Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 9 1

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

ነው? ይህ ጭብጥ በናዝሬቱ በኢየሱስ ሰውነት በኩል የእግዚአብሔርን መንግስት ማቋቋም እና ማወጅ ከሚለው ሀሳብ ጋር እንዴት ይዛመዳል? አብራራ። 2. እግዚአብሔር በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ መለኮታዊ ተዋጊ የተገለጸበትን ጭብጥ በአጭሩ አሳይ፤ ይህ ጭብጥ ስለ “አመጻ ምስጢር” ምን ያረጋግጣል? በመንግስተ ሰማያትስ የእግዚአብሔርን አገዛዝ በመቃወም ምክንያት የተከሰተው ምንድን ነው? 3. የእግዚአብሔርን ሚና እና ማንነት እንደ ተዋጊ ለመረዳት ፕሮቶኢቫንጌሊየም ለምን በጣም አስፈላጊ ሆነ (ዘፍ 3፡15)? የአመጽ ምስጢር፣ ውድቀትና እርግማን እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር በተለይም ከሰው ልጆች ጋር ያለውን ግንኙነት እንዴት አድርጎ ቀየረ? 4. በብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር ከክፉው ጋር የገባበት ግጭት የተመሰለው እንዴት ነበር? እግዚአብሔር ከፈርኦንና ከከነአን ሰዎች ጋር የነበረው ግጭት እግዚአብሔርን እንደ መለኮታዊ ተዋጊ ለመረዳት እንዴት ያግዘናል? ደግሞስ እግዚአብሔር ከገዛ ህዝቡ ጋር ግጭት ውስጥ የገባው ለምንድን ነው? 5. የእስራኤል ነብያት የመሲሑን መምጣት የእግዚአብሔር መለኮታዊ ተዋጊነት ቅጥያ እንደሆነ አድርገው የተመለከቱት እንዴት ነው? ይህ መሲህ በመጨረሻ እንዴት ያጠፋቸዋል? 6. የእግዚአብሔርን አገዛዝ የሚመልሰው ከዳዊት የዘር ሀረግ ወራሽ የሆነው የመሲሁ ኢየሱስ ተስፋ የተከፈተባቸውን መንገዶች በአጭሩ አስቀምጥ፡፡ ውልደቱ ፣ ትምህርቶቹ፣ ተዓምራቱ፣ አጋንንት ማስወጣቱ፣ ስራዎቹ፣ ሞቱ እና ትንሳኤው በቤተክርሰቲያን ህይወት ውስጥ ተስፋ የተሰጠው የእግዚአብሔር መንግስት አሁን እንደደረሰ እንዴት ያሳያል? 7. የእግዚአብሔር መንግስት “አሁን መጥታለች” ግን ደግሞ “ገና አልተጠናቀቀም” ማለት የሚቻልበትን ሁኔታ አብራራ፤ በዚህ ዘመን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስራ ለመወያየት ይህን ልዩነት ከግምት ማስገባት ለምን አስፈላጊ ሆነ? 8. ዛሬ በዚህ ዘመን ያለችው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የመንግስቱ ምልክትና ቅምሻ ናት የምንለው በምን አግባብ ነው? በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ በእርግጥ የእግዚአብሔር መንግስት በኢየሱስ በኩል መምጣቱን የሚያረጋግጠው በምን መልኩ ነው? አሁን ቤተክርስቲያን ክርስቶስን በመወከል ለመንግስቱ መስፋት ስልጣን የተሰጣት ምን ታደርግ ዘንድ ነው? 9. ሚሽን እንደ ሽፍቶች ጦርነት የሚለው ጭብጥ ውስጥ ዋና አንድምታዎች ምንድን ናቸው? በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ዛሬ በፍጥረታት ሁሉ ላይ ያለውን የእግዚአብሔርን አገዛዝ ማረጋገጥ በተመለከተ ሚሲዮናውያን ምን ማድረግ አለባቸው? በጠፉትስ ዘንድ ስራቸውንና አገልግሎታቸውን መወከል ያለባቸው እንዴት ነው? 10. ቀጥሎ የቀረበውን የራይከንን ጥቅስ አንብብ፡፡ እነዚህን የተለያዩ ስለ እግዚአብሔር የተነሱ ጭብጦች ከመለያየት ይልቅ እርስ በእርሳቸው የተዛመዱ መሆናቸውን ማየቱ ለምን አስፈላጊ ሆነ? እነዚህን ምስሎች እግዚአብሔር ማን እንደሆነና በዚህ አለም ውስጥ ስለሚሰራው ስራ (በእርግጥ እነዚህ ዛሬ ሚሽንን ለማከናወን መሰረቶች ናቸው) ለመረዳት እንዲረዱን ራይከን በምን መልኩ ሊያግዘን ይችላል?

2

Made with FlippingBook - Online catalogs