Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

ትምህርት 7 እኛ የምንዋጋው ጠላት • 87

በመጠቀም የእግዚአብሔርን ሥራ ለመቃወም ይጠቀማሉ፤ ስለዚህ ከሚሰነዝሯቸው ሴራዎች ጥቃቶች በሙሉ እራሳችንን መጠበቅ አለብን። በተጨማሪም ማንም ሰው ጠላታችን እንዳልሆነ ማወቅ አለብን። ምንም እንኳን በሁሉም አቅጣጫ መንፈሳዊ አደጋዎች ቢያጋጥሙንም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለሆነ እና ስለሚረዳን የቱንም ያህል የጠላቶቻችን ትጥረቶች ቢፈታተኑንም መልካሙን የእምነት ገድል በድልን እንድናጠናቅቅ ይረዳናል። ምንም እንኳን ኢየሱስ ለሁሉም ክርስቲያኖች በዲያብሎስ ላይ ድል የተቀዳጅ ቢሆንም፤ እኛ አሁንም ጠላትን ለመዋጋት፣ እራስን ለመግዛት እና ንቁ በሆነ መንገድ መጋደል አለብን። ጠላት (ሰይጣን) እኛን ለመጉዳት፣ ለማጥቃት እና ለማጥፋት የሚያመቹ ምቹ ሁኔታዎቸን ያለማቋረጥ እየፈለገ ስለሆነ ጠንቃቃ እና ንቁ መሆን አለብን። እኛ ክርስቶስን ስንከተል በመንፈሳዊ ህይወታችን ለማሸነፍ በውሸት እና በክስ መንፈስ አማኞችን ማጥቃት፣ ተስፋ ማስቆረጥ እና ማሸነፍ ይፈልጋል። እንግዲያው ዲያብሎስን እንዴት በተሳካ ሁኔታ ፀንተን ለመቃወም እንደምንችል መማር አለብን። ራሳችንን ከጥቃቱ መጠበቅ አለብን፣ እውነትን ለራሳችንን መናገር አለብን፣ ሙሉ በሙሉ በክርስቶስ ላይ እንድንታመንን ማረጋገጥ አለብን። በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መጓዝ እና በእምነታችን እውነቶች ላይ ጸንተን መቆም አለብን። በተጨማሪም በዚህ ውጊያ ውስጥ ብቻችንን አለመሆናችንን አስታውሱ፤ በዓለም ዙሪያ ያሉ ሌሎች ክርስቲያኖችም በራሳቸው ውጊያ ውስጥ ናቸው። በርግጥ ምንም እንኳን ጦርነቱ ሃይለኛ፣ ቋሚ እና በየቀኑ ቢሆንም በመጨረሻ ላይ ግን የእግዚአብሔር ጸጋ የመጨረሻውን ድል እንደሚሰጠን እርግጠኞች መሆን እንችላለን። ሥቃያችን ለጥቂት ጊዜ ብቻ ነው የሚቆየው ነገር ግን በክርስቶስ የምናገኘው ክብር ዘላለማዊ ነው። እግዚአብሔር ራሱ እንደገና ያድሰናል፣ ብርቱ ያደርገናል፣ ውጊያውን እስከምናጠናቅቅ ድረስ ጸንተን እንድንቆም እና እንድንጸና ያግዘናል! ምንም እንኳን እናንተ እና እኔ ከጨለማው መንግስት ወደ ውዱ የእግዚአብሔር ልጅ መንግሥት መንግስት ብንፈልስም፤ አሁንም የእግዚአብሄር ታላቅ ጠላት በሆነ በሰይጣን ቁጥጥር ስር በሆነ ባሕልና ያአኗኗር ዘይቤ ተከብበናል። ክርስቶስን እንደ አዳኛችን ከተቀበልንበት ጊዜ አንስቶ ፍርዱ እስከሚገለጥበት ጊዜ ድረስ በዚህ ውስጥ መኖር ግድ ነው። በርግጥ በአንድ ወቅት እኛን የመራን ንጉሣችን ቢሆንም አሁን ግን የመደብ ጠላታችን ነው። አንድ ክርስቲያን በጠላት ግዛት ውስጥ እየኖር መንፈሳዊ ጦርነት አይኖርብኝም ብሎ መጠብቅ አላዋቂነት ነው።

~ Francis Schaeffer. The Complete Works of Francis Schaeffer

Volume 2: Joshua and the Flow of Biblical History. Westchester, IL: Crossway Books, 1975, page 210.

እኛ የምንዋጋው ጠላት ትምህርት 7 የመጽሃፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ያንብቡ እና ከእያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ጋር የተያያዙትን ጥያቄዎች አጠር ያለ መልስ ይስጡ። 1. ዲያቢሎስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እና መንግሥት ከመጀመሪያው ሲቃወም ኖሯል፤ እናም ይህ ዓመፅ በአዳኛችን እና በጌታቸን በኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚወረወር ያውቃል። የሚከተሉትን ጥቅሶች ከትክክለኛው ሀረጎቻቸው ጋር ያዛምዱ:

Made with FlippingBook - Online magazine maker