The Kingdom of God, Amharic Student Workbook

/ 8 3

የ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር መ ን ግ ስ ት

በርግጥ መንግሥቱን እያሳየ ያለው ማን ነው? ሚስተር ጆንስ የተባለ አንድ ዲያቆን በቅርብ ጊዜ በቤተክርስቲያኒቱ ስለተጀመረው የእስር ቤት አገልግሎት ላለፉት 12 ወራት በጣም ተደስቷል። በየሳምንቱ ከ3-4 የሚደርሱ ሰራተኞች በአካባቢው ወደሚገኝ እስር ቤት በመሄድ ከእስረኞቹ ጋር ህብረት በማድረግ፣ ለሥጋዊ ፍላጎቶቻቸው ድጋፍ በማድረግና እና ክርስቶስን ለእስረኞቹ በማካፈል ያሳልፋሉ። ውጤቱ እጅግ አመርቂ ነበር! ከ20 በላይ ወንዶች እና ሴቶች ክርስቶስን የመከተል ውሳኔ ላይ ደርሰደዋል፣ እንዲሁም አብዛኛዎቹ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከእስር ቤት ለመውጣት ባይችሉ እንኳን ወጥተው የመስራት ፈቃድ አግኝተዋል። ሚስተር ጆንስ ወደ መጋቢው ሄዶ ቤተ ክርስቲያኒቱ እነዚህን አዳዲስ አማኞች ወደ ቤተ ክርስቲያናቸው ለማምጣት፣ ደቀ መዛሙርት ለማድረግ እና በማህበረሰቡ ውስጥ እንደገና እንዲቋቋሙ ለማድረግ የሚያስችል መርሃ ግብር መፍጠር እንዳለባት ጠቁሟል። መጋቢው ብዙ የእስረኞች ፍሰት በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ችግር ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት ካደረባቸው አንዳንድ አባላት የስልክ ጥሪ ደርሶታል፣ “ከዚህም በተጨማሪ ከእነዚህ ሰዎች ውስጥ ብዙዎቹ ዘግናኝ ድርጊቶችን አድርገዋል። ታዲያ የቤተክርስቲያንን ልጆች ለእንደዚህ አይነት ሰዎች ማጋለጥ አለብን? ሚስተር ጆንስ ምክር ይጠይቅሃል። ስለ ቤተ ክርስቲያን፣ ስለ መንግሥቱ እና ስለ ከተማ አገልግሎት ከምታውቀው አንጻር፣ እርሱ፣ መጋቢውም ሆነ ቤተ ክርስቲያን ይህንን ዕድልና ፍላጎት ለማሟላት ምን እንዲያደርጉ ሐሳብ ታቀርባለህ? የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን፣ እንደ አካሉ እና ወኪል፣ እራሷ የእግዚአብሔር ማዳን ስፍራ (ቦታ እና/ወይም አውድ)፣ የመንፈስ ቅዱስ ህላዌ እና ትክክለኛው የመንግስቱ ህይወት እና ምስክርነት መገለጫ ናት። የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ቦታ ብቻ ሳትሆን የእግዚአብሔር ወኪል ናት፣ በዚህ ዘመን እንደ ተዋጊ ቤተክርስቲያን በአለም ላይ የመንግስቱን አላማ ለማስፈፀም ፈቃደኛ እና ዝግጁ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነች።

3

3

የትምህርቱን ንድፈ ሃሳብ በድጋሚ መጻፍ

የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አሁን ባለው ዓለም ውስጥ እንደ እግዚአብሔር መንግሥት ቦታ እና ወኪል ስለመሆኗ የበለጠ ለማንበብ ፍላጎት ካለህ እነዚህን መጻሕፍት መመልከት ይረዳህ ይሆናል:

ማጣቀሻዎች

Perkins, John. With Justice for All. Ventura: Regal Books, 1984.

Sider, Ron. Rich Christians in an Age of Hunger. Downers Grove: InterVarsity Press, 1977. Snyder, Howard A. The Community of the King. Downers Grove: InterVarsity Press, 1977. Stott, John W. Involvement: Being a Responsible Christian in a Non-Christian Society. Vol. 1. Old Tappan: Fleming H. Revell Co., 1985.

Made with FlippingBook - Share PDF online