Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

ተጨማሪ መግላጫ • 149

በመሆን ቤተክርስቲያን በሐዋርያት በኩል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የተላለፈውን እምነቷን በግልፅ ለመግለጥ እና ለቤተክርስቲያን ለመከላከል ስልጣን ተሰጥቷታል።

መደምደሚያ-እንደገና ወደኋላ በመመልከት የወደፊቱን መፈለግ ብዙ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር በመናገር በሚሰማው ሁካታ ውስጥ ግራ በተጋቡበት ጊዜያት የእምነታችንን መሠረት ዳግመኛ ለማግኘት የክርስትናን ንቅናቄ እንደገና ለመጀመርና ለመለማመድ እና ለመመልከት በዕርግጥም እውነቱን በመናገር ዓአምን የለወጠውን ክርስቶስን በማምለክ እና የደቀመዝሙርነት ጅማሬ ማንነታችንን ለመመለስ እና ለማየት እንድንችል ለእኛ ምቹና ከፍ ያለ ጊዜ ነው። በእኔ አመለካከት ይህ ወሳኝ የሆነ ጉዞ ለታላቁ ትውፊት ጥልቅና ከፍተኛ በሆነ የጋለ ፍቅር፣ ለእነዚህ ትውፊቶች ሁሉ ማለትም የካቶሊክ የኦርቶዶክስ የአንግሊካን ወይም የፕሮቴስታንት እምነቶች ሁሉ ዋና በሆኑ እምነቶች እና ልምዶች መሰረት ላይ በመመስረትነው። እርግጥ ነው የተወሰኑ የቢተክርስቲአን ልማዶች በእውነተኛው አምልኮ በማስተማር እና በአገልግሎታቸው ለታላቁ ባለሥልጣን (ማለትም ለመጻህፍ ቅዱስ) እና ለታላቁ የቤተ ክርስቲያንትውፊት ያላቸውን ቁርጠኝነት ለመግለፅ እና ለመኖር መፈለጋቸውን ይቀጥላሉ። የእኛ የተለያዩ የክርስትና ትውፊቶች (ትንሹ ‘ቲ’) በመጽሓፍ ቅዱስ መሰረት ላይ የተመሰርቱ እና የመጽሐፍ ቅዱስን አስተምህሮ የሚገልጡ ከሆነ እና በመንፈስ ቅዱስ የሚመሩ ሲሆኑ የጌታ ኢየሱስን ወንጌል በአዲስ ባህሎች ወይም ንኡስ ባህሎች ውስጥ ግልፅ ማድረግን ይቀጥላሉ፤ በሚያጋጥሟቸውም ብቸኛ ሁኔታዎች የራሳቸውን ጥያቄዎች በመመልስና የተለየ ቅርጽ በመስጠት ስለ ክርስቶስ ተስፍን በመስጠት ወደ አዲስ ሁኔታዎች ያሸጋገራሉ። የእኛ ትውፊቶች በዋነኝነት የአውዳዊ ሁኔታ እንቅስቃሴዎች ናቸው ማለትም እነሱ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነት እንዲኖራቸው በሚያስችል መንገድ ህዝቡን በታማኝነት እና በታቀደው መንገድ ወደ ክርስቶስ ለመምራት ነው። ስለዚህ የዘመናዊ እምነታችንን እና ትውፊቶቻችንን ከትላቁ የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ጋር በማጣመር እና በማዋሃድ የዛሬዎቹን ባሕሎች ለማጎልበት መንገድን መፈለግ ይገባናል። የክርስትና ዋናው ነጥብ በታሪክ ውስጥ የእግዚአብሔርን የማዳን ሥራዎች ታማኝ ምስክር አድርጎ ማቅረብ እንደሆነ ፈጽሞ አንዘንጋ። እንደዚሁም ሁሌም መጭው ዘመናችንን ብሩህ ለማደርግ ወደኋላ መለስ በማለት የእግዚአብሄር ገዢ በስጋዌ ፣ በፍቅር ፣ በትንሣኤ ፣ በእርገት፣ እና በቅርቡ ዳግም በሚመጣው በክርስቶስ መገለጥ ላይ የተመሰረትን ሰዎች መሆን አለብን። በመሆኑም ከዛ ባዶ መቃብር ጠዋት ላይ አማኞች የሰሙትን የምስራች ወንጌል መልእክት ይህም በአዲስ ኪዳን የናዝሬቱ ኢየሱስ ለራሱ ህዝቡን እንዲታደግና እንዲያድናቸው ቃል የገባው የመዳን ታሪክ የምናስታውስ፣ የምናውጅ፣ በፍቅርና በሃይል የምንመሰክር ሁልጊዜም በእርሱ የምንታደስ እንሁን።

Made with FlippingBook - Online magazine maker