Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
160 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
ተጨማሪ አባሪ 24 የኒቂያ የሐይማኖት መግለጫ
እኛ ሁሉን በሚችል ሰማይንና ምድርን እና ሁሉንም ነገር የሚታየውን እና የማይታዩትን በፈጠረ ሁሉን ቻይ በሆነ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን
ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን። ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ እውነተኛ አምላክ የተፈጠረ ያይደለ የተወለደ በመልኮቱ ከአብ ጋር የሚተካከል ሁሉም በእርሱ የሆነ ያለ እርሱ ግን አንዳች የሚሆን በሌለ በእርሱ እናምናለን። ስለ እኛ ስለ ሰው ልጆች ስለ መዳናችን ከሰማይ ወረድ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ከቅድስት ድንግል ማሪያም ፈጽሞ ሰው ሆነ። ሰው ሆኖ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን ስለ እኛ ተሰቀለ መከራን ተቀበለ ሞተ ተቀበረ። በሶስተኛውም ቀን ከሙታን ተነሳ በቅዱሳት መፃሕፍት እንደተፃፈ በክብር ወደ ሰማይ ዓረገ በአባቱም ቅኝ ተቀመጠ። ዳግመኛም በህያዋን እና በሙታን ላይ ሊፈርድ በክብር ይመለሳል ለመንግስቱም ፍጻሜ በሌለው በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን።
ደግሞም ህይውትን በሚሰጥ ከአብና ከወልድ በሰረጸ፤ ከአብና ከወልድ ጋር በከበረና በሚመለክ በነብያትም በተናገር በእግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ እናምናለን
በአንዲት ቅደስት ካቶሊካዊት እና ሐዋሪያዊት በሆነች ቤተ ክርስቲያን እናምናለን.
ኃጢአትን በምታስተሰርይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን፤ የሙታንን ትንሳኤ የሚመጣውንም የዘለዓለሙን ህይወት ተስፋ እናደርጋለን። አሜን።
Made with FlippingBook - Online magazine maker