God the Father, Amharic Mentor Guide
/ 2 3
እግዚአብሔር አብ
መደምደሚያ
» እንድናውቀው ካስፈለገ እግዚአብሔር ራሱን ሊገልጥልን ይገባል።
» እግዚአብሔር ራሱን በሁለት ልዩ ዘይቤዎች ወይም መንገዶች ይገልጥልናል፡ በአጠቃላይ መገለጥ፣ እግዚአብሔር በሁሉም ስፍራ ላሉ ሰዎች ሁሉ ራሱን ይገልጣል፣ በልዩ መገለጥ ደግሞ እግዚአብሔር ራሱን ለተወሰኑ ሰዎች በተወሰነ ጊዜና ቦታ ይገልጣል።
እባክህ በእነዚህና በሌሎችም በዚህ ቪዲዮ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች በቂ ጊዜ ወስደህ ምላሽ ለመስጠት ሞክር፡፡ እግዚአብሔር ራሱን ለእኛ የመግለጡ አስፈላጊነት እና የአጠቃላይ እና የልዩ መገለጥ ተፈጥሮ በእግዚአብሔር አብ ጥናታችን ውስጥ ማዕከላዊ ጉዳዮች ናቸው። መልሶችህ ግልጽ እና አጭር ይሁኑ፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ በቅዱሳት መጻሕፍት አስደግፍ! 1. “ፕሮሌጎሜና” የሚለው ቃል ምን ማለት ነው? ስለ እግዚአብሔር ማንነት እና ሥራ መደበኛ ጥናት ውስጥ ከመግባትህ በፊት በመጀመሪያ ግምቶችህን ግልጽ ማድረግ አስፈለጊ የሆነው ለምንድነው? 2. አንድ ሰው እግዚአብሔርን በራሱ መንገድ እና በብርታቱ ማወቅ የማይችለው ለምንድን ነው? 3. በአምላክ ጥናት ውስጥ ምክንያታዊነት እና ምርምር ምን ሚና አላቸው? አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ሙሉ እውቀት እንዲኖረው ለመርዳት በራሳቸው በቂ የማይሆኑት ለምንድነው? 4. እግዚአብሔርን እንድናውቅ ከመርዳት አንጻር የመንፈስ ቅዱስ ድርሻ ምንድን ነው? 5. አጠቃላይ መገለጥ ምንድን ነው? እግዚአብሔር በሁሉም ስፍራ ለሰው ልጆች ሁሉ ራሱን የገለጠው በምን አይነት ልዩ ልዩ መንገዶች ነው? ይህ አይነቱ የእግዚአብሔር እውቀት ለመዳን በቂ ነው? መልስህን አስረዳ። 6. ልዩ መገለጥ ምንድን ነው? የልዩ መገለጥ ባህሪያት ምንድናቸው? እግዚአብሔር ራሱን ለሰው ልጆች የገለጠበት ከሁሉ የበለጠ ግልጽ እና ብርቱው መንገድ የትኛው ነው? 7. በአጠቃላይም ይሁን በልዩ መገለጥ እግዚአብሔር ራሱን ለእኛ ሊገልጥልን ለምን አስፈለገ? ከአምላክ ጥናት ረገድ ምንጊዜም አመለካከታችን ምን መሆን አለበት?
መሸጋገሪያ 1
1
የተማሪው ጥያቄዎች እና ምላሾች
ገጽ 256 8
Made with FlippingBook - Online magazine maker