Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

146 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ

ዋና እምነቶች እና ልምምዶች ከመጥፋታቸው በፊት እና ቤተክርስቲያን በአስከፊ ሁኔታ ከመከፋፈል ታሪኳ በፊት ያሉትን እምነቶችና ልምምዶች ስንቀበል ስንለማመድ ልንለወጥ እንችላለን።

በርግጥ ቢያንስ ቢያንስ የጥንቱን ቤተክርስትያን ትውፊት እና ህይወቱን እንደገና ለማየት እና ይህንን ትውፊት ወደ ቤተክርስቲያን ለመጪው ህይወትና ለቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ እንደግና ለማምጣት ስንጥር --- በርግጠኝነት እኛ ልናግኝ ተስፋ የምናደርገው ምንድን ነው? እኛ ግን ተመልሰን ለመመለስ ተስፋ እናደርጋለን ? እኛ የጥንት ቤተክርስትያን የተናገራቸውን እና እንደ “ወንጌል” ያደረጉትን ሁሉ የናዝሬቱ ኢየሱስ የአገልግሎት ዘመን ጋር ቅርበት ስላለው ብቻ ያለምንም መመዘኛ እርግጠኛነት መቀበል አለብን? በእድሜ የገፋ በራሱ “ውርስ” ነው? አይሆንም። ሁለንም ነገር ያለ ምንም መመዘኛ አልያም በእድሜ የገፋ በራሱ ጥሩ ውርስ ነው የሚለውን አናምንም። ለእኛ እውነት ከሀሳቦች ወይም ከጥንታዊ ድንጋጊዎች በላይ ነው፤ ለእኛ እውነት በናዝሬቱ ኢየሱስ ውስጥ ተዋህዶ እና ቅዱሳት መጻሕፍት በታሪክ ውስጥ የእርሱን መገላጥ እና ድነት ትርጉምን ማረጋገጫ እና የመጨረሻ ትርጓሜን ይሰጣሉ። ባለፉት ጊዜ እንደተከናወነ ወይም ቀደም ሲል የተከናወነ በመሆኑ ምክንያት ነገሮችን መቀበል አንችልም። በሚገርም ሁኔታ ታላቁና የጥንቱን ቤተክርስትያን ትውፊት ራሱ ነግሮችን በአንክሮ እንድንመለከት ፣ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ(ይሁዳ 3) ፣ በሐዋርያት ተቅባይነት ስላለውና ስለተከበረው ታላቁ ትውፊት፣ በቅዱሳን መጻሕፍት መሰረት በተመሰረተውና በተተርጎመው እና በክርስቲያኖች የእምነት መግለጫ እና ልምምድ የተገለጠውን እንድነመረምር ይሞግተናል። የታላቁ ትውፊት ወሳኝ እሴቶች ምንም እንኳን ታዮርሆም ስለ ታላቁ ትውፊት ለትርጓሜ እና ትኩረት ለመስጠት የሚያስችሉ አስር ሥነ መለኮታዊ ይዘት ነጥቦችን ቢያቀርብም 4 እኔ ከመጽሐፍ ቅዱስ እና ከመንፈሳዊ እይታ አንጻር የጥንቷ ቤተክርስትያን የያዘችው እምነት ምን እንደሆነ፣ እንዴት እንዳመለኩ እና እንዴት እንዳገለግሉ እንዲሁም የተነሱባቸውን ኑፋቄዎች እንዴት እንደትቃውሙና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላቸውን ህያው እምነት እንደጠበቁ የሚያሳዩ ሰባት ነጥቦችን ጨምሬአለሁ። ዳቆሙ ያምን ነበር. ፣ ለእነዚህ ሰነዶች፣ የእምነት መግለጫቸው እና ልምምዶች ባላቸው ታማኝነትና መታዘዝ የጥንቷ ቤተክርስቲያን በአረማውያነ እና በጠማማ ትውልድ መካከል ስለ እግዚአብሔር የድነት ተስፋ ህያው ምስክርነታቸውን አቅርበዋል።

አሁን ያለን እምነታችን እና ልምምዳችን በዚህ ዘመን ውስጥ የተገነባ ሲሆን ለሁለተኛ ጊዜ (እና ለሃያ-ሁለተኛው ዘመን) መታየት ይገባዋል።

ስለ ታላቁ የቤተ ክርስቲያን ትውፊት የታሪዮም ንድፈ ሐሳብን ማስተካከል፣ በተገቢው ስፈራ ማስቀመጥ እና ማሳደግ እንዲቻል ሙሉ ትኩረታችንን እና በሙሉልብ የሆነ ማደስ እንዲሆን ወሳኝ መመዘኛዎች ናቸው ብዬ የማምንባቸውን ዝርዝር ነጥቦች ከዚህ በታች እጽፋለሁ። 1. የሐዋርያት-ተውፊት። ታላቁ ትውፊት በሐዋርያት ልምምድ ውስጥ የተመሰረተ ነው። ማለትም የኢየሱስ የሐዋርያነት ምስክርነት እና ዛሬ በእኛ መጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና ውስጥ በተካተተው የናዝሬቱ የኢየሱስን ሕይወት እና ሥራ በሙሉ ስልጣን በሰጡት የእርሱ ምስክርነት ላይ የተመሰረተ ነው። ቤተ ክርስቲያን ሐዋሪያዊት ናት- ክርስቶስ ራሱ የማዕዘን ድንጋይ የሆነላት

4 Ibid ., ገጽ27-29 የቶርሆም አሥሩ ክፍሎች ከሥራው አንፃር ያለውን መከራከሪያ ያቀረበ ሲሆን ከዚያም በተጨማሪ ስለ መዋቅሩ አካላት እና ስለ ታላቁ ልምዶች እንደገና ስለመጠቀም በመከራከር ላይ ያተኮረ ነው። እኔ በሙሉ ልቤ የእርሱን ማስረጃ እና አመክንዮ እቀበለዋሉ፤ ማለትም ልክ እኔ እንደማምነው ታላቁን ባህል ለማወቅ ያለን ፍላጎትን እና የምናደርገው ጥናት የዘመናዊቷን ቤተክርስትያን በአምልኮ በአገልግሎት እና በተልዕኮዋ ላይ ተሃድሶ ለማምጣት እና ለማበልጸግ እንደሚያስችል እርግጠኛ ነኝ።

Made with FlippingBook - Online magazine maker