The Kingdom of God, Amharic Mentor Guide

/ 5 9

የ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር መ ን ግ ስ ት

ከውድቀት ጀምሮ፣ እግዚአብሔር መንግስቱን ወደዚህ ዓለም በማምጣት የውድቀትን ውጤት ለማጥፋት እና ለመሻር ይፈልጋል። ቅድመ-ዝንባሌውን በጠላቶቹ ላይ እንደ ተዋጊ በመውሰድ አገዛዙን በተጨባጭ ማሳየት ጀመረ። ለአብርሃም በገባው የቃል ኪዳን ተስፋ፣ የእባቡን ራስ የሚቀጠቀጥ እና የምድርን አህዛብ ሁሉ የሚባርክ ዘርን ወደ አለም ለማምጣት ወሰነ። የተስፋው ቃል በአባቶች፣ በእስራኤል፣ ለይሁዳ ነገድ እና ለዳዊት ቤተሰብ ታደሰ። በመጨረሻም፣ በናዝሬቱ ኢየሱስ ማንነት እና ሥራ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት አገዛዝ በዚህ ዓለም በመጨረሻው ደረጃ ተመርቋል። እንደ ክርስቶስ ቪክተም፣ ከዲያብሎስ፣ ከኃጢአት እና ከሞት ኃይል አዳነን፣ ደግሞም እንደ ክርስቶስ ቪክቶር፣ ከመቃብር ተነስቶ የሁሉም ጌታ ሆኖ ወደ ሰማይ አርጓል። እስካሁን መንግሥቱ ሙሉ በሙሉ ባይፈጸምም፣ የመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነት አማካኝነት ነው። እግዚአብሔር እንደ መለኮታዊ ተዋጊ ስለሚለው ሃሳብ ተጨማሪ ሀሳቦችን ለመከታተል ፍላጎት ካለህ እነዚህን መጻሕፍት መመልከት ይረዳህ ይሆናል Dawson, John. Taking Our Cities for God. 2nd. ed. Altamonte Springs: Charisma House, 2001. Lind, Millard. Yahweh is a Warrior: The Theology of Warfare in Ancient Israel. Scottsdale: Herald Press, 1980. የኢየሱስ ድል ትስስር ለእያንዳንዱ የአገልግሎታችን ክፍል ትልቅ ጠቀሜታ አለው። ይህንን ከፍተኛ ሥነ-መለኮት በእውነተኛ የተግባር አገልግሎት ግንኙነት ለመመስከር የምንሞክርበት ጊዜ አሁን ነው፣ በዚህ በሚቀጥለው ሳምንትም ልታስብበት እና ልትጸልይበት ይገባል። በተለይ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት እና የዛሬውን ተግዳሮት በሚመለከት ምን ይመክራል? የእግዚአብሔር መንግሥት እውነት እንዴት እንደሚመረቅ እና ስለ ራስህ ህይወት እና አገልግሎት ስታስብ ምን አይነት ሁኔታ ወደ አእምሮህ ይመጣል? በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ለራስህ በጌታ ፊት ለማሰላሰል ጊዜ ስጥ፣ እርሱም ምን እንደሆነና ልታደርገው የሚገባህን ይገልጥልሃል። ከዚህ ትምህርት አስተምህሮ አንጻር ተገቢው የጸሎት ዓይነት አምልኮ፣ ውዳሴና እና ምስጋና ነው። እግዚአብሔር እኛን ለመርዳት፣ ጠላቶቻችንን ለመዋጋት፣ የውድቀትን ውጤት ለመሻር፣ ለእኛ ሲል ዲያብሎስን እና ሞትን የተጋፈጠውን ልጁን እንዲልክ የሥላሴን ቁርጠኝነት ለማየት - ይህ ታላቅ ፍቅር በውስጣችን የምስጋናን መንፈስ ሊፈጥር ይገባዋል: አስደናቂ የሆነን የምስጋና ፍሰት። በተዳከምንበት ጊዜ እግዚአብሔር አልተወንም፣ ነገር ግን ያለውን ሁሉ ለኛ ሰጥቶናል። ኢየሱስ በጠላቶቻችን ላይ ያስመዘገበውን ድል ትክክለኛ በሆነ መንገድ ማሳየት እና እግዚአብሔር በጥቂቷ እምነታችን ሲሠራ መመልከት ምን ማለት እንደሆነ የምናሳይባቸው መንገዶች መፈለግ አለብን። ምናልባት እነዚህ መንገዶች በቤተሰብህ ወይም በቤተክርስቲያንህ፣ በስራ ቦታህ ወይም በአከባቢህ ለሰዎች እግዚአብሔርን የምናነሳቸው ሊሆኑ ይችላሉ።

የትምህርቱን ንድፋዊ ሃሳብ በድጋሚ መጻፍ

ማጣቀሻዎች

2

የአገልግሎት ግንኙነቶች

ምክር እና ጸሎት

ገጽ 296  15

Made with FlippingBook Digital Publishing Software