Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

ትምህርት 6 እኛ የምንፈልገው መታንጽ • 83

ከሚወዱና ደስ ሊያሰኙህ ከሚፈልጉ ሌሎች ቅዱሳን ሁሉ እርዳታ ውጭ ስላላደረግከው አመሰግንሃለው። በአጥቢያ ቤተክርስትያን ውስጥ ህዝብህን ስለምትገነባበት መንገድ፣ ቅዱስ ፈቃድህን እንድንረዳና እንድናደርግ የሚረዱኝን ምሳሌ በመሆን እንዲያስተምሩኝና እንዲመግቡኝ ስለሰጠኽኝ መሪዎች እና መጋቢዎች አመሰግንሃለሁ። ከሌሎች ጋር በትዕግስት እንድኖር፣ ከእነሱ ለመማር እና የእነሱን ትችትና ምክር ለመስማት እንድችል ጸጋን አብዛልኝ። እነርሱን ከእኔ ለመለየት፣ ከእነሱ ለመደበቅ ወይም ለመለየት የሚሰማኝን ማንኛውንም ዝንባሌን ለማሸነፍ እንድችል እርዳኝ፤ እኔ እንድሆን የምትፈልገውን እንድሆን እነርሱ ያስፈልጉኛልና ስለዚህ ከሌሎች ጋር ለመቆራኘት እንድችል ድፍረትን፣ እና ሁልጊዜ ከእነሱ ጋር መሰብሰብን ላለመተው እና ችላ ላለማለት እንድችል እርዳኝ። በመሪዎቼ አስተምረኝ እንዲሁም በእምነት ባልንጀሮቼ በሆኑት ቅዱሳን አበረታታኝ እና ገስጸኝ። ይህን በምታደርግበት ጊዜ ልጅህ በብስለት እንደማድግ አውቃለሁና። አባት ሆይ ስለህዝብህ ስጦታ አመሰግናለሁ። በኢየሱስ ስም እፀልያለሁ አሜን!

At www.tumi.org/sacredroots, we have a section dedicated to additional written and video resources.

ለተጨማሪ ጥናት

Don L. Davis. Sacred Roots: A Primer on Retrieving the Great Tradition . Wichita, KS: The Urban Ministry Institute, 2010.

በቀጣዩ ክፍለ ጊዜ እነዚህን አርዕስቶች ጨምሮ ስለ ምንዋጋው ጠላት ትማራለህ 1. ከሥጋና ከደም ጋር እንጋደልም 2. ጠላታችን ዲያብሎስ በወደቀው ዓለም እና በሥጋ ምኞቶች በመጠቀም ይሰራል 3. ጠላት እኛን ተስፋ ለማስቆረጥ እና ትኩረትን እንድናስጠው የሱን ሴራ የሚያስፈጽሙ ተከታዮቹን ያሰማራል።

ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ

ዮሐንስ 13፡35

የመጻሕፍ ቅዱስ ጥቅስ ጥናት

1. ሁለት በእምነት የጎለመሱ ክርስቲያኖችን አግኝና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከሌሎች ቅዱሳን በሚያገኙት ምክር አማካይነት ከእግዚአብሔር መመሪያን ለመቀበል ስላላቸው ልምድ እንዲያካፈሉህ ጠይቃቸው። ከሌሎች አማኞች ምክር ባለመጠየቃቸውም ምክንያት ምን ስህተቶችን እንደሰሩ ጠይቃቸው። 2. እስካሁን ድረስ ካላደረጋችሁት በሚቀጥለው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ በአንድ ቤተ ክርስቲያን በቋሚነት ለመከታተል፣ ህብረት መጀመር የምትችሉበት ቦታ እና በቤተክርሰቲያ አባል እንድትሆኑ እግዚአብሔር የሚፈልጋችሁ ቦታ ከሆነ ለመምረጥ ይወስኑ። ያስታውሱ በአጥቢያ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ካልሆኑ በአምላካዊ የእረኝነት አመራር ስር ካልሆናችሁ ልትታነጹ (ወይም ሌሎችን ለማነጽ) አይችሉም። 3. መመሪያ የሚፈልጉባቸ ጉዳዮችን በዝርዝር ያዘጋጁ። በነዚህ ጉዳዮች ለአንድ ሳምንት ያህል እግዚአብሔር በቃሉ እና በሌሎች አማኞች አማካይነት እንዲመራዎት በየዕለቱ ጸልዩ። 4. ዝርዝሮችዎን ለማጋራት እና ምክሮቻቸውን እንዲጠይቁ ሁለት የጎለመሱ አማኞችን ፈልጉ።

የቤት ስራ

Made with FlippingBook - Online magazine maker