Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

መግቢያ • 9

ከሌሎች ጋር አብረን የክርስትና ህይወትን ለመኖር የእርሱን እውነት በመረዳት እግዚአብሔርን በማምለክ እና እንደ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት አብረን እያደጉ ለመሄድ ተጠርተናል። ይህን በማድረግ በእምነታችን ላይ እየተገነባን (እየታነፅን) እና ስለ ክርስቶስ ክብር (በአክብሮት) አንዳንዳችን ለሌላችን እንዴት መገዛት እንዳለብን እንማራለን፡፡ ትምህርት 7 የምንዋጋው ጠላት: - በእግዚአብሔር ጠላቶች ላይ በድል መመላለስ የሚለው ትምህርት የተቀላቀልነውን ታላቅና አዲስ ታሪክ ባህሪውን ይገልጻል፡፡ ይህ ዓጽናፈ ዓለም በመንፈሳዊ ጦርነት ውስጥ ነው ያለው - ዲያቢሎስና የጨለማው መንግሥት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እና የብርሃን መንግስትን እየተዋጉ ናቸው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሕይወቱ፣ በሞቱ እና በትንሳኤው በጠላታችን ላይ ማለትም በዚህ በወደቀ ዓለም ውስጥ ያለውን ስርዓት በመጠቀም በማታለል እና በድሮው ኃጢአተኛ ተፈጥሮ ውስጥ ይህም “በሥጋ ምኞቶች” እያሰራ ባለው ዲያቢሎስ ላይ ድልን ተቀዳጅቷል። እኛም በክርስቶስ በመኖር በእምነት በመመላለስ እና ዲያቢሎስ እኛን ለመፈትን የሚጠቀመውን ማናቸውንም የውሸትና የማታለል ጥረትና ሴራዎች በንቃት ከተከላከልን ድል እንነሳዋለን፡፡ ትምህርት 8 የምንታጠቀው መሳሪያ: የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ መልበስ የሚለውን ርዕስ ይዳስሳል ። እግዚአብሔር ለእያንዳንዱን አማኝ ጠላትን ለመቋቋም እንዲችሉ እና በክፉ ቀን ሁሉን ፈጽመው ለመቆም የሚያስችላቸውን አስፈላጊውን አቅርቦተ እንዳደረገላቸው ያብራራል። የቅዱስ ቃሉ እውነት (ማለትም የእግዚአብሔር ቃል) ጠላት በእኛ ላይ የሚሰራውን ውሸት ለመለየት፤ ለመቃወም እና ለማስወገድ ያስችለናል፤ እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ በግልም ሆነ ከሌሎች አማኞች ጋር መንፈሳዊ ልምምዶችን ስንለማመድ በተጋድሎው ፀንተን እንድንቆም ብርታትንና ጥንካሬን ይሰጠናል፡፡ ትምህርት 9 የመጨረሻው ትምሕርታችን ነው፤ ይህም የምናሳየው ጽናት: - የቅዱሳን ጽናት የቅዱሳት ጽናት የሚል ርዕስ ተሰጥቶታል። በዚህ ትምህርት ውስጥ ወደ ክርስቶስ እያደገ የመሄድ ህይወት ማዕከላዊና መሰረታዊ መርሁ መፅናት፤ ንቁ መሆን እና በጠላት ከመያዝ ውጭ እንደሆነ እንመለከታለን። እንደ የክርስቶስ ተወካዮች ነገሮች የቱንም ያህል ከባድ እና አስቸጋሪ ቢሆኑም ሽልማታችንን ለማግኘት ወደፊት መግፋት እና መቀጥል አለብን፡፡ መንፈስ ቅዱስ ለተጠራንበት መጠራት በእውነት ለመቆም የሚያስችለንን ኃይል ይሰጠናል እንዲሁም ክርስቶስን በታማኝነት ስንወክልና ስንገልጥ ሌሎች አማኞችን በመንፈሳዊ ተጋድሎአቸው ጊዜ ለማበረታታና ለማጠንናከር ይጠቀምብናል፡፡ የእያንዳንዱ ክፍለ-ጊዜ ንድፍ : መሰረቶቹ እና ክፍሎች እያንዳንዱ ትምህርት አትኩሮት መስጠት በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ላይ መሰረት በማድረግ አጽነዖት መስጠት እንዲችሉ በአንድ ዓይነት ክፍፍሎች ተከፋፍሏል። (እንደ መሪም ሆነ ወይም እንደ የትንንሽ ቡድን አስተባባሪ ሆነው ይህን መፅሐፍ ከሌሎች ጋር ሆነው ሲያጠኑ ይህንን መገንዘብ በጣም ጠቃሚ ነው)። የትምህርቱ ዓላማዎች ለእያንዳንዱ ክፍለ-ጊዜ ሦስት ግቦች አሉት፤ ይህም በግልም ሆነ ወይም ከሌሎች ጋር ሆነው ሲያጠኑ በትምህርቱ ማጠቃለያ ላይ በትክክል መረዳት የሚገባችሁን እንድትረዱ እና ምን ማመን እንዳለባችሁ እንድታውቁ ይረዳችኋል፡፡ የመክፈቻ ጸሎት- ለጥበብ ይህን ጸሎት በቃላችሁ እንድትደጋግሙት እና ከፍ ባልድምጽ እንድትጸልዩት እናበረታታለን። የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶች ከማጥናታችን በፊት ጌታ ኢየሱስ ለእኛ ሊናገር ያለውን ሁሉ እንድንረዳ እና መቀበል እንድንችል ልባችንን እንዲከፍትልን እንፀልይ።

Made with FlippingBook - Online magazine maker