Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
86 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
1. “እነዚህ ሰዎች ለእግዚአብሔር የተገቡ አይደሉም- እነዚህ ሰዎች የጌታ ጠላቶች አይደሉምን?”በምንኖርበት ዓለም ውስጥ በሁሉ ስፍራ በሃይማኖት ምክንያት ጦርነትና ግጭቶች ሲበዙ እንዲሁም ዓመጽ እየጨመረ ሲመጣ ስናይ እንዲሁ በደምሳሳው ስናይ ውጊያው ከሰው ልጆች ጋር ይመስለናል። በዓለም ዙሪያ እግዚአብሔርን እንደሚያውቁ የሚናገሩት ሰዎች መናፍቃን እንደሆኑ ወይም ክፉ እንደሆኑ አድርገው የሚያሰቧቸውን ስዎች እየገደሉ ነው።. በእርግጠኝነት ብዙ ሰዎች በዓለም ላይ ግድየለሽነት በተሞላበት ስህተት እስክ እርስ በእርስ መገዳገል ድረስ አስከፊና አደገኛ የሆኑ ነገሮችን እያደረጉ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ግን ውጊያው ከሥጋ እና ከደም (ሰብዓዊ ፍጡሮች) ጋር አይደለም ነገር ግን በሰዎች በኩልና በሰዎች ውስጥ አስነዋሪ ነገሮችን እንዲፈጽሙ ከሚያደርጉት መንፈሳዊ ኃይሎች ጋር ነው። ይህ እውነት ለአዲስ ወይም በእምነት ለሚጎለምሱ ክርስቲያኖች መረዳት እና ተግባራዊ ማድረግ ለምን አስፈለገ? አስደንጋጭ ፊልሞች ዓይነት - አስቀያሚና ያልተለመዱ ሞንስተሮች ንጹሃንን እና አቅም ዓልባ የሆኑ ሰዎችን በጨለማ ዋሻዎች እና በእሾሃማ ቤቶች ውስጥ ሲያሳድዱ የሚያሳይ እንዳልሆነ ያሳየናል። የዲያቢሎስ በጣም ውጤታማ የሆኑ መሳሪያዎች ሽንገላ፣ ውሸት እንዲሁም የተዋቡና ምንም ጉዳት የሌላቸው ሊታመኑ የሚችሉ እና እምነት የሚጣልባቸው የሚመስሉ ክርክሮች ናቸው። እነዚህ ውሸቶች አምላክ እንደሌለ፣ መንፈሳዊነት ተራ ነገር እንደሆነና ሳይንስ ብቻውን የሰው ልጆችን ከጥፋታቸው ሊያድናቸው እንደሚችል ይጠቁማሉ። የእኛ ጠላት መሳሪያ ሚስጥራዊ አይደለም። በአጠቃላይ ዲያቢሎስ ውሸታም እና የውሸት አባት ነው። በሳይንሳዊ ማረጋገጫ እና በቴክኖሎጂ ግኝት በጣም ላተኮረው ማህበረሰብ ዲያቢሎስ ለምንድን ነው ውሸትን በኅብረተሰባችን ውስጥ እንደ ዋነኛ መሣሪያ ያደረገው? 3. “ምንም እንኳን ድላችሁ የተረጋገጠ ቢሆንም፣ ለእሱ መታገል አለባችሁ።” ሐዋርያት በትምህርታቸው ዓፅንዖት ከሰጧቸው ነገሮች መካከል አንዱ በእግዚአብሔር ታሪክ ውስጥ የራሳችንን ድርሻ መጫወት እንዳለብን ነው። በቀላል አነጋገር ለማስቀመጥ ምንም እንኳን እግዚአብሔር ጠላታችን ዲያቢሎስን ድል ቢነሳውም እሱ ግን ሊቋቋም እና ሊቃወም ይችላል። ምንም እንኳን ጌታችን ኢየሱስ በመስቀል ላይ ድል ቢቀዳጅም ድሉ ግን አውቶማቲክ(ልፋትና ድካም የሌለበት) አይደለም። ምንም እንኳን እግዚአብሔር በፈሰሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ነፃ ቢያወጣንም ነገር ግን ያንን እውነት በማረጋገጥ እና ውሸቶችን ባለመቀበል አሁን ያንን ድል በተግባር ማዋል ያስፈልገናል። ይህን ስናደርግ በባህሪያችን፣ በማንነታችን እና በአመለካከታችን እንለውጣለ። ይህ ድል የእኛ ነው፤ ነገር ግን በየቀኑና በእያንዳንዱ ሁኔታ ላይ መጋደል፣ መከላከል እና መተግበር አለበት። እግዚአብሔር አማኞችን ለእርሱ እንዲገዙ ዲያብሎስን ገን እንዲቃወሙት አዝዞአል እናም በዚህም ብቻ ጠላት ከእኛ ይሸሻል። ለምን ይመስልዎታል ጌታ እኛ ድል እንድናገኝ ጠላትን በመጋፈጥ እና ዲያቢሎስ እኛን ለመጉዳት፣ ለማታለል፣ እና ለማሸነፍ የሚያደረጋቸውን ማናቸውም ሙከራዎች ከተቃወምን በኋላ እንዲሆን ያደረገው? 2. “የዲያቢሎስ ሚስጥራዊ ያልሆነ ድብቅ መሣሪያ።:” መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንዳስቀመጠው የዲያቢሎስ ውጊያ ልክ እንድ አሜሪካ የፊልሚ ኢንዱስትሪ እንደ ሆሊውድ አስፈሪና ባለፈው ክፍለ ጊዜ (እኝ የምንሻው መታነጽ) በሚለው ትምህርት ስር እርስ በራስ መዋደድ እንዳለብን እና በአጥቢያ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ በመታቀፍ አንዳችን ለሌላችን እንድንገዛ ተምረናል። አሁን በዚህ ክፍልደግሞ መልካሙ የእምነት ገድል ስንጋደል ጠላታችንን በበለጠ እናውቀዋለን። በሰይጣን ዲያቢሎስ ምክንያት ዓጽናፈ ዓለሙ በሙሉ በጦርነት ላይ ነው እናም እኛ በዚህ ጦርነት ውስጥ ተዋጊዎች ነን። ገለልተኝነት ሊኖር አይችልም። ባለጋራችን ዲያቢሎስ ብዙ ርኩስና በተንኮል የተሞሉ መናፍስትን ይመራል። እነሱ የወደቀውን ዓለምን ባህሪ እና የገዛ ስጋችንን ፍላጎቶች
ማዛመድ
ይዘት
Made with FlippingBook - Online magazine maker