The Kingdom of God, Amharic Mentor Guide
/ 2 1
የ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር መ ን ግ ስ ት
ማጠቃለያ
ገጽ 282 11
» አምላከ ስላሴ በሁሉ ላይ የሚገዛ ከሁሉ በላይ የሆነ ጌታ ነው።
» ንግሥናውን በሰማያት ባለው በሰይጣን አመጽ፣ እና በምድር ላይ በነበሩት የመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስት አመጽና አለመታዘዝ ተፈትኗል።
እነዚህን እና ሌሎች ቪዲዮው ያነሳቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ የቻልከውን ያህል ጊዜ ውሰድ። መልሶችህ ግልጽ እና አጭር ይሁኑ፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ በቅዱሳት መጻሕፍት አስደግፍ! 1. መጽሐፍ ቅዱስ በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ያለውን ሁሉን ቻይ አምላክ ስልጣንና አገዛዝ የሚገልጸው እንዴት ነው? “ሉዓላዊነት” የሚለው ቃል ምን ማለት ነው? 2. የሥነ መለኮት ሊቃውንት የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር “በራሱ የሚኖር” ነው ሲሉ ምን ማለታቸው ነው? 3. እግዚአብሔር ዓለምን እንደፈጠረ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ከሚናገረው ሐሳብ ጋር በሚስማማ መንገድ ማስተማር አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? 4. በቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት፣ የእግዚአብሔር ሉዓላዊነት እና አገዛዝ በዓለም እና በአጽናፈ ዓለም ውስጥ እስከ ምን ድረስ ይዘልቃል? መልስህን አስረዳ። 5. በአጽናፈ ዓለምውስጥ ያለውን “የሰይጣን ዓመፅ መሠረታዊ ሥርዓት” እንዴት ትገልጸዋለህ? 6. ቪዲዮው “የሰይጣናዊ ሥራ ዋነኛ መንስዔ” ምን እንደሆነ የሚገልጸው እንዴት ነው? በዚህ መግለጫ ትስማማለህ? ለምን? 7. የሰይጣን ዓመፅ በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ያሉትን ሌሎች ሁለት የሕይወት ዘርፎች ይነካል። ምንድን ናቸው? ያስከተለውስ ውጤት ምንድነው? 8. የሰው ልጆችን ውድቀት እንዴት ልንገልጽ እንችላለን - በሁሉን ቻይ አምላክ አስተዳደርና አገዛዝ ላይ ለማመፅ ውሳኔ ምን ምክንያቶች ልንሰጥ እንችላለን? 9. ሰይጣን በሔዋን ላይ ያቀረበው ፈተና ሐዋርያው ዮሐንስ በዓለም ላይ ያለውን ክፋት ከገለጸበት (ለምሳሌ 1 ዮሐንስ 2፡16) ጋር እንዴት ይመሳሰላል? 10. በሰማያት ውስጥ የሰይጣን አመጽ እና አዳምና ሔዋን በገነት አለመታዘዛቸው ያስከተለው አሳዛኝ ውጤት ምን ነበር? የነገረ መለኮት ሊቃውንት ስለዚህ አስከፊ ክስተት ምን ይላሉ?
መሸጋገሪያ 1
1
የተማሪ ጥያቄዎች እና ምላሾች
ገጽ 282 12
Made with FlippingBook Digital Publishing Software