Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide
/ 3 1
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
የሚከተሉት ጥያቄዎች የተነደፉት በሁለተኛው የቪዲዮ ክፍል ውስጥ የሚገኘውን ሕይወት ሰጪ የሆነው የእግዚአብሔር ቃል በሕይወታችን ውስጥ ስላሉት ባሕርያት ላይ ያተኮረውን ሐሳብ እንድትከልስ ለመርዳት ነው። መልሶችህ ግልጽ እና አጭር ይሁኑ፣ አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ አስደግፍ! 1. መጽሐፍ ቅዱስ በክርስቶስ ለሚያምን ሰው አዲስ ሕይወት በመስጠት ረገድ ቅዱሳት መጻሕፍት የሚጫወቱትን ሚና እንዴት ይገልጸዋል? አዲስ ውልደትን ለመፍጠር እምነት ከቃሉ ጋር ምን ሚና ይጫወታል? 2. የኢየሱስ ፈተና የእግዚአብሔር ቃል በሕይወታችን ያለውን ኃይል የሚያስተምረን በምን መንገድ ነው? ኢየሱስ በምድረ በዳ በዲያብሎስ ሽንገላ በተፈተነ ጊዜ ምን አይነት እውነት ጠቅሷል? 3. መንፈሳዊ ሰው የቅዱሳን ጽሑፎችን ትርጉም እንዲገነዘብ መንፈስ ቅዱስ ምን ሚና ይጫወታል? ፍጥረታዊው ሰውስ - ሊረዳው ይችላልን? ለምን? 4. የኢየሱስ ክርስቶስ የደቀመዝሙርነት እውነተኛ ምልክት ምንድን ነው? በመንፈሳዊ እድገት እና የእግዚአብሔርን ቃል በመመገብ መካከል ያለውን ግንኙነት ግለጽ? 5. አንድ ሰው በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ እንዴት መኖር እንደሚችል ቅዱሳት መጻሕፍት የሚጠቁሟቸው አንዳንድ መንገዶች ምንድን ናቸው? በቃሉ ውስጥ መኖር በክርስቲያን ማህበረሰብ ውስጥ ከመኖር ጋር እንዴት ይገናኛል? 6. ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔርን ቃል እንድትረዳ እና እንድትተገብር እግዚአብሔር የሰጣት ምን አይነት ሰዎችን ነው? ክርስቲያኖች አገልግሎት እንዲሰጡ በመርዳት ረገድ ያላቸውስ ሚና ምንድን ነው? 7. በቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት፣ እግዚአብሔር ለፈጠረው ጽንፈ ዓለም ያለው ዘላለማዊ ዓላማ ምንድን ነው? 8. እግዚአብሔር ለአማኞች የሰጠው የመጨረሻው የላቀ ዓላማ ምንድን ነው? አማኞች ይህን ዓላማ በሕይወታቸው ውስጥ ማስፈጸም የሚችሉትስ እንዴት ነው? 9. ቅዱሳት መጻሕፍት በዓለም ላይ ካሉ መጻሕፍት ሁሉ የተለዩና የላቁ የሆኑት በምን መንገድ ነው? 10. ፈጣሪ ለሆነው የእግዚአብሔር ቃል ስንገዛ በልባችንም ሆነ በሕይወታችን ውስጥ ምን እንዲፈጠር እንጠብቃለን? አብራራ።
መሸጋገሪያ 2
የተማሪው ጥያቄዎችና ምላሽ
ገጽ 163
9
1
Made with FlippingBook Annual report maker