The Kingdom of God, Amharic Student Workbook
/ 1 0 3
የ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር መ ን ግ ስ ት
9. የመካከለኛውን ሁኔታ አመለካከት “የነፍስ እንቅልፍ” እና “ፐርጋቶሪ” የሚለውን እንዴት ትገልጸዋለህ? ለእነዚህ አመለካከቶች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ምንድን ነው? አሳማኝ ሆኖ አግኝተሃቸዋል? 10. የመካከለኛው ሁኔታ የጌታ መገኘት ለክርስቲያኖች ብቻ እንደሆነ ስለሚያትተው እይታ ግለጽ። እዚህ ላይ ያለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ አሳማኝ ሆኖ አግኝተሃል? ለምን?
የእግዚአብሔር አገዛዝ ተፈፀመ ክፍል 2
ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ
ከእግዚአብሔር መንግሥት ፍጻሜ ጋር የተያያዙት አጠቃላይ አካላት የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት፣ የሙታን ትንሣኤ እና የመጨረሻው ፍርድ፣ እና የእግዚአብሔር ሁሉ-በሁሉ መሆን ነው። የዚህ የእግዚአብሔር አገዛዝ ተፈጸመ ለተሰኘው የሁለተኛው ሴግመንት አላማችን የሚከቱልትን እንድትችል መርዳት ነው፡- • የእግዚአብሔርን መንግሥት በምድር ላይ ይፈጸም ዘንድ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ጋር የተያያዙትን አስፈላጊ ነገሮች ግለጽ። • ከሙታን ትንሣኤና ከመጨረሻው ፍርድ ጋር የተያያዙ የቅዱሳን መጻሕፍትን ትምህርቶች በግልጽ ተናገር። • ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ሁሉ በሁሉ በሚሆንበት ጊዜ ስለሚጠናቀቀው መንግሥት የመጨረሻ ሁኔታ አሰላስል።
የሴግመንት 2 ማጠቃለያ
4
I. መንግሥቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓት ትፈፀማለች።
የቪዲዮ ሴግመንት 2 ዝርዝር
ሀ. የኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት (parousia) በእርግጥ ይፈጸማል፣ ደግሞም ተወስኗል።
1. “መገኘት” ወይም “መምጣት” ተብሎ ሊተረጎም የሚችለው ፓሮሲያ ብዙ ጊዜ ከኢየሱስ ዳግም ምጽአት ጋር ይያያዛል። እንደ ማቴዎስ 24:30 እና 26:64
2. ጴጥሮስ የኢየሱስን መምጣት እርግጠኝነት ያመለክታል፣ ሐዋ 3፡19-21።
Made with FlippingBook - Share PDF online