The Kingdom of God, Amharic Student Workbook

8 2 /

የ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር መ ን ግ ስ ት

* የእግዚአብሔርን አገዛዝ በሕይወቱ እና በምስክርነቱ ላይ ኃይለኛ ምስክር እየሰጠ በማይመስለው ቤተክርስቲያን ወይም የክርስቲያን ማህበረሰብ ላይ መነቃቃትን ለማየት ምን ደረጃዎች አሉ? * ቤተክርስቲያን የመንግሥቱ ቦታ እና ወኪል ሆና ለማየት መሪዎች ምን ሚና ይጫወታሉ? * አብያተ ክርስቲያናት በጣም ሊበዘዙ እና ሊበታተኑ ይችላሉ - እንዴት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ራዕይን ወስደህ በአብያተ ክርስቲያናት መካከል ተካፍለው ስለ እግዚአብሔር መንግሥት አብረው እንዲመሰክሩ ለመገዳደር? ይህ ትክክለኛው ነገር ነው? በቅርቡ በአንዲት ትንሽ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ፣ ወጣቶቹ በአስደናቂ ሁኔታ ወደ መመለስን አሳዩ። 100 ወይም ከዚያ በላይ የሚሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ያሉት ይህ ቡድን ለወራት ከተራዘመ ጸሎት እና የእርስ በርስ ግልጽ ውይይት በኋላ እግዚአብሔር በመካከላቸው አስደናቂ ነገሮችን ሲያደርግ ማየት ጀመሩ። በርካታ ተማሪዎች እምነታቸውን ለጓደኞቻቸው ከማካፈላቸው እና ወደ ጌታ ሲመጡ ከማየታቸው በተጨማሪ፣ በርካታ ተማሪዎች አልኮልን፣ አደንዛዥ እጾችን እና ህገወጥ ወሲባዊ ድርጊቶችን በመተው ኃጢአታቸውን በጌታ እና በህዝቡ ፊት ተናዘዋል። የዚህ ቡድን አምልኮ አስደናቂ ነበር - አምልኮው ፍሰቱን፣ ትኩሳቱንና እውነተኛነቱን ሳያጣ ሰዓታት ያለፉ ይመስላሉ ። የእነዚህ ለውጦች ተጽእኖ በወጣቶች ላይ ብቻ የሚወሰን ቢመስልም፣ ይህ አዲስ ፍሰት ያስከተለውን ተጽዕኖ ወደ መላው ቤተ ክርስቲያን ይስፋፋ መላው ቤተ ክርስቲያን ፍላጎት አድሮበታል። ዛሬ በክፍል ውስጥ ከተነጋገርነው ትምህርት አንጻር የወጣት ቡድኑ መሪ ለእነዚህ ወጣቶች ስለ ልምምዳቸው ማስተማር ያለበት ምንድነው? ሰፋ አድርገን ብናየው እነዚህ ወጣቶች እንደ ሕያው ቤተ ክርስቲያን ወጣቶች ምን ማድረግ አለባቸው? በቤተ ክርስቲያናቸው ውስጥም ሆነ ከቤተክርስቲያን ውጪ የመንግሥቱ ምሥክር ይሆኑ ዘንድ እንዴት ሊጠቅሙ ይችላሉ? ተስፋ በመቁረጥ ጫፍ ላይ የአንዲት ትንሽ ከተማ ቤተክርስቲያን ወጣት መጋቢ እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን ውስጥ ሲንቀሳቀስ ለማየት ለዓመታት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ተግቶ ያገለግላል። ከትልቁ ቤተ ክርስቲያን የወጣች አነስተኛ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ነች። አብዛኞቹ አባላት እርስ በርስ ግጭት ውስጥ ገብተዋል፣ በርከት ያሉትም በቤተክርስቲያኒቱ አመራር ላይ ቅሬታ እንዳላቸው ገልጸዋል። ስለ ቤተ ክርስቲያን እድገት እና መነቃቃት የቅርብ ጊዜ መጻህፍትን ለማገላበጥ ሞክሯል፣ ነገር ግን ይህም የሚሰራ አይመስልም። እውነቱን ለመናገር፣ አሁን እራሱም በጣም ተስፋ ቆርጧል። በቤተክርስቲያን እና በመንግሥቱ መካከል ስላለው ግንኙነት ግንዛቤ እንዳለህ አወቀ እንበል። ይህንን የወጣት መጋቢ በአገልግሎቱ ለማበረታታት ምን ትለዋለህ? ከዚህ ለቅቆ ሌላ ቤተ ክርስቲያን ፈልጎ ይሂድ፣ ከጥቂቶች ጋር በዚያው ይቆይ ወይስ ቅር የተሰኙትን ምእመናን ይዞ ይገንጠል? ለመቀጠል አስፈላጊውን ማበረታቻ ለማግኘት የራሱን አመለካከት እንዴት መቀየር ይችላል?

ጥናቶች

1

3

2

Made with FlippingBook - Share PDF online