Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

ትምህርት 8 እኛ የምንጠቀመው መሳሪያ የእግዚአብሄርን ዕቃ ጦር ሁሉ መልበስ

ስለዚህ በክፉው ቀን ክፉን ሁሉ በመቃወም ትቆሙ ዘንድ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ። እንግዲህ የጽድቅንም ጥሩር ከለብሳችሁ በኋላ፥ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ ቁሙ። እንደመከላከያና እንደመሸፈኛ የሰላም ወንጌልን በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ይቁሙ። በምትጋደሉት በሁሉም ነገር ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ። እንዲሁም የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ እርሱም የእግዚአብሔርን ቃል ለመያዝ ጥንቃቄ አድርጉ።

~ ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች (ኤፌ 6፡13-17)

በዚህ ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ እኛ ስለምንጠቀማቸውን መሳሪያዎች የሚከተሉትን በማመን እንይዛለን: • እግዚአብሔር እያንዳንዱን አማኝ በጠላት ላይ ለመቋቋም እና በሁሉ ላይ ጸንተው መቆም እንዲችሉ የሚያስችላቸውን መሳሪያ ሁሉ ሰጥቷቸዋል። • የቅዱሳት መጻሕፍት እውነት (ማለትም የእግዚአብሔር ቃል) ጠላት በእኛ ላይ የሚያደርገውን ውሸት ለይተን እንደናውቅ፣ ለመቃወም እና ለመተካት ያስችለናል። • መንፈስ ቅዱስ በመንፈሳዊ ተግባራዊ ልምምዳችን በኩል ጠላት ለመዋጋትን ለመዋጋት እንድንችል አቅማችንን ያዳብራል። ዘለዓማዊ አምላክ አባቴ ሆይ በቃልህ እንደተናገርክ አንተ የእውቀት እና የጥበብ ሁሉ ምንጭ ነህ። ይህም እውነት መሆኑን አምናለሁ አውጃለሁም፣ እናም ውድ አባቴ ሆይ የእውነትን ቃል በትክክለኛ መንገድ ማካፈል እንድችል መለኮታዊ ጥበብ እንድትሞላብኝ እጠይቃለሁ (2 ኛ ጢሞቴዎስ 2፡15)። እባክህ ውድ አባቴ ሆይ የምሄድበትን መንገድ ምራኝና አስተምርኝ (መዝሙር 32፡8) እርምጃዬንም አቅና። ድምፅህን ለመስማት ጆሮዬን አዘንብል አስተሳሰቤን እና ንግግሬን አቅና እናም ከስህተት በመመለስ በትክክለኛው መንገድ እንድሄድ ምራኝ። አባት ሆይ የማስተዋል እና የመለየትን ስጦታን ስጠኝ እናም ቃልህን በምማርበት ጊዜ በእውነተኛውና በሃሰተኛው ትምህርቶች፣ መናፍስትና ጸጋዎች መካከል ያለውን ልዩነት እንድረዳ እርዳኝ። በመንፈስ ቅዱስህ ፈቃድህን አሳየኝ ፈቃድህንም በሙሉ ልቤ መቀበልና መያዝ እንድችል ማስተዋልን ስጠኝ። የተከበርክ ጌታ ሆይ እባክህን ለመስማት እና ለማዳመ የፈጠንሁ ፤ ለመናገርና ለቁጣ ግን የዘገየሁ እንድሆን እርዳኝ (ያዕቆብ 1፡19)። የአፌም ቃልና የልቤ ሃሳብ በአንተ ዘንድ ተቀባይነት ይኑራቸው። ሰው ሁሉ እውነትህ ሊረዳና ሊያተርፍበት እንዲችል እውነትህን የምናገርበትን ጥበብን ሥጠኝ።

ዓላማዎች

የመግቢያ ጸሎት ለጥበብ

በዚህ ጥናት ቃልህንና መመሪያህን እንድቀበል አስተምረኝ። ይህንን ሁሉ ጌታዬና አዳኜ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ብርቱ ስም እጠይቃለሁ አሜን።

97

Made with FlippingBook - Online magazine maker