Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
98 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
1. “ሁሉም ሰው በመንፈሳዊ ጦርነት ተካፍሏልን? ያ ልክ ትንሽ እንደ ሆሊውድ ዓይነት ነገር ይመስለኛል!” ስለ መንፈሳዊ ውጊያ ፓስተሩ ባስተላለፈው ስለ መንፈሳዊ ውጊያን ስብከት በሚመለከት እንዲት የክርስቶስ ደቀመዝሙር ከማያምኑ ጓደኞችዋ ጋር ውይይት ስታደርግ ስለ መንፈሳዊ ነገሮች እውነታ ጥርጣሬን ለመጀመሪያ ጊዜ አደረባት። የዲቢ ጓደኛ ራልፍ ዴቢ በክርስቶስ ስላላት እምነቷ የምታካፍለውን ያዳምጥ ነበር፤ ከክርስቶስ ኢየሱስ የሰው ልጆቸን የሃጢአት ዕዳ ለመክፈል እንዴት በመስቀል እንደሞተ፣የሰውን ዘር በሙሉ በሞት ፍርሃት ባርነት ውስጥ ከቶ የነበረውን የጠላትን ኃይል ድል ማድረጉን ሁሉ ያደምጥ ነበር። ዴቢ ምን አለሽ? እኛ ሁላችን በሆነ በአንድ መንፈሳዊ ውጊያ ውስጥ እንዳለን ታምኛለሽ? ዴቢም መልሳ እንዲህ አለችው “አዎ መጽሐፍ ቅዱስ መላው ጽንፈ ዓለም በጦርነት ላይ እንደሆነና የሰው ልጅም እውነተኛ ጠላት ሌላው የሰው ልጅ እንዳልሆንና ነገር ግን ክፉ ሰይጣን በውሸት እና በማታለል ሰዎች በእግዚአብሔር ላይ እንዲያምፁ እና እርስ በርሳቸው እንዲጎዳዱ እንዳደረጋቸው ።” “ ይህንን መቀበል እንደምችል አላውቅም ዴቢ። ሁሉም ሰው በመንፈሳዊ ጦርነት ውስጥ ተካትቷል ማለት ነው እያልሽኝ ነው? ያ ልክ እንድ ሆሊውድ ነገር ሆኖ ነው የሚሰማኝ! “ዴቢ ለጓደኛዋ ለራልፍ ስለመንፈሳዊ ውጊያን እውነታ ምን ዓይነት ምላሽ መመለስ እንዳለባት ትመክራታለህ? 2. “ውሸቶች በዓለም ላይ ካሉ በጣም ኃይለኛ ከሆኑት ሚሳይሎች ይልቅ እጅግ አጥፊና ጠንካራ መሣሪያዎች ናቸው።” ይህ በዓለም የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች መካከል እጅግ ታዋቂ የሆነው የሬቨረንድ ዶክተር ጆን ስቶት ውስጣዊ እይታ ነው። እርሱም በቅዱሳት መጻሕፍቱ ትርጓሜ ላይ ብዙ ያስተማረና እያንዳንዱ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር በመንፈሳዊ ውጊያ ውስጥ እንደሚሳተፉና የጦርነቱም እምብርት በእውነቱ ላይ ነው፤ ማለትም ስለአለም፣ ህይወት እና ወደፊት ስለሚመጡ ነገሮች ትክክለኛውን ትርጓሜ ነው ብሎ ይሞግታል። የቅዱስ ቃሉ እውነት (ማለትም የእግዚአብሔር ቃል) ጠላት በእኛ ላይ የሚያደርገውን የውሸት ወረራ ለይተን እንድናውቅ፣ ለመቃወም እና ለመተካት ያስችለናል። ስለዚህ አባባል “ሐሰቶች የአለም ገዳይ መሣሪያዎች ናቸው” ምን ያስባሉ? በታሪክ ውስጥ በሃሰት ምክኒያት ሰዎች እንዲሁ ውሸትን ተቀብለው ማለትም ሰዎች እንዲሁ ውሸትን እንደ እውነታ ተቀብለው በአስከፊ ሁኔታ ስለሰሯቸው ወይም በሌሎች ላይ የፈጸሙትን አሰቃቂ ነገር አንዳንድ ምሳሌዎችን ማሰብ ይችላሉ? 3. “የበለጠ ባደረጋችሁ መጠን በተሻለ ሁኔታ ታገኙታላችሁ” ሁላችንም የሰው ልጆች የራሳችን ባህላዊ ልማዶች ፍጥረቶች ነን በተለይም ይህ ሲለወጥ የሰው ልጅ ካሉት በጣም ጠቃሚ ጸባዮች መካከል አንዱ ነው። ይህ መመሪያ ቀላል ነው። አንድ ዓይነት አመለካከት፣ አስተሳሰብ፣ ልምምድ፣ ወይም ባህሪን በተደጋጋሚ በተግባር እየገለጹ በሄዱ ቁጥር ደጋግመው ማድረጉ ይቀልላል - እና በተለመደው መልኩ በተሻለ ሁኔታ ማድረግ ያስችላል። በተመሳሳይ መንገድ እኛን በመንፈሳዊነት ሊቀርጹን የሚያስችሉና ጠላትን ለመዋጋት አቅማችን የሚጨምሩ የተወሰኑ ልምዶችን ( ብዙውን ጊዜ ዲሲፕሊን በመባል የሚታወቁ) እግዚአብሔር ሰጥቶናል። የክርስቲያናዊ ሕይወት ልምዶች (ለምሳሌ ጸሎት፣ ከሌሎች አማኞች ጋር ኅብረት ማድረግ፣ ቅዱሳን ጽሑፎችን በማንበብ በማጥናትና በማስታወስ እና እግዚአብሔርን ማምለክን) የበለጠ እየፈጸምን በሄድን መጠን የበለጠ እየጠነከርን እና የጠላት ውሸቶችን መለየት እና በእምነትን መቃወም ያስችለናል። ገላ. 6፡7-9 አንብብ። ይህ የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል በንባብ፣ እውነተኛና መንፈሳዊ ልምምዶችን በትዕግስት በማድረግ አማካኝነት በክርስቶስ በብስለት ማደግ እንድንችል እንዴት ይረዱናል?
ማዛመድ
Made with FlippingBook - Online magazine maker