Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
88 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
ሀ. ዘፍ 3፡1-15
______ መላው ዓለም ከዲያቢሎስ ቁጥጥር ሥር ነው
ለ. ኢሳ. 14፡12-17 ______ ዲያቢሎስ ፍጹም ሆኖ ተፈጥሮ ነበረ፤ ግን በእግዚአብሔር ላይ አመጸ
ሐ. ሕዝ. 28፡12-17 ______ ሰይጣኑ ልክ እንደ ጌታ ለመሆን ወስኗል
መ. 1 ዮሐ 3፡8-10 ______ ጌታ ኢየሱስ የዲያቢሎሰን ሥራ ያፈርስ ዘንድ ወደምድር መጣ
ሠ. ራእይ 12፡7-11
______ እርሱም ሰይጣንን የዓለም ሁሉ አታላይ ብሎ ይጠራዋል
ረ. 1ኛ ዮሐንስ 5፡19 ______ ዲያቢሎስ የመጀመሪያዎቹን ሰብዓዊ ጥንዶች ዋሸ፤ ውድቀትን አስከተለ
ሰ. 2 ቆሮ. 2፡11
______ ሰይጣን የተለመዱ ስልቶችን ይጠቀማል እኛም የእርሱን ሴራዎች ለይተን ልናውቅ ይገባል
2. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዲያብሎስን ሥራ ለማፍረስ፣ ለማሸነፍ እና ድል ለመንሳት መጥቷል - የሰው ልጆችን ለእግዚአብሔር ባለመታዘዝ ምክንያት ከመጣባቸው እርግማን ነፃ ለማውጣት መጣ። ሉቃስ 11፡14-23 ያንብቡ እና የሚከተሉትን ጥያቄዎች ይመልሱ
ሀ. ጌታ ኢየሱስ አጋንንትን ባወጣበት ጊዜ ሰዎች ኢየሱስን ስለሚሰራው ስራ ምን ክስ አቅርበው ነበር?
ለ. ኢየሱስ በአጋንንት አለቃ በብዔልዜቡል አማካኝነት አጋንንትን ታስወጣለህ ለሚለው ክስ ምላሽ የሰጠው እንዴት ነው?
ሐ. ኢየሱስ የእርሱ ንብረት እንዲበዘብዝ “ኃይለኛውን ሰው” ድል መንሳት እንደሚያስፈልግ የሚገልጽ ምሳሌ ተናግሮ ነበር። የዚህን ዓረፍተ ነገር ትርጉም ግለፅ።
3. ሰይጣን በአለም ላይ ክርስቶስን የሚወክሉ አማኞችን ለማታለል፣ ለመጉዳት እና ተስፋ ለማስቆረጥ ውሸትን፣ ውንጀላዎችን እና ማታለያዎችን ይጠቀማል። የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ከትክክለኛው ገለፃዎች ጋር ያዛምዱ።
ሀ. የዮሐንስ ወንጌል 10፡1-18 ______ ኢየሱስ መልካም የበጎች እረኛ ነው፤ ጠላት ግን ለመስረቅ፣ ለመግደል እና ለማጥፋት ይመጣል
ለ. ዮሐንስ 8፡31-44
______ ሰይጣን ዲያብሎስ ውሸታምና የውሸት አባት ነው
ሐ. ራዕይ 12፡9-10
______ ሰይጣን ክርስቲያኖችን በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ይከስሳል
Made with FlippingBook - Online magazine maker