Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
ትምህርት 6 እኛ የምንፈልገው መታንጽ • 79
9. ጠላት ዲያቢሎስ ሁልጊዜ እግዚአብሔር አንድ ነገር ከእኛ እንደዳስቀረብን አልያም እንደያዘብን በማሳሰብ እኛ በክርስቶስ ስላለን ብቃት ሁልጊዜ ይዋሻል። ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ለህይወት እና ለመልካም ነገር የሚያስፈልጉን ነገሮች በሙሉ እንደሰጠን እና እንዳለን ያረጋግጣል።
ሀ. ዘፍጥረት 3: 7ን ያንብቡ። እባቡ ሔዋን እግዚአብሔር የሆነ ነገር እንደደበቃት እንድታምን ምን ውሸት ነገራት?
ለ. 2 ጴጥሮስ 1፡3 አንብቡና የሚከትሉትን ባዶ ቦታዎች ይሙሉ።
የመለኮቱ ኃይል በገዛ _________________________________ ነገር ሁሉ ____________________________ _________ሰጠን።
በትክክለኛው የክርስትና ጎዳና ላይ እየተጓዙ ካሉ ቅዱሳን ጋር– በጎዳናው ላይ ካሉት ጋር ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በጌታ ነገር ርቀው ከሄዱት ጋር መገናኘትና ህብረትን ማደረግ ለእኛ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። ምክኒያቱም ወደ እግዚአብሄር አምላክ የሚቀርቡ ሰዎች ወደ እርሱ እንድንቀርብ የሚያስችለን ችሎታና አቅም አላቸው፤ ምክንያቱም እነሱ እኛን ይዘው የመሄድ አቅም አላቸውና።
~ Teresa of Avila. Richard J. Foster and James Bryan Smith, Eds. Devotional Classics: Revised Edition: Selected Readings for Individuals and Groups. Renovare, Inc. (HarperCollins Publishers), New York. 1993, p. 165.
እግዚአብሔር እያንዳንዱ አማኝ እንዲገነባ (እንዲታነጽ)፣ በክርስቶስ ባለ እውቀት ወደ ብስለት እንዲያድግ እና ሌሎችን እንዴት መገንባት ምን ማለት እንደሆነ እንድናውቅ ይፈልጋል። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በአጥቢያ ቤተ-ክርስቲያን ማለትም በአማኞች ኅብረት ውስጥ በምናደርገው ተሳትፎ ውስጥ በእምነታችን እንድናድግ ፈቃዱ ነው። እግዚአብሄር ከእውነትኛ መንፈሳዊ ፓስተሮችን ምሳሌ እና አስተምህሮ መማር እንድንችል እና እርስ በርስ አንዱ ለአንዱ በመታዘዝና በፍቅር ከሌሎች የእምነት ባልንጀሮች ጋር አብረን ለመኖር እንድንችል እና መልካሙን የእምነት ገድል እንድንጋደል አዝዞናል። ለዚህ የዕድገት ጎዳና የእግዚአብሔር ብቸኛ መንገድ የእርሱ እውነተኛ አፍቃሪ የሆኑት የክርስቲያን ማኅበረሰብ ማለትም በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ናት። እኛ አሁን በእግዚኣብሄር ታሪክ ውስጥ የእኛ ን ድርሻ እየተጫወትን ነው! እያንዳንዳችን የክርስቶስን አካል ለማሳደግ፣ ለአምልኮ ስንሰበሰብ እና ወይም ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በትንንሽ ቡድኖች ውስጥ ስንገናኝ ልናሳድገው የምንችለው ልዩ መንፈሳዊ ስጦታ ተሰጥቶናል። እግዚአብሔር እንደወደደን እኛም እርስ በርስ እንድንዋደድ የእግዚአብሔር ዓላማ ነው።ይህም በመንፈስ ቅዱስ ስንመራ እና እግዚአብሄር በሰጠን እረኞች (ፓስተሮች) ስንመግብ እና አንድ ላይ በመሆንና በመታዘዝ የምንማረው ነገር ነው። ከሌሎች አማኞች ጋር ጓደኝነት ለመመስረት መጣር አለብን፣ ወደ ህይወታችን እና ወደ ቤቶቻችን በመጋበዝ እና ወዳጅነትን ማዳብርና እና አብረን ለመጫወት ጊዜን ለማሳለፍ መጣር አለብን። እኛ አሁን የእግዚአብሄር ቤተሰቦች ነን፤ እናም እንደ አንድ የቤተሰብ አባል አንድ ላይ መሆንን መማር አለብን።
ማጠቃለያ
Made with FlippingBook - Online magazine maker