Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

ትምህርት 7 እኛ የምንዋጋው ጠላት • 95

በሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ውስጥ እኛ የምንጠቀማቸው መሳሪያዎች የሚለውን ትምህርት የሚከተሉትን በማካተት እንመለከታለን: 1. እግዚአብሔር በስፍራችን ላይ ጸንተን ለመቆም እንድንችል የጦር መሳሪያን ሰጥቶናል 2. እውነቱን በማመን መቆም እና ውሸት መቃወም ይኖርብናል 3. መንፈሳዊ ልምምዶችን በማዳበር በመንፈሳዊ ተጋድሎ ለመዋጋት አቅማችንን እናሳድጋለን

ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ

ዮሐ 16፡33

የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅስ ጥናት

1. ይህንን ጽሑፍ በዚህ ሳምንት ውስጥ ቢያንስ ሶስት ጊዜ ለመከለስ ግብ ያስቀምጡ። በቀን ውስጥ ሲጓዙ እውነቱን ቢያንስ ቀለል ያሉ እውነታዎችን ለራሳችሁ ጮክ ባል ድምጽ በመናገርን ተለማመዱ። ለምሳሌ, “ ሰማያዊ አባት ሆይ በኢየሱስ ክርስቶስ ባለኝ እምነት በኩል በህይወቴ ውስጥ በዲያብሎስ እና በመንገዶቹ ሁሉ ላይ ድልን ስለሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ” ወይም “ይህ ሀሳብ ከእግዚአብሔር አይደለም ውሸት ነው እና ልቀበለው አልፈልግም።” በየቀኑ በራስ ላይ በእምነት መከተልና መናገርን ስትለማመዱ አዲስ ልማዶችን መገንባት ትጀምራላችሁ። 2. እኛ ጠላት የምናሸንፍበት አንዱ መንገድ በጾም ልምምድ ውስጥ ነው። ጾም ለእግዚአብሔር እና ለትክክለኛዉ የእምነት ተጋድሎት ልዩ ትኩረት ለመስጠት ምግብን ወይም ሌሎች የተለመዱ ተግባሮችን ማቆም ነው። ወደ እግዚአብሔር ለመጸለይ፣ ቅዱስ ቃሉን ለማጥናትና ለማሰላሰል አንዱን የምግብ ሰዓታችሁን ይተው። (የራስዎ የጤና ሁኔታዎ ምግቡን መዝለል የማይፈቅድ ከሆነ በሱ ፈንታ የቴሌቪዥን ትርዒት ​ወይም የታቀደ የመዝናኛ እንቅስቃሴ ይተዉ።) 3. በዕለታዊ ማስታውሻው ውስጥ የጾም ልምዳችሁን መዝግቡ እና በቤተክርስቲያን ውስጥ በእምነት ለጎለመሰ አማኝ አካፍሉ። 4. የሚቀጥለውን የጾም ቀንዎን ያቅዱ እና በፕሮግራምዎ ውስጥ ያስቀምጡ።

የቤት ስራዎች

Made with FlippingBook - Online magazine maker