God the Father, Amharic Mentor Guide

2 2 /

እግዚአብሔር አብ

ለ. በኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት (1) ዮሐንስ 1፡14

(2) ዮሐንስ 1፡18

(3) ሉቃስ 10፡22

3. ልዩ መገለጥ አናሎጂያዊ ነው። (እግዚአብሔር እርሱ ማን እንደሆነና ከእሱ ጋር ያለን ግንኙነት ምን እንደሚመስል ለማሳየት ምሳሌዎችን ይጠቀማል።)

1

ሀ. ተመሳሳይነት = አንድን ነገር ከሌላው ነገር ጋር በማነፃፀር እንድንረዳ ይጋብዘናል፡- ሀ ከ ለ ጋር ተመሳሳይ እንደሆነው፣ እንዲሁ ሐ ደግሞ ከ መ ጋር ተመሳሳይ ነው። (1) ዮሐንስ 10፡9

(2) ዮሐንስ 10፡14-15

ለ. እግዚአብሔር ለማነጻጸር አንዳንድ ክፍሎችን ይመርጣል፣ እንድንገነዘብም ግንኙነታቸውን ይጠቁመናል።

ሐ. እርሱ በፅንሰ-ሀሳቦች ወይም ሃሳቦች ብቻ ሳይሆን (ለምሳሌ፣ ኢየሱስ የይሁዳ አንበሳ ነው) ከመላው ሰው ጋር ይገናኛል።

4. ልዩ መገለጥ ተጨባጭ ነው።

ሀ. በታሪካዊ ክስተቶች (ለምሳሌ፣ የአብርሃም ጥሪ)፣ ዘፍ. 12.1-3

ለ. በመለኮታዊ ንግግር፣ ለምሳሌ፣ ዕብ. 1.1-2

ሐ. በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ፣ 1ኛ ዮሐንስ 1፡1-3

Made with FlippingBook - Online magazine maker