Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

80 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ

በተጨማሪም እርስ በርስ በፍቅር መገሳስጽን፣ መልካም ተግባሮችን ለማድረግ፣ እና ከዚህ በፊት በእምነት በክርስቶስ የእግዚአብሔር ህዝብ ከመሆናችን በፊት እናደርጋቸው የነበሩትን ክፉ ነገሮችን እንድንቃወም ተጠርተናል። መልካሙን የእምነት ገድል በትክክል ልንጋደል የምንችለው በእውነተኛ ክርስቲያናዊው ማህበረሰብ ውስጥ ከክርስትና ወታደሮች ጋር በመሆን እና የእግዚአብሔርን ቃል በማስተማር በሚያንጹን እና በሚያበረታቱን እንዲሁም በመንፈሳዊ ህይወታቸው ምሳሌ በሚሆኑን መንፈሳዊ መሪዎች ስር በመሆን ነው።

የሚከተሉትን ተጨማሪ ትምህርቶችን ከዚህ ትምህርት ጋር ተያያዥነት ላላቸው ነገሮች ማጥናትና ማሰላሰል እንዲችሉ የተጨመሩ ናቸው

ተጨማሪ አባሪ

በእርሱ ላይ ጥገኛ የመሆናችን መግለጫ-በክርስቶስ ያለን ነጻነት (ተጨማሪ አባሪ 9) ለመወከል ብቁ መሆን: የእግዚአብሔር መንግሥት ደቀ-መዝሙርትን ማብዛት (ተጨማሪ አባሪ 20) የ ኦኮስ ሁኔታ (ተጨማሪ አባሪ 10)

እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት። (ዮሐ. 13.34)

ቁልፍ መርሆች

ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ፅሁፎች ላይ በመመርኮዝ የሚከተሉትን ክርክሮች እና ጽንሰ ሐሳቦች ያንብቡ እና ያብራሩ እና መልስም ይስጡ።

የናሙና ጥናቶች

1. “ምን ምን ዓይነት መንፈሳዊ ስጦታዎች አሉኝ? እንዴትስ ልጠቀምባቸው እችላለሁ?” መጽሐፍ ቅዱስ እያንዳንዱ ክርስቲያን በቤተክርስቲያን ውስጥ ሌሎችን ለማነጽና ለመገንባት የሚስቻለውን ወይም የሚያስችላትን መንፈሳዊ ስጦታዎች ይሰጣቸዋል (ሮሜ 12፡3-8 1 ቆሮ 12፡4-11 ኤፌ 4፡9-15 1 ጴጥ 4፡10-11)። እነዚህ ስጦታዎች አማኞች እርስ በእርስ በህብረት አብረው ሲኖሩ በአገልግሎት ውስጥ ሲሳተፉ እና በአንድ መጋቢ መንፈሳዊ እንክብካቤ ስር ሆነው አብረው ሲያድጉ ሊጠቀሙባቸው ይገባል። የእኛ ስጦታ ምን ሊሆን እንደሚችል ከመጨቃጨቅና ከመከራከር ይልቅ ሌሎች ማገልገል እና እነርሱን መንከባከብ የበለጠ አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድን ነው? 2. “በየሳምንቱ በቤተ ክርስቲያን በቋሚነት እስከተሳተፍኩ ድረስ ቤተክርስቲያን በአባልነት መመዝገብ ወይም አባል መሆን አለብኝ?” ደቀመዝሙርትን በማፍራት እና ሌሎችን ማነጽ (መገንባት) አገልግሎት የአጥቢያ ቤተክርስቲያን ሚና ምን ሊሆንይገባል በሚለው ሃሳብ ላይ ውይይት ሲደረግ አንድ አዲስ አማኝ በቤተክርስቲያን ተሳትፎ ውስጥ ስላላት ስለ ራሷ ልምምድ “አሁን እኔ ወደምሄድበት ቤተክርስቲያን መሄድ ያስደስተኛል። አምልኮውን እና የመጋቢውን ስብከት እወዳለው እናም አገልግሎታቸው አጭር እና ጣፋጭ ነው። በርግጥ ከልቤ ነው የምላችሁ እኔ በቤተክርስቲያንን እንደ አባል የመመዝገብና አባል የመሆንፍላጎትየለኝም። ልክ እንደኔ የእሁድ አምልኮን ብቻ የሚካፈሉትን ነገር ግን በትንንሽ የመጽሐፍ ቅዱስ ህብረቶች ያልታቅፉትንና በሌሎች ፕሮግራሞች የማይሳትፉ ክርስቲያኖችን አውቃለሁ። ይህ ተመችቶኛል። ታዲያ በየሳምንቱ እዚያ እየሄድኩ መካፈሌ ተመችቶኝ ሳለ የቤተክርስቲያን አባል መሆን አለብኝን?” በዚህ ጥናት ውስጥ በተማራችሁትን መሠረት ይህችን በጌታ የሆነችን እህት ከእሁድ ማለዳ አምልኮ ባሻገር የቤተ ክርስቲያን አባል የመሆንን አስፈላጊነት እንዴት በጥልቀት ልታስረዷት ትችላላቸሁ?

Made with FlippingBook - Online magazine maker