Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
ትምህርት 6 እኛ የምንፈልገው መታንጽ • 77
2. በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባለን ሙሉ የእምነት ዋስትና እና በእግዚአብሔር የመታደግ ተስፋችን እርግጠኝነት ሌሎች አማኞችን ለማበረታታት እና ለማነጽ ተግባራዊ መንገዶችን መፈለግ ይገባናል። ዕብራውያን 10፡19-25ን አንብብና ባዶ ቦታዎቹን ሙላ:
ሀ. __________________ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ (ቁ. 24)
ለ. በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ _______________________________________ አንተው (ቁ. 25)
ሐ. እርስ በርሳችን _________________________________________________፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ። (ቁ.25)
3. በክርስቶስ ጸጋ ስለዳንን በአዲስ ታሪክ ወስጥ አዲስ ማንነት ይዘን አዲሱን ፍጻሜያችንን እንጠባበቃለን። ስለሆነም አማኞች ጌታን የማያውቁትን የአኗኗር ዘይቤ መከተል የለባቸውም ይልቁንም በክርስቶስ እንደተዋጁ ሰዎች በመልካም አኗኗርን መነሮ አለባቸው። 1ኛ ጴጥሮስ 4፡ 1-11ን አንብቡ እና ጴጥሮስ እግዚአብሔር እንደመረጣቸው አማኞች ማድርግ ያለባቸውን አራት ተግባሮች ጻፍ።
ሀ.
ለ.
ሐ.
መ.
4. ከሌሎቹ አማኞች የምንገናኝበት መንገድ ክርስቶስ ለእኛ ድነታችንን ለማሸነፍ ያሳየንን ትሕትናን ማንጸባረቅ ይኖርበታል። ፊልጵስዩስ ምዕራፍ 2፡1-11ን አንብብ እና ጳውሎስ ትህትና ምን መምስል እንዳለበት የተናገረውን ጻፍ?
5. ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ የሰጠው አዲስ ትእዛዝ እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ማለትም እርስ በራሳችን ሕይወታችንን ለሌላው መስዋዕት አድርገን ማቅረብ ነው። 1 ዮሐንስ 3፡11-18ን አንብብና የሚከተሉትን ሐረጎች ከተጓዳኙ እውነት ጋር ያዛምዱ።
ሀ. ይህ የሰማችሁት መልእክት
______ እርስ በርስ መዋደድ አለብን
ለ. አትጨነቁ
______ ኢየሱስ ሕይወቱን ለእኛ ሲል ሰጥቷል
ሐ. ከሞት ወደ ህይወት እንደተሸጋገርን እናውቃለን ______ በተግባር እና በእውነት
መ. በዚህ ፍቅር ምን እንደሆነ እናውቃለን
______ ወንድሞቻችንን ስለምንወዳቸው
Made with FlippingBook - Online magazine maker