Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

ተጨማሪ መግላጫ • 125

ተጨማሪ መግለጫ 2 እግዚአብሔር እየተናገረ ያለው ታሪክ ሬቨ. ዶን አልስማን

የምዕራፍ ርዕስ

የምዕራፍ ማጠቃለያ

ጭብጥ ቁጥር

በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም(የዮሐ. ወንጌል1፡1-3 )። ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ( ሮሜ 5፡12)። እነርሱ እስራኤላውያን ናቸውና፥ ልጅነትና ክብር ኪዳንም የሕግም መሰጠት የመቅደስም ሥርዓት የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና፤ አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን (ሮሜ 9፡4-5)። ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት ትታወቅ ዘንድ፤ ይህም በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የፈጸመው የዘላለም አሳብ ነበረ (ኤፌ. 3፡10-11) ። 24 በኋላም፥ መንግሥቱን ለእግዚአብሔር ለአባቱ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ አለቅነትንም ሁሉና ሥልጣንን ሁሉ ኃይልንም በሻረ ጊዜ፥ ፍጻሜ ይሆናል። ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና። የኋለኛው ጠላት የሚሻረው ሞት ነው (1ኛ ቆሮ. 15፡24-26) ። የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ሆኑ (ራዕ. 11፡15ለ) ። የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ (1ኛ ዮሐ. 3፡8ለ) ።

ሙከራ የተደረገበት መንግስት

እግዚአብሔር ከመፍጠሩ በፊት ፍጹም በሆነ ህልውና ውስጥ ይኖራል። ዲያብሎስ እና ተከታዮቹ አመፁ እናም ክፉን ወደ ሕልውና አመጡ።

(ከጊዜ በፊት) ዘፍጥረት 1፡1 ሀ

መረጋጋት

ሰይጣንን በአመጽ የተባበረውን የሰውን ለጅ እግዚአብሄር በመልኩና በአምሳሉ ፈጥሮታል።

(ፍጥረት እና ውድቀት) ዘፍጥረት 1፡1b - 3፡13

እግዚአብሔር አህዛብን ጨምሮ ሰዎችን የሚያድነውን ንጉሥ የሚያመጣበትን የራሱን ሕዝብ ለመለየት ይሟገታል። ለጦርነት ያሉትን ዕቅዶቹ የሚረዱ ፍንጮችን በጉዞ ላይ ጠቁሟል።

ወረራ ለማካሄድ ዝግጅት

(አባቶች፣ ነገሥታት እና ነቢያት) ከዘፍጥረት 3፡14 - ሚልክያስ

ድል እና ማዳን

አዳኙ ጠላትን ትጥቅ ለማስፈታትና ለማጥፋት ይመጣል።

(ሥጋ መልበስ፣ ፈተና ተአምራት ትንሳኤ) የማቴዎስ ወንጌል-የሐዋ. ስራ 1፡11

አዳኙ የጠላት ንብረት የሆነውን እየጨመረ በሚሄድ የባለቤትነት መብት እንዲወስዱ ለመረጣቸው ህዝቦቹ ወደፊት የሚመጣው መንግሥት ህይወት በማቅመስ ያለውን ዕቅዱን ገልጧል።

የሰራዊቱ መስፋፋት

(ቤተክርስትያን) የሐዋርያት ሥራ 1:12 - ራዕይ ምዕራፍ 3

የፍጻሜው ጦርነት

ይህ አዳኝ ጠላቱን ለማጥፋት ሙሽራውን ለማግባት እና ትክክለኛ ስፍራውን ዙፋኑ ላይ ለማስቀጠል ይመለሳል።

(ሁለተኛው መምጣቱ) የዮሐንስ ራዕይ 4-22

የመጽሐፍ ቅዱስ ትረካዊ ዋናው ማሰሪያ ጦርነት ነው።

በመንግስታቱ መካከል ያለ ጦርነት

ይህ ዓለም አስፈሪ ነገሮች እና ድንቅ ነገሮች ያሉበት ዓለምም ነው። መልካምነት ከክፉ ጋር የሚጣረሱበት፣ ጥላቻን በመውደድላይ፣ ስርዓት ከስርዓት አልበኝንት ከፍተኛ ትግል የሚያደርጉበት፣ ብዙን ጊዜም በየትኛውም ጎራ ውስጥ ማን ምን እንደ ሆነ ማወቁ አስቸጋሪ በሚሆንበት አስቸጋሪ ሁኔታ በሚፈጠርበት ታላቅ ትግል ውስጥ ያለው። ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ ውዥንብር እና አውሬነት ተሸንፎ፤ ይህ ዓለም ውጊያው በፍጻሜ በመልካምነት የበላይነት የሚጠናቀቅበት፣ሁሉም ከዚያ ብኋላ በደስታ የሚኖሩበት እና ሁሉም ሰው, መልካም እና ክፉ, በእውነተኛው ስሙ የሚታወቅበት ይሆናል።

-ፊደርሪክ ብዩነር. እውነትን መናገር

Made with FlippingBook - Online magazine maker