The Kingdom of God, Amharic Student Workbook

8 4 /

የ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር መ ን ግ ስ ት

እነዚህን እውነቶች በቤተክርስቲያንህ በኩል ከራስህ አገልግሎት ጋር ለማዛመድ መፈለግ የዚህን ትምህርት ዋና ነገር ያመለክታል። በእነዚህ እውነቶች ላይ ተመስርቶ የአገልግሎትህን አካሄድ እንድትቀይሩ ወይም እንድታስተካክል እግዚአብሔር እንዴት እንደሚፈልግ የተመሰረተው አንተ ስላለህበት፣ የመጋቢነት አመራርህ የት እንዳለ፣ የቤተክርስቲያናችሁ አባላት ስላሉበት ቦታ መንፈስ ቅዱስ የሚናገርህን ለመስማት ባለው ችሎታ ላይ ነው። በተለይም ስለእነዚህ እውነቶች እግዚአብሔር አሁን ምን እንድታደርግ እየጠራችሁ በመሆኑ ላይ ነው። በዚህ ሳምንት ቤተክርስቲያን የመንግስቱ ቦታ እና ወኪል ትሆን ዘንድ ስለመጠራትዋ እና አገልግሎትህ እና የቤተክርስትያንህ አገልግሎት ይህን ጥሪ እንዴት እንደሚያንጸባርቁ በማሰላሰል ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ እቅድ ያዝ። ለዚህ ሞጁል የአገልግሎት ፕሮጄክትህን በምታስብበት ጊዜ፣ ከእነዚህ እውነቶች ጋር በተግባራዊ መንገድ ለመገናኘት ልትጠቀምበት ትችላለህ። ማስተዋል ይሰጥህ ዘንድ የእግዚአብሔርን ፊት በመፈለግ በሚቀጥለው ሳምንት ያገኘኸውን ግንዛቤ በክፍልህ ውስጥ ላሉ ሌሎች ተማሪዎች ለማካፈል ተዘጋጅተህ ቅረብ። ምናልባት መንፈስ ቅዱስ በዚህ ስለ ቤተ ክርስቲያን ባደረከው ጥናት እና ውይይት የገለጻቸው አንዳንድ ልዩ ፍላጎቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ሸክሙን የሚካፈል እና ልመናህን ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርብ የጸሎት አጋር ለማግኘት አታቅማማ። እርግጥ ነው፣ በዚህ ጥናት ላይ ከአንተ ጋር በጸሎት ለመቆየት አስተማሪህ በጣም ዝግጁ ነው፣ በተጨማሪም በዚህ ጥናት ላይ ለሚነሱብህ ማናቸውም ጥያቄዎች መልስ እንዲሰጡህ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችህ፣ በተለይም መጋቢህ፣ ከዚህ አንጻር የታጠቁ ሊሆኑ ይችላሉ። ለእግዚአብሔር ክፍት ሁን እና እርሱ እንደወሰነው እንዲመራህ ፍቀድለት።

የአገልግሎት ግንኙነቶች

ምክር እና ጸሎት

3

ምደባዎች

1ኛ ጴጥሮስ 2፡9-10

የቃል ጥናት ጥቅስ

ለክፍል ለመዘጋጀትና የሚቀጥለውን ሳምንት የምንባብ ምደባ ለማግኘት www.tumi.org/books ን ጎብኝ ወይም መምህርህን ጠይቅ።

የንባብ የቤት ስራ

እንደተለመደው የሳምንቱን የንባብ ይዘት ማጠቃለያ የያዘ የንባብ ድልድል ወረቀትህ ጋር መምጣት አለብህ። እንዲሁም፣ ለትርጓሜ ፕሮጄክትህ የምትሰራበትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል መርጠህ ወደ አገልግሎት ፕሮጀክትህ መመለስ ይኖርብሃል።

ሌሎች የቤት ስራዎች

Made with FlippingBook - Share PDF online