Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide
3 2 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ግንኙነት
ይህ ትምህርት የእግዚአብሔርን ቃል የመፍጠር ሃይል አንዳንድ ወሳኝ ገፅታዎችን ያጎላል፣ በፅንፈ ዓለሙ አፈጣጠር ውስጥ እና በአማኙ ልብ ውስጥ ስለሚፈጠረው አዲስ መንፈሳዊ ህይወት ያስረዳል። በሁሉም መልኩ፣ የእግዚአብሔርን ቃል በአለም እና በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ያለውን ስራ ለመረዳት የእግዚአብሔር ቃል እሳቤ ጠቃሚ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሕያው እና ዘላለማዊ የእግዚአብሔር ቃል ነው። በእርሱ አነሳሽነት ተጽፏል፤ እንዲሁም ከእግዚአብሔር ማንነት እና ስራው ጋር በቀጥታ የሚታወቀው በራሱ የእግዚአብሔር ህይወት ተሞልቷል። ቅዱሳት መጻሕፍት ከእግዚአብሔር ማንነትና ሥራ ጋር በጣም የተቆራኙ በመሆናቸው በሚገልጹት እና እውነት በሆኑ ነገሮች ሁሉ ላይ ሙሉ በሙሉ እምነት የሚጣልባቸው እና ስልጣን ያላቸው ናቸው። አጽናፈ ሰማይ እና በውስጡ የያዘው ሁሉም ህይወት የተፈጠረው “ኤክስ ኒሂሎ” (ማለትም ከምንም) በእግዚአብሔር ቃል ሕይወት ሰጪ ኃይል ማለትም በፍጥረት ጊዜ በተናገራቸው ቃላት ነው፤ በተጨማሪም፣ ሁሉን ቻዩ አምላክ ሕያው በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ሁሉንም ነገር ፈጥሯል (ዮሐንስ 1.1-3፤ ቆላ. 1.16)። ቅዱሳት መጻሕፍት በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፉት “ፕሮፖዚሽናል” የእግዚአብሔር ቃል ሲሆን ሁለቱንም ብሉይ ኪዳን (ማለትም፣ የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች) እና አዲስ ኪዳንን (ማለትም፣ የክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍት) ያካትታል። እግዚአብሔር ራሱን በገለጠበት፣ ዓለምን በመቤዠት እና በጽድቅ አገዛዙ ሥር ያለውን ጽንፈ ዓለም በሚመልስበት በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ራሱን ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ሙሉ በሙሉ ገልጿል። የእግዚአብሔር ቃል፣ በመንፈስ ቅዱስ የተፃፈ እና የእግዚአብሔር ሕይወት ያለበት፣ በኢየሱስ በሚያምኑት ውስጥ አዲስ ሕይወትን የሚፈጥር ዋና መሣሪያ ነው። የወንጌል መልእክት ከላይ ከእግዚአብሔር እንድንወለድ የሚያደርገን መንፈሳዊ ዘር ነው። ትክክለኛው የክርስቶስ ደቀመዝሙርነት ምልክት አማኞችን ነጻ በሚያወጣው በኢየሱስ ቃል ውስጥ መኖር እና መቀጠል ነው። እርሱ በመንፈሱ የጻፈውን የቅዱሳት መጻሕፍትን ትርጉም እንድንረዳ እና እንድናስተውል እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ አማኝ መንፈስ ቅዱስን ሰጥቷል (1ቆሮ. 2.9-16 ዝ. 2 ጴጥ. 1.21-22)። መንፈስ ቅዱስ የፍጥረት አጽናፈ ዓለም የመጨረሻ ዓላማ ሁሉን ቻይ የሆነውን እግዚአብሔርን ማክበር እንደሆነ ያስተምረናል (ኢሳ. 43.7፤ ምሳ. 16.4፤ 1 ቆሮ. 10.31)። ቅዱሳት መጻሕፍት፣ የሚፈጥረው ቃል፣ በእግዚአብሔር አገዛዝ ሥር ስንኖር እግዚአብሔርን እንድናከብር በመንፈስ ያስችለናል።
የቁልፍ ፅንሰ-ሀሳቦች ማጠቃለያ
ገጽ 163 10
1
Made with FlippingBook Annual report maker