Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
ትምህርት 7 እኛ የምንዋጋው ጠላት በእግዚአብሔር ጠላቶች ላይ በድል መመላለስ
የዚህ ጉዳይ እውነታው የምንዋጋው ከሌሎች የሰው ልጆች ጋር ማለትም ከደምና ከስጋ ጋር አይደለም ማለታችን ነው። ይልቁንም ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር አሁን በጽንፈዓለም ላይ ከሚሰሩት ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካሉ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።
~ ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች (ኤፌ. 6፡12)
በዚህ ትምህርት በመጨረሻ ላይ የሚከተሉትን መርሆች በመገንዘብና በማመን የምንዋጋውን ጠላት እውነታዎች ምን እንደሆነ እንረዳለን። • አጽናፈ ዓለሙ በመንፈሳዊ ጦርነትውስጥ ነው፤ ማለትም የዲያቢሊስና የጨለማው መንግስት ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ከብርሃን መንግስት ጋር ማለት ነው “እኛ ከስጋና ከደም ጋር አንጋደልምና”። • ክርስቶስ በዚህ በወደቀው የዓለም ሥርዓት እና በድሮው ኃጢአተኛው ተፈጥሮ በኩል እያታለለ አሁን የሚሰራውን ጠላታችንን ማለትም ዲያብሎስን አሸንፏል “የሥጋ ምኞቶች”። • ኢየሱስ በመስቀል ላይ ስለ ኃጢአት ያለውን ድል እንዳገኘን ካመንን፣ ካወጅን፣ እኛን ለማታለል የዲያብሎስን ትጥቅ በንቃት ከተከታተልን፣ እና በጠላታችን ላይ ፈጽመን ለመቆም እግዚአብሄር የገባልንን ቃል ኪዳን ጋር ከተጣበቅን እኛም ድል እንነሳዋለን። ዘለዓማዊ አምላክ አባቴ ሆይ በቃልህ እንደተናገርክ አንተ የእውቀት እና የጥበብ ሁሉ ምንጭ ነህ። ይህም እውነት መሆኑን አምናለሁ አውጃለሁም፣ እናም ውድ አባቴ ሆይ የእውነትን ቃል በትክክለኛ መንገድ ማካፈል እንድችል መለኮታዊ ጥበብ እንድትሞላብኝ እጠይቃለሁ (2 ኛ ጢሞቴዎስ 2፡15)። እባክህ ውድ አባቴ ሆይ የምሄድበትን መንገድ ምራኝና አስተምርኝ (መዝሙር 32፡8) እርምጃዬንም አቅና። ድምፅህን ለመስማት ጆሮዬን አዘንብል አስተሳሰቤን እና ንግግሬን አቅና እናም ከስህተት በመመለስ በትክክለኛው መንገድ እንድሄድ ምራኝ። አባት ሆይ የማስተዋል እና የመለየትን ስጦታን ስጠኝ እናም ቃልህን በምማርበት ጊዜ በእውነተኛውና በሃሰተኛው ትምህርቶች፣ መናፍስትና ጸጋዎች መካከል ያለውን ልዩነት እንድረዳ እርዳኝ። በመንፈስ ቅዱስህ ፈቃድህን አሳየኝ ፈቃድህንም በሙሉ ልቤ መቀበልና መያዝ እንድችል ማስተዋልን ስጠኝ። የተከበርክ ጌታ ሆይ እባክህን ለመስማት እና ለማዳመ የፈጠንሁ ፤ ለመናገርና ለቁጣ ግን የዘገየሁ እንድሆን እርዳኝ (ያዕቆብ 1፡19)። የአፌም ቃልና የልቤ ሃሳብ በአንተ ዘንድ ተቀባይነት ይኑራቸው። ሰው ሁሉ እውነትህ ሊረዳና ሊያተርፍበት እንዲችል እውነትህን የምናገርበትን ጥበብን ሥጠኝ።
ዓላማ
ለጥበብ የመግቢያ ጸሎት
በዚህ ጥናት ቃልህንና መመሪያህን እንድቀበል አስተምረኝ። ይህንን ሁሉ ጌታዬና አዳኜ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ብርቱ ስም እጠይቃለሁ አሜን።
85
Made with FlippingBook - Online magazine maker