Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
76 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
ፍቅር ከሌሎች ጋር ያለንን ግንኙነት የሚያሳይ መሆን አለበት። ይህን በማድረግ በሁሉም ነገሮች ክርስቶስን ለማስደሰት እንቀርባለን ማለት ነው።
እኛ የምንሻው መታነጽ ትምህርት 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ያንብቡ እና ከእያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ጋር የተያያዙትን ጥያቄዎች አጠር ያለ መልስ ይስጡ። 1. የእግዚአብሔር ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ ወይም በቅዱሳን ጽሑፎች እንደተነገረው የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ሥራን ያካትታል። በክርስቶስ አማኞች እንደመሆናችን መጠን የዚህ ታሪክ ሰዎች ነን-ስለዚህ ታላቅ ሥራ በ”ስለ ሥነ-መለኮት” ትምህርታችን ውስጥ እናስባለን፣ ስለ እርሱ በአምልኮአችን ውስጥ በዝማሬያችና በስብከታችን እንናገራለን በደቀ መዛሙርትነት ትምህርታችን ውስጥ ማንነታችን ተቀርጾበታል እንዲሁም በምሥክርነታችን ስለዚህ ጉዳይ ለሌሎች እንናገራለን። የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብብ ተጨማሪ ማብራሪያ “የእግዚአብሔር ታሪክ: የእኛ ቅዱስ ስነ-ስርአቶች” የሚለውን ተመልከቱ እና ከዚህ በታች ካለው ጋር ተያይዘው ለሚወጡት ጥያቄዎች መልስ ይስጡ።
የእኛ ዋነኛ መሠረት -የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ፍቅር ነው
ሀ. በዮሐንስ 3:15-18 መሰረት- በፍጥረት የማዳን እና የመታደግ ታሪክ ውስጥ አብ ምን ሚና ተጫውቷል?
ለ. በ2 ቆሮ 5፡18-21 ውስጥ- በመዳናችን ታሪክ ውስጥ ኢየሱስ ምን ሚና ተጫውቷል?
ሐ. በኤፌ. 1፡13-14. መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ታሪክ ተግባራዊ እንድናደርግ በመርዳት ምን ሚና አለው?
መ. በ2ኛ ጢሞ 3፡15-17- መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክን ሥራ ለመረዳት እንድንችል የሚረዳን እንዴት ነው?
የእኛ የግል ምላሽ : ድነት በጸጋ በኩል በእምነት ነው
ሠ. በሮሜ 10፡9-10 መሰረት እኛ አማኞች ማለትም ቤተክርስቲያን ለዚህ ታሪክ የመጀመሪያው ምላሽን እንዴት እንሰጣለን?
ረ. በ1ጴጥ 2፡8-9 መሰረት የአምልኮአችን ግብ ምንድን ነው - በክርስቶስ ውስጥ ቀዳሚ ዓላማችን ምንድነው?
ሰ. በቆላ 2፡6-10 መሰረት እኛ በታሪኩ ውስጥ እንዴት እንሠራለን - ማንን ወይም በምን ላይ እናተኩራለን?
ሸ. በማቴ 28፡18-20 መሰረት ቤተክርስቲያን በዓለም ላይ ስትኖር ክርስቶስ ምን ትእዛዝ ሰጥቷታል?
Made with FlippingBook - Online magazine maker