God the Father, Amharic Mentor Guide

2 4 /

እግዚአብሔር አብ

ፕሮሌጎሜና፡ ትምህርተ እግዚአብሔር እና የመንግሥቱ መስፋት ሴግመንት 2፡ እግዚአብሔር ሊታወቅ ይችላልን?

ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ

ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ አምላክ እንደመሆኑ፣ አብ በአጽናፈ ዓለም ውስጥ በሁሉም ቦታ የሚገኝ እና የሚሰራ ነው (ማለትም፣ እግዚአብሔር ህልው ነው)፣ እንዲሁም ከነገሮች እና ከፍጥረታት ሁሉ በላይ (ማለትም፣ እግዚአብሔር ምጡቅ ነው)። በሥነ-መለኮት ውስጥ፣ የእግዚአብሔርን ባህሪያት፣ የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ ታላቅነት እና መልካምነት የሚገልጹትን ባህሪያት እናጠናለን። የዚህ እግዚአብሔር ሊታወቅ ይችላልን? የተሰኘ ሴግመንት ዓላማ፣ የሚከተሉትን ማየት እንድትችልል ለማስቻል ነው፡- • እግዚአብሔር የሁሉም ነገር ፈጣሪ እና አድራጊ እንደመሆኑ መጠን ከአጽናፈ ዓለሙ ጋር ልዩ የሆነ ዝምድና አለው ይህም በሁሉንቻይነቱ እና በምጡቅነቱ ሊገለጽ ይችላል። • የእግዚአብሔር ህልውና በፍጥረቱ ሁሉ መካከል ያለውን ያልተቋረጠ ንቁ ተሳትፎን ያመለክታል። • በሌላ በኩል፣ የእግዚአብሔር ልዕልና ማለቂያ የሌለውን የእግዚአብሔርን ተፈጥሮ እና ታውቆ የማይደረስበት መሆኑን ያመለክታል። • የእግዚአብሔር ባሕርያት የአምላከ ስላሴን፣ የአብ፣ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ባህሪያትን ያመለክታሉ። • የእግዚአብሔርን ባህሪያት ከእግዚአብሔር ታላቅነት እና ቸርነት አንጻር ልንመድባቸው እንችላለን። • የእግዚአብሔር የታላቅነቱ ባህሪያት መንፈሳዊነት፣ ህይወት፣ ስብዕና፣ ማለቂያ የለሽነትል እና ቋሚነት ናቸው። • የእግዚአብሔር የመልካምነት ባህሪያት ደግሞ የሞራል ንጽህና፣ ጽኑ አቋም እና ፍቅርን ያካትታሉ።

የሴግመንት 2 ማጠቃለያ

ገጽ 256  9

1

Made with FlippingBook - Online magazine maker