Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

ትምህርት 6 እኛ የምንፈልገው መታንጽ በክርስቶስ አካል ውስጥ እርስ በርስ መተናነጽ

አልኮል መጠጥን ለምሳሌ እንደ ወይን ጠጅ ዓይነቶችን አትጠጡ ምክኒያቱም ውርደትን* ያስከትላልና። ይልቁንም መንፈስ ይሙላባችሁ፤ በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ* እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ቅኔን ተቀኙና ዘምሩ። በርግጥ ሁልጊዜ ስለ ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንንና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ።እያንዳንዳችሁ ለሌላችሁ በክርስቶስ ፍርሃት የተገዛችሁ ሁኑ።

የሐዋርያው የጳውሎስ መልዕት (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፡ 18-21)

በዚህ ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ ይህን “እኛ የምንፈልገው መታንጽ” የሚለውን ሃሳብ የሚከተሉትን በማመን እንይዛለን • የክርስቲያን ሕይወት እንዲኖር የታሰበው አብሮ እንደሚኖር እንደ አንድ ማህበረሰብ፣ እንደ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ማለትም የክርስቶስ አካል እና የመንፈስ ቅዱስ ቤተመቅደስ አብረው እንደ አንድ ቤተሰብ እንዲያድጉ ነው። • በአጥቢያ ቤተክርስቲያን እና በትንንሽ ቡድኖች ከሌሎች አማኞች ጋር ስንገናኝ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ነገሮች እንማራለን፣ እግዚአብሔርን እናመልካለን እንዲሁም እንደ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት አብረን እናድጋለን። • ክርስቶስን እንደ ጌታ ስንከተል እኛ ለእያንዳንዳችን ለክርስቶስ ባለ ፍርሃት አንዳችን ለአንዳችን ስንገዝ በእምነታችን እየተገነባን (እየታነጽን) እንሄዳለን። ዘለዓማዊ አምላክ አባቴ ሆይ በቃልህ እንደተናገርክ አንተ የእውቀት እና የጥበብ ሁሉ ምንጭ ነህ። ይህም እውነት መሆኑን አምናለሁ አውጃለሁም፣ እናም ውድ አባቴ ሆይ የእውነትን ቃል በትክክለኛ መንገድ ማካፈል እንድችል መለኮታዊ ጥበብ እንድትሞላብኝ እጠይቃለሁ (2 ኛ ጢሞቴዎስ 2፡15)። እባክህ ውድ አባቴ ሆይ የምሄድበትን መንገድ ምራኝና አስተምርኝ (መዝሙር 32፡8) እርምጃዬንም አቅና። ድምፅህን ለመስማት ጆሮዬን አዘንብል አስተሳሰቤን እና ንግግሬን አቅና እናም ከስህተት በመመለስ በትክክለኛው መንገድ እንድሄድ ምራኝ።

ዓላማዎች

ለጥበብ የመግቢያ ጸሎት

አባት ሆይ የማስተዋል እና የመለየትን ስጦታን ስጠኝ እናም ቃልህን በምማርበት ጊዜ በእውነተኛውና በሃሰተኛው ትምህርቶች፣ መናፍስትና ጸጋዎች መካከል ያለውን ልዩነት እንድረዳ

*ውርደትን- ውርደት ወይም መሳለቂያ መሆን ማለት ከልክ ባለፈ ራስን ለመሳለቂያ በሚያድርግ በስጋዊ ደስታ መደሰት ማለት ነው። በርግጥ እኛ ደስታ የሚያስገኝልን ማንኛውንም ነገር ማስወገድ የለብንም፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን ከሚያሰድብና እንዝላልነት ከሞላው ደስታዎች መራቅ አለብን ማለት ነው። እግዚአብሔር ልንደሰትበት የሚያስችለንን ነገር ሁሉ ሰጥቶናል ሆኖም ግን ሁሉም ነገር የራሱ ገደብ አለው። ለምሳሌ ወንዞቹ በዳርቻቸው ወይም በገደባቸው ውስጥ በሚፈስሱበት ጊዜ ኃይለኛ የሆን ጠቃሚ ኃይል ነው፤ ነገር ግን ወንዞቹ ገደባቸውን አልፈውእና ጎርፍዎችን ሞልተው ወደ ከተማ በሚፈሱበት ጊዜ ወንዙ ከፍተኛ ጥፋትን የሚያስከትል ኃይለኛ አጥፊ ኃይል ይሆናል። በተመሳሳይም ከልክ በላይ በመጠጣት መጎሳቆል ማለትም እግዚአብሔር የሰጣቸውን ደስታን አላግባብ መጠቀም ገደቦቹን ጥሰው ለግለሰብ እና ለሌሎች ሁሉ አጥፊ ይሆናል። * በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ - መዝሙሮች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ የዝማሬ ግጥሞች በክርስትያኖች ዘንድም እግዚአብሄርን ለማምለክ የሚያገለግሉ የአምልኮ መግለጫዎች ናቸው። ዝማሬና መንፈሳዊ ቅኔዎች በሁለቱም በመጽሐፍ ቅዱስም በክርስትያኖች የተጻፉ የፍቅር እና የአምልኮ መግለጫዎች ናቸው።

73

Made with FlippingBook - Online magazine maker