Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

ትምህርት 6 እኛ የምንፈልገው መታንጽ • 81

3. “ከክርስቲያኖች መካከል ጓደኞችን ማፍራት ቀላል አይደለም።” ቤተ ክርስቲያን የሚካፈሉ ብዙ ክርስቲያኖች ከሚገጥማቸው ችግሮች መካከል አንዱ የግል ጓደኛን ለማፍራት መቸገር ነው። በአጥቢያ አብያተ-ክርስቲያናት ውስጥ ምን እንኳን ብዙ ሰዎች በንቃት ቢሳተፉም ከነዚህ አባላቶቹ መካከል አንድም የቅርብ ጓደኛ ለማፍራት መቸገር እጅግ የሚገርም ነገር ነው። ለመጀመር ያህል የግል ጓደኝነት አስፈላጊ ቢሆንም ነገር ግን ውድ ወይም ዋጋ የሚያስከፍል ነው። ጓደኛ እንዲኖሮት ከፈለጉ በፍቅር ከሰዎች ጋር ለመገናኘት ክፍት መሆን አለብዎት (ምሳ 17፡17)፣ ሰዎች እንዲያውቅዎት እና እንዲረድዎት ፈቃደኞች ይሁኑ (ዮሐ 15፡14-14)፣ እንዲሁም እርስዎም በሚያደርጉዋቸውና ሊያስተካክሏቸው በሚገቡ ነገሮች ላይ ሰዎች ለሚሰጥዎት አስተያየት እንዲሁም ትችትን ለመቀበል ዝግጁ መሆንን ይጠይቃል (ምሳ 27፡ 6)። ጓደኞች በክርስቶስ እንድናድግ የሚያስፈልገንን ብርታትን እና ምክርን ይሰጣሉ (ምሳ 27፡ 9)። መንፈሳዊ ስጦታዎቻችንን እርስበርሳችን ስንጠቀምና ስንተናነጽ ቢለዋን ቢላ እንደመሳል ዓይነት ነው። በተመሳሳይ መንገድ አንድ ብረት አንድ ሌላ ብረት እንደሚስል እንዲሁ አንድ ሰው ደግሞ ሌላውን ይስላል (ምሳሌ 27፡17)። እነዚህን እውነቶች መሰረት በማድረግ በአጥቢያ ቤተክርስትያንህ ውስጥ ከሌሎች ጋር ጠንካራና ትርጉም ያለው ግንኙነት ለመመሥረት ከፈለግህ በአሁኑ ጊዜ ለአንተ በጣም አስፈላጊው በገር ምን ማደርግ ነው? ጌታ ኢየሱስ እንደ ደቀመዝሙር ሆነ እንድናድግ እንዲሁም ብቻችንን ሳይሆን በእምነት ባልንጀሮቻችን ከሆኑ ከሌሎች አማኞች ጋር በህብረትና በአንድነት መልካሙን የእምነት ገድል እንድንጋደል ይፈልጋል። በቤተ ክርስቲያን ብዙ ጊዜ በቋሚነት የማትካፈሉ ከሆናችሁ አሁኑኑ የኅብረት አባል ለመሆን ቃል ግቡ። በእምነት የጎለመሱ አማኞች በየሳምንቱ ለአምልኮ የሚሰበሰቡበትን ቦታ ይጠይቁና በዚያ ለመሄድና ለመካፈል ቁርጠኝነትን ያሳዩ። ለአዳዲስ አባላት ስላላቸው መደበኛ ትምህርት ይጠይቁ እና በሰንበት ትምህርት ክፍልና / ወይም በትንሽ ይመጽሐፍ ቅዱስ ቡድን ጥናት፣ ወይም የሕዋስ ቡድን መከታተል ይጀምሩ። ተስፋ አትቁረጡ ነገር ግን ሌሎች አማኞችን በትዕግስት ለማወቅ ጥረትን ያድርጉ፣ ሊሎችን ለማነጽና ለመገንዳት ስጦታዎችዎን ይጠቀሙ ከእነርሱም ለመማር ይወስኑ። በተጨማሪም መጋቢዎቹን (ወይም መሪዎችዎ፣ ወይም ሽማግሌዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ በሚከተሉተ የመሪነት መጠሪያ የሚጠሩ መሪዎችን) ለማወቅ ጥረት አድርጉ። በቤተክርስቲያኗ እንደምትካፈሉ እና ለእነሱ እየጸለያችሁ እንደሆን እንዲያውቁ ያድርጉ። እርሶ መጎብኝት እንደሚፈልጉ ይጠይቁ እና ማንነትዎን ለነሱ በተገቢው ያስተዋውቁ። መሪዎቻችሁ የሚሰጧችሁን ትዕዛዝ በመታዘዝ እንዲሁም ለእነርሱ በጥንቃቄ በመታዘዝ ታዛዦች መሪዎቻችሁ በበለጠ መንገድ እንዲመሩዎት ይርዷቸው፤ ምክንያቱም እነርሱ እረኛ በጎቹን እንደሚጠብቅ የእናንተን መንፈሳዊ ህይወት ለመጠበቅ የተሾሙና እንዲሁም በዚህ ጉዳይ ላይ ለሠሩት ነገር ለእግዚአብሔር መልስ የሚሰጡ ናቸውና። መሪዎችህ ይህ ጥሪያቸውን በደስታ እንዲፈጽሙ ይርዷቸው እንጂ እናንተ በምተሰጡት ምላሽ በማጉረምረም እንዳይኖሩ እርዷቸው ምክኒያቱም ይህ ለእናንተ ምንም ረብ ይለውምና(ዕብ 13፡17)። ከሌሎች ጋር በኅብረት ውስጥ ለመኖር ጠንካራ እምነት እንዲኖሮት የአዕምሮ ቅድመዝግጅት ያድርጉ። እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር በሚያደርጉት ጠንካራ ክርስቲያናዊ ሕይወት ወደፊት ሲጓዙ ጸጋን ይሰጣችኋል።

ማዛመድ

ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን እርስ በርሳቸው እንዲዋደዱ ስላዘዛቸው እኔም በቤተክርስቲያን በህብረት ላለ ሕይወት ለይቅርታና እርስ በእርስ ለመገዛት ራሴን እሰጣለሁ።

ማረጋገጫ /ማፅኛ

Made with FlippingBook - Online magazine maker