The Kingdom of God, Amharic Student Workbook
7 2 /
የ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር መ ን ግ ስ ት
2. በኒቂያ የሃይማኖት መግለጫ አራት መልክ ያለው የቤተ ክርስቲያን ፍቺ እና ትርጓሜው ምንድን ነው? ለምንድነው እነዚህ ትርጓሜዎች ለቤተክርስቲያን ግንዛቤ አስፈላጊ የሆኑት? 3. የመንፈስ ቅዱስ የሥልጣን መገኘት ቦታ እንደመሆኑ መጠን፣ መንፈስ የሚመጣው የመንግሥቱ በረከቶች ቀብድ (አርቦን) የሚሆነው በምን መንገድ ነው? ይህ ከብሉይ ኪዳን የቤተክርስቲያን መረዳት ጋር እንዴት ይዛመዳል (የጴጥሮስ መግለጫ በበዓለ ሃምሳ)? 4. ቤተክርስቲያን በክርስቶስ የእግዚአብሔር መገለጥ “ጠባቂ” ወይም “ባላደራ” ናት ሊባል የሚችለው በምን መልኩ ነው? 5. በክርስቶስ አካል እና በኃጢአት ስርየት መካከል ያለው ግንኙነት ምንድን ነው? አንድ ሰው የእግዚአብሔርን ይቅርታ አግኝቶ የክርስቶስ አካል አለመሆን አይችልም? ለምን ወይም እንዴት? 6. “የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የቤተክርስቲያን ጌታ፣ እሷንም በዓለም ላይ የሚያስታጥቃት፣ የሚመራ እና የሚያግዛት ነው” የሚለውን ሃሳብ የሚደግፉ በርካታ ምሳሌዎችን ከቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ስጥ። 7. የእግዚአብሔር መንግሥት በቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ የሚታየው እና የሚገለጸው በምን መንገዶች ነው? ቤተክርስቲያን የመንግስቱ ሃይል (የእግዚአብሔር ሉዓላዊ አገዛዝ) የሚተገበርባት የመሆኗን እውነት ማረጋገጥ ለምን አስፈለገ? 8. መንግስቱ ለቤተክርስትያን እንደ ስጦታ እና ተግባር መሆኑን መናገሩ ትክክል የሚሆነው በምን መንገድ ነው?
3
የእግዚአብሔር መንግሥት ወረራ ክፍል 2
ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ
የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በአለም ላይ ያለውን የመንግስቱን አላማ ለማራመድ ወኪል፣ ፈቃደኛ እና የሚገኝ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነች። የዚህ የእግዚአብሔር ግዛት ወረራ ሁለተኛ ክፍል አላማችን የሚከተሉትን እንድታይ ለማስቻል ነው፡- • የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በአለም ላይ ያለውን የመንግስቱን አላማ ለማራመድ ወኪል፣ ፈቃደኛ እና ለእግዚአብሔር የሚገኝ አገልጋይ ነች። • ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔርን እንደ ንጉሥና ጌታ በማምለክ የእግዚአብሔር መንግሥት ወኪል ናት። • ቤተክርስቲያን በሐዋርያዊ ምስክርነት የእግዚአብሔር መንግሥት ወኪል ናት።
የክፍል 2 ማጠቃለያ
Made with FlippingBook - Share PDF online