Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
ተጨማሪ መግላጫ • 147
በሐዋርያትና በነቢያት መሰረት ላይ የተመሰረተች ናት። መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ምን ማለት እንደሆነ ለመተርጎም እንድንችል ማለትም እግዚአብሄር እኛን የመቤዠት የፍቅር ታሪክ ለአብርሃም እና ለአባቶች በሰጠው ቃልኪዳን ወሰጥ፣ በእስራኤል ቃል ኪዳኖች እና ልምምዶች ውስጥ እንዲሁም በነቢያት እንደተነበየው እና በሐዋርያት ምስክርነት እንደተብራራው በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ የሚደመደመው እንደሆነ በግልጽ አስቅምጦታል። 2. የቤተ-ክርስቲያን ጉባኤዎችና የሃይማኖት መግለጫዎች በተለይም የኒቂያው የሃይማኖት መግለጫ። ታላቁ የቤተ ክርስቲያን ትውፊት በተለይም የኒቂያው የሃይማኖት መግለጫ ልዩ ትኩረትን በመስጠት በጥንታዊ እና ባልተከፋፈለችው ቤተክርስትያን ውስጥ ታሪካዊው ቀጥተኛ ወይም ኦርቶዶክስ እምነት ምን እንደሚመስል እውነቶችን እና ወሰኖች ያስቀምጣል። ይህ የሃይማኖት መግለጫቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተቀመጡት የሐዋርያት ትምህርት ትርጓሜና ማብራሪያ ጋር ትክክለኛነት አለው። ምነም እንኳን የእምነት መሰረት ወይም ምንጭ ባይሆንም የቤተክርስቲያን ጉባኤዎቹ እና የሐይማኖት መግለጫዎጩ የትምህርቶቹ ማዕከላዊውን ነገር ይወክላሉ በተለይም ከአምስተኛው ክፍለ ዘመን በፊት የነበሩትን (በአጠቃላይ ሁሉም ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ ክርስቶስ እና ስለ ድነት መሠረታዊ የሆኑ ዶክትሪኖች በዋናነት ያካትታሉ) 6 3. ጥንታዊ የእምነት መመሪያ። ታላቁ ትውፊት የክርስትና እምነት ዋናውን ነገር አቅፎ የያዘ ነው፤ ማለትም የጥንታዊ የእምነት ህግጋት ተደርጎ ይወሰዳል ይህም የመጽሐፍ ቅዱስ እምነት ትርጓሜ የሚሰጠውን መግላጫ እና አስተያየት የሚገመገምበት መለኪያ ተደርጎ ይወሰድ ነበር። ይህ ደንብ በአክብሮትና በታማኝነት ሲተገበር የጥንታዊቷ እና ያልተከፋፈለችው ቤተክርስቲያን የእምነቷ ማዕከል ምን እንደሚመሰል እንድናይ ይረዳናል። ይህንንም የሌሬንሱ ቪንሰንት በጽሁፋቸው ውስጥ ስለሚሰጡት መመሪያ እና አባባል በግልጽ እንዲህ ብለዋል “ ሁልጊዜ በየትኛውም ቦታ እና በሁሉም በሁሉም የታመነ”7 በማለት ገልጾታል። 6 ምንም እንኳን ሰባቱ የቤተ ክርስቲያን ጉባኤዎች (ከሌሎች ጋር ተደምረው) በካቶሊክና በኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያኖች ዘንድ እንደ ጽኑ ማሰሪያ በአጽንዖት የተረጋገጡ ቢሆንም ጥንታዊ እና ያልተከፋፈሉ አብያተክርስቲያናት እጅግ ወሳኝ እና በጣም አስፈላጊ የሆኑት ጉባኤዎች ተብለው የሚወሰዱ የመጀመሪያዎቹ አራት ጉባኤዎች ናቸው። እኔን ጨምሮ እጅግ በርካታ ሰዎች ይህ ትክክል እንደሆነ በማመን በአጽንዎት እንከራከራለን ምክንያቱም እነዚህ የመጀመሪያዎቹ አራት የቤተ ክርስቲያን ጉባኤዎች የእምነታችን አዕማድ የሆኑትን ትምህርተ-ሥላሴን እና ትምህርተ-ስጋዌን በጥልቀት እና በጽኑ መሰረት ላይ እንዲመሰረት አድርገዋል(ፊሊፕ ሻፍ የቤተክርስቲያን ጉባኤዎች ቁ. 1. ግራንድ ራፒድስ ቤከር የመጽሐፍ ቅዱስ ቤት, 1996, ገጽ 44)። በተመሳሳይም እነዚያ ልዑላን የተሃድሶ አራማጆች እንኳ የታላቁን የቤተ ክርስቲያን ትውፊትን አስተምህሮ በመቀበል እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆኑትን የሃይማኖት የእምነት መግለጫ እንደ ባለስልጣን አድርገው ተቀብለውት ነበር። ከዚህ ጋር በሚመሳሰል ካልቪን በራሱ ሥነ-መለኮታዊ ትርጓሜዎች እንዲህ በማለት መከራከሪያውን አቅርቧል “እነዚህ የቤተክርስቲያን ጉባኤዎቹ ግርማ የተላበሱ ናቸው ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉም ትምህርቶችን እና ልምምዶችን የሚለካና የሚያስገዛ ሆኖ ከፍ ባለ ስፍራ ተለይቶ መታየት ወይም መቀመጥ ይኖርበታል። በዚህ መንገድ የመጀመሪያዎቹ የቤተ ክርስቲያን ጉባኤዎች እንደ የኒቂያ ጉባኤ፣ ኮንስታንቲኖፕል፣ የመጀመሪያው የኤፌሶን ጉባኤ፣ የኬልቄዶን እና የመሳሰሉት በእምነታችን ላይ የተነሱትን የስህተት ትምህርቶችን በእግዚአብሄር ቃልመሰረትነት በማውገዝ ተመሳሳይነት አላቸው። እነዚህ የሃይማኖት መግለጫዎች ቅዱሳን አባቶች መጽሐፍ ቅዱስን በጥንካሬና በጥንቃቄ የተጠቀሙበት እና በወቅቱ የነበሩትን የሃይማኖትን ጠላቶች ለመደምሰስ ከቅዱስ ቃሉ ንጹህና እውነተኛ ይዘት በስተቀር ምንም አይቀበሉም። “(ጆን ካልቪን የክርስትና ሃይማኖት ተቋም, IV, ix. ጆን ቲ. ማክኔይል / Ed. Ford Lewis Battles / ፊላደልፊያ: ዌስትሚንስተፕ ፕሬስ, 1960, pp. 1171-72)። 7 ይህ መመሪያ ለትክክለኛ የክርስትና እውነት ተምሳሌታዊው የስነመለኮት መለኪያ ሆኖ በዘመናት መካከል ሞገስን እና ተቀባይነትን ያገኘ ሲሆን ሶስት የአስፈላጊ ግምገማ ገጾችን ይይዛል ይህም የትኞቹ አስተምህሮዎች በቀጥተኛይቱ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገቡትን ለመወሰን ወይም ላለማስገባት ያገለግላል። ቅዱስ ቪንሰንት ሎሬንስ የተባለ ከ450 ዓ.ም. በፊት የሞተ የሥነ መለኮት ተንታኝ “የቪንሲያን ካኖን” የሦስትዮሽነት የካቶሊክ ቅኝት “ በሁሉም ስፍራ፣ ሁልጊዜ እና በሁሉም የታመነ) የሚል አውጥቶ ነበር። በዚህ ሶስትዮሽ መለኪያ መሰረት ማለትም የአንድነት፣ የጥንታዊነት እና ስምምነት መለኪያዎች ቤተክርስቲያን በእውነተኛና በሐሰተኛ ትምህርቶች መካከል ያለውን ልዩነት ልትገነዘብ ትችላለች። “(ቶማስ ኦውደን, ክላሲካል ፓስቶሪ Care, ቅጽ 4) ግራንድ ራፒስስ: ቤከር ቡክስ 1987, ፒ 243). 5 ለቀድሞው ዶ/ር ኢ. ዌበር በክርስትና እምነት ምንጭና ዋና ነገር እና በትርጓሜው መካከል ያለውን ልዩነት በግልጽ ለያይቶ በማስቀመጡ ስላገኘነው ጠቀሜታ ከፍ ያለ ውለታ አለብኝ።
Made with FlippingBook - Online magazine maker