡ ~ Leland Ryken. The Dictionary of Biblical Imagery. (electronic ed.) Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 2000. p. 211.
2
CONNECTION
የቁልፍ ጽንሰ ሃሳቦች ማጠቃለያ
Made with FlippingBook - Online catalogs