Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
82 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
በእግዚአብሔር ዕቅድ መሰረት መጽሃፍ ቅዱሳዊው ክርስትና በባህሪው ሁሉዓቀፋዊ ነው፤ የማንኛውንም ባሕል ማንነት መውሰድ ይችላል። ይህን የወንጌል ዓለም አቀፍነት በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ እናያለን። የበዓለ አምሳ ቀን ወንጌል በሁሉም የዓለም ቋንቋዎች በተሰበከበት ወቅት የክርስቲያን ወንጌል ወደ አንድ የተለየ ባህል ወይም ቋንቋ የተዘጋ እንዳልሆነ ግልጽ ማስረጃ ነው። ይህ ዓለም አቀፋዊነት በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን በአይሁድና በግሪኮች ባሕል ውስጥ እንደተነገረ እና እንደተዋሃደ እናያለን። የቤተክርስቲያን ጥሪ ሁሉንም ህዝቦች፣ እያንዳንዱን ባህል፣ በደኅንነት መልዕክት አማካኝነት በመግባት ሁሉም ህዝቦች በየትኛው ብሔር ውስጥ ለእግዚአብሔር እንዲገዙ ማድረግ ነው። እናም በክርስትና ውስጥ እግዚአብሔርን በራሴ ባህል ውስጥ ካላመለክሁ በእምነቴ ቋሚነት እና ዘላቂነት ላይታይብኝ ይችላል።
~ Carl F. Ellis, Jr. Beyond Liberation: The Gospel in the Black American Experience. Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 1983, p. 137.
የአሲሲው ፍራንሲስ (1181 - 1226) የጣሊያን ቤተክርስቲያን መሪ እና ሰባኪ ነበር። ስለ ክርስቶስ በመሰጠት የሚሰብኩና ስለ ክርስቶስና ሌሎችን ለማገልገል ራስን በመካድ የድህነት ኑሮን ለመኖር የቆረጡ ሰዎችን የፍራንሲ ስርዓት በሚል መጠሪያ የተለያዩ ቡድኖችን አደራጅቶ ነበር። በህይወቱ ዘመን በሙሉ ሌሎች ስርዓቶችን እንዲያደራጁ አግዟቸዋል። በታሪክ ውስጥ እጅግ በጣም የተከበሩ ከተባሉት ክርስቲያኖች መካከል አንዱ ነበር።
ጸሎት
የአሲሲው ፍራንሲስ የመታሰቢያ ጸሎት
ጌታ ሆይ የሰላምህ መሣሪያ አድርገኝ ጥላቻ በሚኖርበት ጊዜ ፍቅርን እንድዘራ ጉዳት በሚኖርበት ጊዜ ይቅርታን ጥርጣሬ በሚኖርበት ጊዜ እምነትን ተስፋ መቁረጥ በሚኖርበት ጊዜ ተስፋን ጨለማ በሚሆንበት ጊዜ ብርሃንን ሃዘን በሚኖርበት ጊዜ ደስታን
ኦ መለኮታዊ መምህር ሆይ እኔ ብዙ መጽናናትን ከመፈለግ ይልቅ ማጽናናትን ስጠኝ ሌሎች እንዲረዱኝ ከመፈለግ ይልቅ ሌሎችን መረዳትን በብዙ ከመፈቀር ይልቅ ፍቅርን በመስጠት ውስጥ መቀበል አለና ይቅር በማለት ይቅርታን ማግኘት አለና በመሞት ለዘለአለም ህይወት ህያው እንሆናለንና
~ Don L. Davis. A Sojourner’s Quest . Wichita, KS: The Urban Ministry Institute, 2010, pp. 95.
የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ዘለአለማዊው እግዚአብሔር ሆይ በክርስቶስ አካል ውስጥ ስላስቀመጠኝ አመሰግናለሁ። የክርስትና ህይወቴን በራሴ ብቻ እንዳልኖር ይልቁንም አንተን
ለጌታ የልብ ጩኽት
Made with FlippingBook - Online magazine maker