The Kingdom of God, Amharic Mentor Guide
/ 6 5
የ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር መ ን ግ ስ ት
መታመም፣ ማጣት ወይም መደህየት እንደሌለበት አጽንዖት ይሰጣል። በዚህ ትምህርት መሠረት የዚህ ትምህርት ልብ በክርስቲያን ሥልጣን ላይ የተመሰረተ ነው። ኢየሱስ ወደ ሰማይ ባረገ ጊዜ፣ ኢየሱስ ሁሉንም ሥልጣን ስለያዘ፣ ይህንም ስልጣን ለህዝቡ ለቤተክርስቲያን አሳልፎ ስለሰጠ፣ ቤተክርስቲያን በዲያብሎስ ላይ በቀጥታ ልትገዛ ትችላለች፣ ለመጉዳት ወይም ለማጥፋት ያለውንም ሀሳብ ማክሸፍ ትችላለች። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ ይህን ትምህርት አጥብቀው የያዙ አንዳንዶች ከታመምክ፣ ከተቸገርክ ወይም ከተሸነፍክ ጥፋቱ ያንተ ብቻ ነው ብለው ያምናሉ። እግዚአብሔር ፀጋውን ሰጥቷል፣ ስለዚህም አንተ የሚያስፈልግህ እውቅና መስጠት ብቻ ነው። ይህ ነገር ትክክል ነው ወይንስ ነገሮቹ በጣም ተለጥጠዋል? የትኛው ሞዴል በተሻለ ሁኔታ ይሰራል? በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ካሉት እጅግ በጣም የሚያጋጩ እና አስቸጋሪ ጉዳዮች አንዱ በጥያቄ መልክ ሊቀመጥ ይችላል፡ ቤተክርስቲያን ከአለም ጋር ያላት ግንኙነት ምን መምሰል አለበት? ስለ ቤተክርስቲያን-ዓለም ግንኙነት እንዴት ማሰብ አለብን? ቤተክርስቲያን የገሃነምን ደጆች እንደወረረች መናገር ጥሩ ነው ወይንስ ቤተክርስቲያን ከመካከል ወጥታ ተለይታ ትኑር? እውነቱን ለመናገር፣ ቤተክርስቲያን ከዓለም ጋር ያላትን ግንኙነት ለመረዳት ከሁሉ የተሻለው ሞዴል ምንድን ነው - ቤተክርስቲያን አለምን ለመለወጥ መፈለግ አለባት፣ ቤተክርስቲያን ከአለም መውጣት አለባት ወይስ ቤተክርስትያን በሆነ መንገድ ከአለም ጋር በውጥረት ውስጥ መኖር አለባት?
3
3
የእግዚአብሔር መንግሥት ወረራ ክፍል 1
ይዘት
ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ
የዚህ ክፍል ዓላማ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እንደ አካሉ እና ወኪሉ እንዴትራሷ የእግዚአብሔር ማዳን ስፍራ (ቦታ እና/ወይም አውድ)፣ የመንፈስ ቅዱስ ህላዌ እና እውነተኛ የመንግሥቱን ሕይወትና ምሥክርነት መግለጫ ስፍራ እንደሆነች ማሳየት ነው። ። የዚህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወረራ የመጀመሪያ ክፍል አላማችን የሚከተሉትን እንድታይ ለማስቻል ነው፡- • የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ማዳን ቦታ (ቦታ ወይም አውድ) ነው። • ቤተ ክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ ኅላዌ መገኛ ናት። • ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር እውነተኛ መንግሥት ሻሎም መገኛ ናት። • አዎን፣ የእግዚአብሔር መንግሥት በኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ህልውና እና ልምምድ ይህንን ግዛት እየወረረ ነው!
የክፍል 1 ማጠቃለያ
ገጽ 298 4
Made with FlippingBook Digital Publishing Software