Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

ተጨማሪ መግላጫ • 161

ተጫማሪ አባሪ 25 የኒቂያ የሐይማኖት መግለጫ ከመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ ጋርt የከተማ አገልግሎት ተቋም

በአንድ አምላክ እናምናለን (ዘዳ. 6፡4-5; ማር 12፡29; 1ኛ ቆሮ. 8፡6) ሁሉን ቻይ አብ (ዘፍ. 17፡1; ዳን. 4፡35; ማቴ. 6፡9; ኤፌ. 4፡6; ራዕ. 1.8) የሰማይና የምድር ፈጣሪ ነው (ዘፍ. 1፡1; ኢሳ. 40.28; ራዕ. 10.6) ደግሞም የሚታየውና የማይታየው ሁሉ (መዝ. 148; ሮሜ. 11.36; ራዕ. 4.11)

ዓለም ሳይፈጠር በፊት ከእግዚአብሄር አብ በተወለደው የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ ከእውነተኛ አምላክ የተግኘ አምላክ ከእውነተኛ ብርሃን የተገኘ እውነተኛ ብርሃን የተወለድ እንጂ ያልተፈጠረ ከእግዚአብሔር አብ ጋር አንድ ማንነት ባለው በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን (ዮሐ 1.1-2; 3.18; 8.58; 14.9-10; 20.28; ቆላl. 1.15, 17; ዕብ. 1.3-6) በእርሱም ሁሉ ነገር ተፈጥሮአል (ዮሐ 1.3; ቆላ. 1.16) እኛን ለማዳን ከሰማይ የወረደ በመንፈስ ቅዱስም ከድንግል ማርያም ሥጋ ተፀነሰ እና የሰው ልጅ በሆነ (ማቴ. 1.20-23; ዮሐ 1.14; 6.38; ሉቃ 19.10) ደግሞም በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን መከራን በተቀበል፣ በተሰቀለ፣ በተቀበረ (ማቴ. 27.1-2; ማር 15.24-39, 43-47; የሐዋ ሥራs 13.29; ሮሜ. 5.8; ዕብ. 2.10; 13.12) መጽሐፍ እንደሚል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን እንደተነሳ (ማር 16.5-7;ሉቃ 24.6-8; የሐዋ ሥራ 1.3; ሮሜ 6.9; 10.9; 2ጢሞ. 2.8) ወደ ሰማይ ባረገ በእግዚአብሄር አብም ቀኝ በተቀመጠ (ማር 16.19; ኤፌ. 1.19-20) ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ላይ ለመፍረድ በክብር በሚመጣ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም። (ኢሳ. 9.7; ማቴ. 24.30; ዮሐ 5.22; የሐዋ ስራ 1.11; 17.31; ሮሜ. 14.9; 2ኛ ቆሮ. 5.10; 2ኛ ጢሞ. 4.1) ደግሞም ህይወትን በሚሰጥ እና ጌታ በመንፈስ ቅዱስ (ዘፍ. 1.1-2; ኢዮብ 33.4; መዝ. 104.30; 139.7-8; ሉቃ 4.18-19; ዮሐ 3.5-6; የሐዋ ስራ 1.1-2; 1ኛ ቆሮ. 2.11; ራዕ. 3.22) ከአብንና ከወልድ በሚሰርጽ (ዮሐ 14.16-18, 26; 15.26; 20.22) ከአብንና ከወልድ ጋር በአንድነት የሚመለክ እና የሚከብር (ኢሳ. 6.3; ማቴ. 28.19; 2ኛ ቆሮ. 13.14; ራዕ. 4.8) በነብያትም በተናገረ (ዘኁ . 11.29; ሚኪ. 3.8;የሐዋ ሥራ 2.17-18; 2ኛ ጴጥ. 1.21)

በአንዲት ካቶሊካዊት እና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን

(ማቴ. 16.18; ኤፌ. 5.25-28; 1ኛ ቆሮ. 1.2; 10.17; 1ኛ ጢሞ. 3.15; ራዕ. 7.9)

የኀጢአት ስርየትን በሚሰጥ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን (የሐዋ ሥራ 22.16; 1ኛ ጴጥ. 3.21; ኤፌ. 4.4-5) በሙታን ትንሳኤ በዘላለም ህይወት እናምናለን። (ኢሳ. 11.6-10; ሚኪ. 4.1-7; ሉቃ 18.29-30; ራዕ. 21.1-5; 21.22-22.5) አሜን።

Made with FlippingBook - Online magazine maker