Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

74 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ

እርዳኝ። በመንፈስ ቅዱስህ ፈቃድህን አሳየኝ ፈቃድህንም በሙሉ ልቤ መቀበልና መያዝ እንድችል ማስተዋልን ስጠኝ።

የተከበርክ ጌታ ሆይ እባክህን ለመስማት እና ለማዳመ የፈጠንሁ ፤ ለመናገርና ለቁጣ ግን የዘገየሁ እንድሆን እርዳኝ (ያዕቆብ 1፡19)። የአፌም ቃልና የልቤ ሃሳብ በአንተ ዘንድ ተቀባይነት ይኑራቸው። ሰው ሁሉ እውነትህ ሊረዳና ሊያተርፍበት እንዲችል እውነትህን የምናገርበትን ጥበብን ሥጠኝ።

በዚህ ጥናት ቃልህንና መመሪያህን እንድቀበል አስተምረኝ። ይህንን ሁሉ ጌታዬና አዳኜ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ብርቱ ስም እጠይቃለሁ አሜን።

1. “ከዚህ በፊት ባጋጠሙኝ መጥፎ ሁኔታዎች የተነሳ ወደ አንድ ቤተ ክርስቲያን መሄድ አልችልም።” በአጋጣሚ ብዙ ሰዎች ወደ ቤተክርስቲያን ሄደውና ተካፍለው ከሌሎች ጋር ባላቸው ግንኙንት በተፈጠረ መጥፎ አጋጣሚዎች በጉዳት ውስጥ ይገኛሉ። ችግሩ ምንም ይሁን ምን - ይቅር ያለማለት፣ ማጉረምረም እና ቅናት፤ አለመግባባትና ጉዳት - ወደ ሌላ ግንኙነት ለመሄድ እና አዲስና ትኩስ ግንኙነትን እንዳይመሰርቱ መንገዳቸውን “ይዘጋዋል”። አሁን በምታውቁት ላይ በመመስረት አንድ አዲስ አማኝ በተለይም በሌላ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አስከፊ ሁኔታ አጋጥሟቸው እንደነበረ ካወቃችሁ እንደነዚህ ዓይነት ሰዎችን አሁን በዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥ በክርስቶስ ለማደግ እንዲችሉ እንዴት መርዳት ይችላሉ? ነው! “ መጽሐፍ ቅዱስ በሁለት ኪዳኖች የተከፈለ ማለትም የብሉይ ኪዳን (የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት፣ 39 መጻሕፍት ከዘፍጥረት እስከ ሚልክያስ) እና የክርስቲያናዊ አዲስ ኪዳን (ከማቴዎስ እስክ ራዕይ 27 መጻሕፍት) እንደሆነ ታውቁ ይሆናል። ነገር ግን ምናልባት እናንተ ልታውቁት የማትችሉት ነገር ቢኖር መጽሐፍ ቅዱስ የመጻሕፍት ቤተመፃህፍት ቢሆንም መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ለፍጥረታቱና ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር የሚገልጽ ወጥነት ያለው አንድ ታሪክና ድራማ ብቻ መሆኑን ነው። እግዚአብሄር ለአጽናፈ ዓለፈ ዓለሙ እና ለሰው ልጆች ባለው ታላቅ ፍቅር እና ቁርጠኝነት ምክንያት ብቻ ነው ለመዳን የምንችለው። በዚህ ረገድ ክርስትና ከሌሎች እምነቶች ሁሉ ይለያል። እንደ እውነቱ ከሆነ ሃይማኖቶች ወደ ፍጽምና ደረጃ ለመድረስ፣ በረከትን ለመውረስ፣ ለመለወጥ ወይም ጥበቃ ለማግኘት ሲሉ መከተል ያለባቸው አድርጉና አታድርጉ በተባሉ ህግጋቶችና መመሪያዎች፣ ስርዓቶች ወይም ቀኖናዎች ላይ ያተኩራሉ። ክርስትና ግን እግዚአብሔር ለሰዎች ባይገባቸውም፣ እነርሱ ባይጠይቁትም፣ በየትኛውም ዋጋ ሊያገኙት የማይችሉትን ድኅነትን እንደሰጠ የሚያሳይ መጽሐፍ ነው። ሰዎች የዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ መሰረታዊ መልዕክት ማግኘት በጣም ከባድ የሆነባቸው ለምን እንደሆነ ያስባሉ? እነርሱ ምንም ይሁኑ ምን፣ ምንም ያድርጉ ወይም ማንም ይሁኑ ማን ለእነርሱ የተገልጸውን “የእግዚአብሔር ጸጋ” የእርሱ ንጉሣዊ ፍቅር እና ምህረት እንዳይረዱና እንዳያዩ ምን ሊጋርድባቸው ይችላል ብለው ያስባሉ? 3. “ፓስተራችን እነዚህን ሁሉ ሰዎች እንዴት ይመራቸዋል? እሱን ፈጽሞ አላውቀውም!” እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ ደግሞ ደጋግሞ ከሚናገራቸው ነገሮች አንዱ ለእኛ የሰጣቸውን ታማኝ እና መንፈሳዊ ለሆኑት መጋቢዎች እና መሪዎች ትምህርት እና ምሳሌያዊ ህይወታቸውን ስንከተል የምናድግ መሆናችንን ነው። ነገር ግን በአንዳንድ አብያተ-ክርስቲያናት ዘንድ መጋቢው ምናልባትም በመቶዎች ወይም በሺዎች የሚቆጠሩ አማኞችን እየመራ ነው። በመሆኑም በቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙ አማኞች እንደመኖራቸው እና ፓስተሮቹም እጅግ ብዙ ሃላፊንቶችን ከመሸከማቸው የተነሳ ብዙ ባለትዳሮች እና ቤተሰቦች እንዲሁም ግለሰቦች 2. “መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ፍጥረታቱንና የሰው ዘርን በሙሉ ለማዳን አንድ ወጥነት ያለው መጽሐፍ መሆኑ እጅግ ያስደንቀኛል! ሰው ሆይ እኛ የምናገለግለው እንዴት ያለ አፍቃሪ አምላክ

ማዛመድ

Made with FlippingBook - Online magazine maker