The Kingdom of God, Amharic Mentor Guide

/ 4 7

የ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር መ ን ግ ስ ት

6. እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር በገባውቃል ኪዳን ውስጥ የተካተቱት ልዩ ተስፋዎች ምንድን ናቸው? የአብርሃም ቃል ኪዳን በፕሮቶ ኢቫንጀሊዝም ውስጥ ከገባው የእግዚአብሔር ተስፋ ጋር እንዴት ይዛመዳል? 7. እግዚአብሔር የአብርሃምን ቃል ኪዳን የሚያድሰው በየትኛው የእስራኤል ነገድ ነው? መሲሑ ከዚያ ነገድ እንደሚመጣ ያወቅንበት መንገድስ ምንድን ነው? 8. በዘፀአት 19 መሠረት እግዚአብሔር ለሕዝቡ ለእስራኤል የነበረው የመጀመሪያ ዓላማ ምን ነበር? እስራኤላውያን ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ በመወከል ለአሕዛብ ብርሃን በመሆን ረገድ እንዴት ነበሩ? 9. የናዝሬቱ ኢየሱስ ከአብርሃም ዘር ጋር ያለው ግንኙነት ምንድን ነው? የናዝሬቱ ኢየሱስ በፕሮቶ ኢቫንጀሊዝም ውስጥ ከተጠቀሰችው ሴት ዘር ጋር ያለው ዝምድና ምንድን ነው?

2

የእግዚአብሔር መንግሥት ተመረቀ ክፍል 2

ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ

እግዚአብሔር ለአብርሃም የተስፋውን ዘር እንደሚያመጣ በገባው የቃል ኪዳን ተስፋ መሰረት በውድቀት ምክንያት የመጣውን አለመታዘዝ እና አመጽን ለማጥፋት ከመጀመሪያው ጀምሮ እየሰራ ነበር። ይህ ተስፋ በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ሕዝብ፣ በይሁዳ እና በዳዊት በኩል ሊገኝ ይችላል። ምንም እንኳን የእግዚአብሔር ሕዝቦች በብዙ ውድቀትና የጣዖት አምልኮ ውስጥ ቢገኙም በእነርሱ አማካኝነት የመንግሥቱን መገኘት የሚወክለውና የተቀባው የናዝሬቱ ኢየሱስ ኢየሱስ ተገኝቷል። በመጨረሻው ኃይል እና ሥልጣን፣ የእግዚአብሔር መንግሥት በኢየሱስ ሥጋ መገለጥ፣ ሞት፣ ትንሣኤ እና ዕርገት ታይቷል። ለዚህ የእግዚአብሔር መንግሥት ተመረቀ ለተሰኘው ሁለተኛ ክፍል ዓላማችን የሚከተሉትን እንድታይ ማስቻል ነው፡- • በናዝሬቱ ኢየሱስ ማንነት እና ስራ፣ የእግዚአብሔር መንግስት ግዛት በክብር ተመርቆ (በሙላት) በአለም ውስጥ እውን ሆኗል። • ኢየሱስ በመከራው፣ በሞቱ እና በመቀበሩ እንደ ክርስቶስ ቪክተም ለእግዚአብሔር አገዛዝ ምስክርነት እና ህይወትን ሰጥቷል። • ኢየሱስ በክብር ትንሣኤውና ዕርገቱ እንደ ክርስቶስ ቪክቶር የመንግሥቱ ምሥረታና መገለጡ የማያከራክር ማረጋገጫ ሰጥቷል።

የክፍል 2 ማጠቃለያ

ገጽ 293  9

Made with FlippingBook Digital Publishing Software