Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

መግቢያ

ደቀ መዝሙርነት የዕውቀት መግባባት ሳይሆን የህይወት ግንኙነት።

~ ጁዋን ካርሎስ ኦርቲስ

የእምነት አርበኞች ሆይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅና ብርቱ ስም ሰላም ለእናንተ ይሁን!

ወጣት ደቀ መዛሙርት /የክርስቶስ ተዋጊ/ ሆይ ይህንን መልካሙን የእምነት ገድል መጋደል— በእግዚያብሔር አስደናቂ ሥራ ውስጥ የእኛን ሚና መጫወት የተሰኘውን መጽሐፍ/ ሀብታችንን/ ለእናንተ በማቅረባችን ታላቅ ደስታ ይሰማናል። ይህ የመማሪያ መጽሐፍ የመጽሃፍ ቅዱስ ድራማ ወይም ታሪክ ማለትም እኛ በእግዚአብሔር ዓብይ ታሪካዊ ስራ ውስጥ ያለንን ቁልፍ ተሳትፎ ወይም ገጽታ ምን እንደሚል የተፃፈውን ንድፍ ያሳየናል። እኛ የዓለም እውነተኛ ታሪክ ዓላማና ፍፃሜ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግቧል የሚል ጽኑ እምነት አለን። መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን እንደ የሕይወት ምንጭ፣ አጽናፈ ዓለሙን የፈጠረ፣ የምድርን አህዛብን ሁሉ እንድሚባርክ ለዚህም የተባረከ አንድ ዘር እንደሚልክላቸው ለአብርሃም ቃል ኪዳንን እንደሰጠ እንደሚያሳይ ፅኑ እምነት አለን። እግዚአብሔር አምላክ ለሕዝቦቹ ማለትም የተቀባውን መሲሑ እንዲመጣ የተጠቀመበትን ለእስራኤል ህዝብ ራሱን ገለጠ። ጌታ ኢየሱስ ሞትን ለማሸነፍ፣ እርግማንን ለማጥፋት እና በሰው ልጆች መካከል የእሱን አገዛዝ ለመመስረት ወደ ዓለም የመጣ በእግዚአብሔር የተመረጠ አገልጋይ ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ መሲሁ በሕዝቡ /በእስራኤላውያኑ/ በኩል እንደመጣና እርሱ ማን እንደሆን እናውቃለን፤ የናዝሬቱ ኢየሱስ ቤዛ እና ንጉሥ ነው። ቅዱሳት መጻሕፍት ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር የእግዚአብሄር አብን ዕቅድ እና ክብር ለሰው ልጆች ሁሉ እንደገለጠ በመስቀል ላይ በመሞት እና ከሙታን በመነሳት ከኃጢአታችንም እንደተቤዠን፣ እንዲሁም በዳግመኛ ምፅዓቱ በቅርቡ ሁሉን እንደገና እንደሚያድስ ይናገራሉ። እኛ ንስሓ ስንገባ እና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ጌትነትነትና አዳኝነት ስናምን ይህ ታላቅ ታሪክ የእኛ የራሳችን ታሪክ ይሆናል። ይህም አስደናቂ የጸጋ እና የፍቅር ታሪክ፥እኛ እንድንካፈለው እና በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ ካሉት ቤተሰቦች/በቤተ ክርስቲያን/ ጋር ለመኖር የሚጋብዘን ድንቅ ታሪክ ነው። የትምህርቱ አጠቃላይ ዕይታ: መልካሙን የእምነት ገድል እንዴት መጋደል እንደሚቻል ይህ መጽሐፍ ለአንባቢዎች ግልጽ እና ቀላል በሆነ መንገድ የዘመናት ጥያቄ የሆነውን እና የእርሱን አጠቃላይ ማብራሪያ ጎላ ባለ መልኩ ለማስረዳትና ለማብራራት እንዲሁም ትምህርቱን ከራሳችሁ ጋር በማዛመድ ከእግዚአብሔር ጋር እና ከሌሎች ቅዱሳን ጋር በቤተ ክርስትያን እንዴት እንደምትኖሩ ለመርዳት የቀረበ ነው። ይህም መንፈሳዊ ረሃብን ለተራባችሁ እና እያደጋችሁ ላላችሁ ለእናንተ በእግዚአብሔር ታሪክ ውስጥ አዲስ ተዋናይ እንደሆነ ሰው እያንዳንዱን ትምህርት በጥንቃቄ በመረዳት እና በማዛመድ እንድትኖሩት ለማስቻል ይረዳ ዘንድ በተጠና መልኩ የተዋሃዱ ዘጠኝ ትምህርቶችን በማዋቀር የሚያብራራ ዘጠኝ ትምህርቶች ያካተተ ነው። ትምህርቶቹም ሐዋርያው ​ጳውሎስ በኤፌሶን መጽሐፍ ውስጥ የገለጻቸውን የከበሩ እውነታዎችን በመዘርዘርና በማብራራት እናንተን በመሰረታዊ የክርስትና እምነት እና ምልልስ ላይ መሰረት ለመስያዝ የተነደፈ ነው። የትምህርት ክፍለ ርዕሶቹ እና ስለ እያንዳንዱ ትምህርት የተሰጠው አጭር ማብራሪያ ከዚህ በታች ቀርቧል።

7

Made with FlippingBook - Online magazine maker