The Kingdom of God, Amharic Mentor Guide
6 0 /
የ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር መ ን ግ ስ ት
ምደባዎች
ሉቃ 11፡15-20
የቃል ጥናት ትውስታ
ለክፍል ለመዘጋጀት እባክህ www.tumi.org/booksን ጎብኝ የሚቀጥለውን ሳምንት የንባብ ስራ ለማግኘት ወይም አስተማሪህን ጠይቅ።
የንባብ ምደባ
እባክህ ከላይ ያሉትን የንባብ ስራዎች በጥንቃቄ አንብበህ እንደባለፈው ሳምንት አጭር ማጠቃለያ ጻፍላቸው። እንዲሁም፣ ስለ አገልግሎትህ ፕሮጀክት ባህሪ ማሰብ የምትጀምርበት ጊዜ አሁን ነው፣ በተጨማሪም ለትርጓሜ ፕሮጀክትህ የትኛውን የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍል እንደምትመርጥ ለመወሰን ጊዜው አሁን ነው። አገልግሎትህን ወይም የትርጓሜ ፕሮጀክትህን ለመወሰን አትዘግይ። ለመምረጥ በዘገየህ መጠን ለመዘጋጀት የበለጠ ጊዜ ያስፈልግሃል! እስካሁን በዚህ የመንግሥቱ ሞጁል ውስጥ በውድቀት እና በውጤቶቹ ላይ አተኩረናል፣ እናም በዚህ ትምህርት፣ እግዚአብሔር በልጁ በኩል ግዛቱን ወደ ልዕለአለሙ በመመለስ የውድቀትን ውጤት ለማጥፋት ባደረገው ውሳኔ ላይ ተነጋግረናል። እግዚአብሔር አብ በጣም እንደሚወደንና እግዚአብሔር ኃይለኛ ተዋጊ የሆነውን ልጁን እኛን ከማረኩንና ሕይወታችንን አስቸጋሪና ከባድ ካደረጉት ኃይላትና ስልጣናት ጋር ይዋጋ ዘንድ ወደ ምድር እንደላከልን ማወቁ ምንኛ የሚያስደስት ነው! በሚቀጥለው ትምህርታችን ኢየሱስ የመንግሥቱን ሥልጣን ለሕዝቡ፣ ለቤተክርስቲያን እንዴት እንዳስተላለፈና እኛ አሁን ክብሩን በዓለም ላይ ለማሳየትና የእርሱ ተወካዮች በመሆን የመንግሥቱን አገዛዝ እስከ መጨረሻው ጫፍ ድረስ ለመግለጥ እንዴት እንደተጠራን እንመለከታለን።
ሌሎች ምደባዎች
2
ለቀጣዩ ትምህርት መዘጋጀት
Made with FlippingBook Digital Publishing Software