Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

ተጨማሪ መግላጫ • 145

ተጨማሪ መግለጫዎች 16 ወደ ኋላ መለስ ብለን በመሄድ ወደፊት ማለፍ ወደ ታላቁ የወንጌል ባህል መመለስ ሬቨ. ዶ/ር ዶን ኤል. ዳቪስ

“ታላቁን ባህል” እንደገና ማግኘት በጣም ግሩም በሆነች ትንሽ መጽሐፍ ውስጥ ኦላ ታዮርሆም 1 “የቤተክርስቲያንን ወግ” ተብሎ የሚጠራውን (አንዳንድ ጊዜ “ ዘመን ተሻጋሪ ክርስቲያናዊ ባህል”) ተብሎ የሚጠራውን እንደ “ሕያው ያልተበከለ እና ተለዋዋጭ” 2 በማለት ገልፆታል። ታላቁ ባህል በመባል የሚታወቀው ወንጌል አማኞች ሐዋርያዊ እና የካቶሊካዊ ዋና የክርስትና እምነት እና ልምምድን በአብዛኛው ከ100-500 ዓ. ም 3 የተገኘው ውጤት ይወክላል። የዚህ ትልቅ ውርስ እና ውድ ሀብት የቤተክርስቲያንን የእምነት አቋም ምስክርነት /ኮንፌሽን/ ሁልጊዜ ያመነችውን ቤተመንግስት ያመለክት ነበር, የጥንት ቤተ ክርስቲያንን አምልኮ, ያልተከፋፈለችው ቤተክርስትያን ያከበረችውና ያፀደቀችው እና ቤተ ክርስቲያን ያቀፈችውና ታካሂድ የነበረውን ተልዕኮ ይወክላል ምንም እንኳን ታላቁ ልምምድ የሐዋርያትን ልምምድና ባህል መተካት ባይቻልም (ማለትም የሁሉም ክርስቲያናዊ እምነቶች መሰረት የሆነውን መጻሕ ፍቅዱስን) ወይም በቤተ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ በኩል በሙላት የተገለጠውን የክርስቶስን መገኘት መተካት ባይችልም አሁንም የእግዚአብሔር ሕዝብ እንደገና ለማነቃቃትና መመሪያ ለመስጠት እጅግ ጠቃሚ ነው። አሁንም ቢሆን ለእግዚአብሔርን ህዝብ መሰረታዊ የእምነት ዶግማዎችን እና የእምነት መሰረት ወይም ፍሬ ነገርን ሊሰጥ ይችላል። ታላቁ ትውፊታዊ ባህል በከካቶሊክ በኦርቶዶክስ በአንግሊካን እና የፕሮቴስታንት ጥንታዊና ዘመናዊው የሥነ መለኮት ምሁራን ዘንድ ተዓማኒነቱ የተረጋገጠ እና የሴሚናር ሰነዶችን ዶክትሪኖችን የእምነት እና የቤተክርስቲያን ልምዶችን (ለምሳሌ የቅዱሳን መጻሕፍት ቅደም ተከተል፣ የሥላሴ መሠረተ ትምህርቶች፣ የክርስቶስ አምላክ ወዘተ) መሰረት በመሆን የሚያገለግል ነው። በዛሬው ጊዜ በርካታ ወንጌላውያን ምሁራን ወደፊት ለታማኝ እምነት እና ቀጣይነት ላለው መንፈሳዊ እድገት ለሚደረገው ጉዞ ወደ ቀድሞው ወይም ወደ ጥንቱ ዘመን መመልከት እንዳለብን በአጽንዎት ያምናሉ፤ ይህም የድሮውን “መልካም ዘመን” ናፋቂ ወይም ከችግር ነጻ የሆነችን የጥንት ቤተ ክርስቲያንን አልያም የጥንት የእምነት አርበኞች ጉዞን ለመጎዳኘት እና እርባና ከሌለ መከራ ለመላቀቀ ካለ አስተሳሰብ ሳይሆን በተቃራኒው በዚህ ወሳኝ ታሪካዊ ወቅት ለጥንታዊ ቤተክርስቲያን ከፍ ያለ የአክብሮት መንፈስ እና ለቅዱስ ቃሉ ጥልቅ መሰጠት በታላቁ የቤተክርስቲያን ትውፊታዊ ባህል የተመሠረተ አዲስ እውነተኛ እና በኃይል የተሞላ እምነት እንደገና ማግኘት ይገባናል። ቤተክርስትያኗ

1 ኦላ ታዮርሆም, የምትታይ-ቤተክርስትያን-የሚታይ አንድነት፡ ኢኪሚንካል ትምህርተ ቢተ-ክርስቲያን እና “ታላቁ የቤተክርስቲያን ትውፊታዊ ባህል።” ኮሌጅቪል, ሚኔሶታ-Liturgical Press, 2004። ሮበርት ዌብበር ታላቁን የቤተክርስቲያን ትውፊታዊ ባህል ወይም ልምምድን በዚህ መንገድ ይገልፀዋል፦ “ይህ የክርስትናን እምነት እና ልምምድ ከክርስቶስ ዘመን እስክ በአምስተኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ደረስ ያለውን መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት አድርጎ የተዘጋጅ ሰፊ ንድፍ ማሳያ ነው።” ሮበርት ኢ. ዌበር, The Majestic Tapestry ናሽቪል: - ቶማስ ኔልሰን አታሚዎች 1986 (እ.አ.አ). 10.

2 Ibid. p. 35

3 የታላቁ የቤተክርስቲያን ትውፊታዊ ባህል በዋናነት የቤተክርስቲያንን የመጀመሪያዎቹ አምስት ክፍለ ዘመናት የክርስትና ህይወትና ስራዎች ላይ ድንጋጊዎች፣ የእምነት መግለጫዎች፣ እና ልምምዶች ላይ ነው የሚያተኩረው። ቶማስ ኦዴን በእኔ ድምዳሜ በርግጠኝነት መናገር የምችለው “. . . . ዘመናዊ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አተረጓጎም ውስጥ በአብዛኛው እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆኑት ትምህርቶች በአምስተኛው ክፍለ-ዘመን የተገኙ ናቸው” በማለት ገልጿል (ቶማስ ኦዴን, የሕይወት ቃል. ሳን ፍራንሲስኮ-ሀርፐር ሰንፍራንሲስኮ, 1989 ገጽ 11)።

Made with FlippingBook - Online magazine maker