Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

ትምህርት 6 እኛ የምንፈልገው መታንጽ • 75

ፓስተሩን በቅርብ ለማወቅ ያላቸው አጋጣሚ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል ስለዚህም በርካታ ቅሬታቸውን ይገልጻሉ። አንድ አዲስ አማኝ “ፓስተራችሁ ደህና አድርጎ ማወቅ ከእርሱ እረኝነት ስር የመሆን ምልክት ከሆነ ምናልባትም እኔ ፓስተር በጭራሽ የለኝም” በማለት ገልጿል። “ፓስተራችን እነዚህን ሁሉ ሰዎች እንዴት ይመራቸዋል። እሱን ፈጽሞ አላውቀውም! “ ይህን ወጣት አማኝ በእረኝነት እንክብካቤ ውስጥ መኖር ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዲረዳ እንዴት ሊያስረዱትና ሊያበረታቱት ይችላሉ - በዛሬዋ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥስ ይህ እንዴት ሊከናወን ይችላል? በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ (እኛ ስለ ምናሳየው ልቀት) ክርስቶስ እንደተወደዱ ልጆች እንደ እግዚአብሄር ቅዱሳን እና የክርስቶስ አምባሳደሮች በመሆን ለወደቀው ዓለም እርሱን እንደምንወክል ተመልክተናል። አሁን ደግሞ በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ በደጋግ መጋቢዎች ሥልጣን ስር በመሆን እና በእውነተኛ ፍቅር እርስ በእርስ በመታዘዝ በእምነታችን እንዴት ማደግ እንደምንችልና መልካሙንም የእምነት ገድል እንዴት እንድምንጋደል የሚያስችለንን የእግዚአብሄርን ሃሳብ እንመለከታለን ጌታ ኢየሱስ የእርሱ የሆኑት ህዝቦቹ እንደ እርሱ ማህበረሰብ ሲኖሩ እርስ በርስ እንዲዋሃዱ እና አንዳቸው ለሌላቸው የተሰጡ እንዲሆኑ ይፈልጋል። በየሳምንቱ ለአምልኮ እና እርስ በራስ ለመተናነጽና ለማደግ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ወይም በትናንሽ ቡድኖች ውስጥ በአንድ ላይ እንሰባሰባለን። በዚህ ህብረት ውስጥ ሌሎች አማኞችን ለማወቅ እና እኛንም እንዲያውቁን መፈቀድ አለብን። ወደቤታችን መጋበዝን እና እርስ በእርስ ዘና ብለን እና አብረን መጫወትንና መተናነጽን እንዲሁም ክርስቶስን ስንከተል እርስ በራስ ለመበረታታት የተቻለንን ማድረግን መማር አለብን። እንደ አማኞች እኛ የተጠራነው በስጦታውቻችን በፍቅራችን በህብረታችን እና በመልካም ጠባያችን እርስ በእርስ በመተናነጽ ሕይወት ለመኖር ነው። በተጨማሪም እርስ በርስ ለመዋደድ እና መልካም ተግባሮችን ለመስራት መወቃቀስን እና በእምነት በእግዚአብሔር የክርስቶስ ህዝብ ከመሆናችን አንፃር ጥንት ወደ ጌታ ከመምጣታችን በፊት የነበሩንን መጥፎ ወይም ክፉ ነገሮችን ለመተው እርስ በርስ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ መተራረም አለብን። ምንም እንኳን ሁላችንም ክፉን ለማድረግ በየጊዜው ብንፈተንም፤ በክርስቲያን ማኅበረሰብ ውስጥ ሐዋርያት ለክርስቲያኖች በጻፏቸው ደብዳቤ ውስጥ እንደጠቀሱ ለዓለማዊነት ሕይወት- ማለትም እንደ ጾታዊ ብልግና፣, ርኩሰት፣ ልቅነትን፣ ምግባረ ብልሹነትን፣ ክፉ ምኞቶች፣ ስግብግብነትና ከመሳሰሉትን ነገሮች ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ሊኖራቸው አይገባም። እንደ እውነቱ ከሆነ ራሳችንን ሊያንጹን ከማይችሉ ከማናቸውም ነገሮች(ማለትም መንፈሳዊ ጉዞአችንን ከሚያጠፉ ማናቸውም ነገሮች) እነዚህም እንደ ቁጣ፣ ንዴት፣ ሐሜት፣ ስም ማጥፋት እና የማይገቡ ንግግሮች ማስወገድ ይጠበቅብናል። በመጨረሻው ትምህርት ውስጥ እንደተማርነው እኛ በእውነት የእግዚያብሔር ቅዱሳን እንደሆንን እናም በምንሄደበት ስፍራ ሁሉ ለክርስቶስ አምባሳደሮች እንድንሆን ተጠርተናል። በመሆኑም አሁን እኛ የምንኖረው ሌሎችን ለመገንባት እንጂ እነርሱን ለማሰናከል አልያም ለክርስቶስ ባላቸው ፍቅር ላይ እንዳይሰናከሉ መሆን ይገባዋል። በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ስንጸልይ ወንድሞችን በፍቅር ለመጋፈጥ እና እርስ በራስ ለመበረታታት፤ እንዲሁም መንፈሳዊ መሪዎቻችን በትምህርታችውና ምሳሌያዊ በሆን በመልካም አኗኗራቸው ለሚያሳዩን አመራር ለመመራት ተጠርተናል። እንደ እግዚአብሔር የተመረጠ ሕዝቦች እርስ በርሳችን ለመዋደድ እና አዳዲስ የአኗኗርና የአስተሳሰብ መንገዶች ለማዳበር፣ ርህራሄን፣ ደግነትን፣ ትህትናን፣ የዋህነትን እና ትዕግስት እንዴት እንደሚኖር ለመማር እንጥራለን። ከሁሉም በላይ ለሰዎች ያለን

ይዘት

Made with FlippingBook - Online magazine maker